Category Archives: Uncategorized

ለቀጣፊው ጌታቸው ረዳ

አዴው

በኦሮሚያ ዉስጥ የተነሳዉን ህዝባዊ ተቋውሞ አስመልክቶ በህዝብ ደም መፍሰስና በህዝብ ስቃይ ተደሳቹ የህወሃት ሚኒስተር ለጋዜጠኞች ሲተርኩ ተደመጡ እኔ ደሞ የታዘብኩትን ልጽፍ ወደድኩ።

ክቡር ሚኒስተር ጌታቸው ረዳ ክቡር አልኩ መሰለኝ መቼም ሚኒስተር ከሚለዉ ፊት ክቡር ስለማይቀር ብይዬ ነዉ።የሆነው ሆኖ ብዥታ ብዥታ እያሉ ደጋግመዉ ሲለፈልፉ ተሰምተዋል በርግጥም ብዥታዉ ማደናገሪያ እንጂ ሃቅ አለመሆኑን መላዉ ህዝብም ሆነ እርሶም በደንብ ያዉቁታል። ይልቁንም ብዥታዉ እርሶ ጋር ስለሆነ በግፍ ስካር የተሞላዉ ንግግሮት ፕሬስ ኮንፈረንሱን በብዥታ አጠናቆታል።

አዎ የተቀናጀዉ ማስተር ፕላን ይቅርታ የተቀናጀዉ ማስተር ጥፋት ማለቴ ነዉ ላይ ህዝቡን ማወያየት በመዘግየቱ በህዝቡ ዘንድ ብዥታን ፈጥሯል ሲሉ ተደምጠዋል። ኧረ እንደዉ ለመሆኑ ምን ያህል እንደዘገዩ ታውቆታል? የለም የለም በፍጹም አያቁትም ምክያቱም ይህ ጉዳይ ከአመት በፊት ተነስቶ የበርካታ ዉድ የኦሮሞ ልጆች ህይወት ከቀጠፈ በሗላ በአንድ የከተሞች ስብሰባ ላይ “አሁን ህዝቡ ተወያይቶበታል ይህን ማስተር ጥፋት ማንም አያቆመዉም ለማቆም የሚቃወምም ካለ ልክ እናስገባዋለን” የሚል የትምክህት ንግግር ተደምጡዋል። ማን እንደማይሉኝ እርግጠኛ ነኝ ምክያቱም የእርሶ የተንኮል አባት የሆኑት ፋሺስቱ አቶ አባይ ጸሃዬ ናቸዉና! አዎ በእርግጥም ግጥም አድርገዉ ያውቁታል። ታዲያ እንደ ፋሺስቱ አባባል ህዝቡ ተወያይቶ ከሆነ ከየት አምጥተዉ ነው እርሶ ማወያየቱ ዘግይትዋል ያሉት? ይህ ብዥታ አንድ ይባላል።

ወግ አይቀርምና አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝም ታዘዉም ቢሆን ዘግይተናል ብለዉ ሲናገሩ ተደምጠዋል። ትንሽ ዘግየት አላችሁና ደሞ ጭራሹኑ ማስተር ጥፋቱ በ 2006 ተዘግቷል አላችሁ, ይህን ደሞ ብዥታ ሁለት በሉልኝ።እረ እርሶ ምን ያልቅቦታል እንደገና ደሞ ያለእፍረት የማወያየቱ ስራ የዘገየው የማስተር ጥፋቱ ጉዳይ በጣም ረቂቅ ስለሆነ ነው አሉ, ይህን ደሞ ብዥታ ሶስት በሉልኝ። በጠቅላላዉ ለህዝብ የሰጣችሁት መግለጫ በግልጽ እርስ ብእርሱ የሚጋጭ አይደለምን?እዉነት ለመናገር መቼም ይሄ ጠፍቷችሁ አይደለም አናንተ በንጹሃን ደም የምትቀልዱና የፋሺስት ምግባር ያላችሁ ስብስቦች መሆናችሁን ያረጋግጣል።

ሌላዉ ደግሞ ለእዚህ ህዝባዊ አመጽ እጃቸዉ ያለበትን ስም ዝርዝር መጥቀስ አልፈልግም ብለዋል! አውነት ነው በጣም ያስፋራል ምክንያቱም የህዝብን ሕገመንግስታዊ መብት ረግጠዉ ሕዝብን ለአምጽ ያበቁትና ያባባሱት የሕውሀትና የኢሐድግ ቅጥረኞች በመሆናቸው ሕወሐትን ማሳጣት ይሆንቦታል። የሗላ ሗላ ግን ንጹ ዜጎችንና በሰላም የሚቁዋሙ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችን በማሰር ተጠመዳቹ እንግዲህ በነኚህ ግለሰቦች ዙሪያ የተሰራ ያልተዋጣለት ድራማ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በኩል ብቅ እንደሚል እርግጠኛ ነኝ።

ሌላው ደሞ ሳያስቡት በምርቃና አንድ እውነት ተናግረዋል ይኸዉም አሁን ጥቄው የማስተር ጥፋቱ አይደለም ተቀይሯል አሉ።እርግጥ ነው ጥያቄው ከማስተር ጥፋቱ ይቁም ወደ መንግስት ይቀየርልን ድብን አድርጎ ተቀይሯል። ምን ሆነ መሰለህ ተማሪዎች ማስተር ጥፋቱ የኦሮሞ ህዝብን ይጎዳል ብልው ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጡ እናንተ ደሞ አጋዚን አሰልፋቹ የኦሮሞ ተማሪን መግደል ጀመራችሁ ይሄኔ ተማሪው አትግደሉን ቤተሰብ ደሞ ልጆቻችንን አትግደሉ በማለት ጥያቄዉን አሳድገዉ በህብረት ገበሬዉን ጨምረው ሰልፍ ወጡ። እናንተ ምን ገዷችሁ 100% መረጠን ያላችሁትን የኦሮሞ ህዝብ በአደባባይ ረፈረፋችሁት ይሄኔ ታዲያ ህዝቡ በአንድ ድምጽ በዱርዬ መንግስ አንተዳደርም በቃን በማለት ጥያቄዉን ከማስተር ጥፋት ይቁም ወደ መንግስት ይቀየርልን አሳድጎታል።

አቶ አያልቅበት ረዳ ሌላው የሚገርመው ነገር ደሞ በተደጋጋሚ ከተለያዩ ሚዲያዎች ስንት ሰው ሞተ ለሚለው ጥያቄ የእርሶ መልስ የነበረው የቁጥር እንካ ሰላምታ ውስጥ አንግባ እሱ ትርጉም የለዉም በማለት ደጋግመው ተናግረዋ። እውነት ነው, 1 ኛ 10 ሰው ሞተ ወይም 10ሺ የሚሞተው ኦሮሞ እስከሆነ ለእርሶ በፍጹም ትርጉም የለውም, 2 ኛ ገዳዮቹ መጻፍና ማንበብ የማይችሉ የፌደራልና የአጋዚ ወታደሮች ቁጥርን ከ 5 በላይ መጥራ የማችሉ ስንት ገደላቹ ሲባሉ 5 እስከስንት ተማራቹ እስከ 5 እያኡ የሚመልሱትን እርሶም እንደብዥታ መፍጠሪያ ስንት ሰው ሞተ ሲባል 5 እያሉ ሲመልሱ ከቆዩ በሗላ የፈለግነውን ያህል ብንገል ማን ያገባዋል በማለት አሁን የቁጥር እንካ ሰላምታውስጥ መግባት አያስፈልግም ሲሉ መልሰዋል። ሌላኛው ሀቅ ደሞ ወያኔ ከጫካ ጀምሮ ሬሳ ለቅሞ የመደበቅ የካበተ ልምድ ስላላት የሟቾችን ቁጥር አሳምረው ያውቁታል ስለዚህ ባለዎት ዳታ መሰረት የሟቾችን ቁጥር በጊዜ እውነቱን ቢናገሩ ይሻላል እላለሁ አቶ ቀጣፊው ረዳ። ለምን ቀጣፊ እንዳልኮት በደንብ ያቃሉ ብዬ አስባለሁ ለነገሩ ሀቅ ተናግሮ የማያቅ ሰው ይሄ እንዴት ይጠፋዋል። የቅጥፈት ነገር ሲነሳ እስቲ አንድ የቀጠፉትን ነገር ላንሳ እንደው ማን ያምነኛል ብለው ነው አመጹን ያነሳዉን ሕዝብ መኪና እያስቆሙ በመኪና አምስት አምስት መቶ ብር ያስከፍሉ ነበር ብለው የወነጀሉት። የኦሮሞ ሕዝብ እኮ በናንተ የተቀመጡት አሻንጉሊቶች ከነፖሊሶቻቸው ሲሸሹ በምትካቸው የሀገ ሽማግሌዎች መርጠው ለአንድም ቀን ቢሆን ዴሞክራሲያዊ አስተዳደደር ምን እንደሚመስል በሚገባ ያሳያችሁ ሕዝብ ነው ። እውነት ነው እውነት ነው እናንተን ጨርቃችሁን ጥሎ ያሳበዳችሁ ነገር ቢኖር ወያኔ በግፍ ያካበተችው ሀብት ላይ ያንዣበበው አደጋ ነው ለምሳሌ በክፋታቸው ሰይጣን የሚቀናባቸው የናንተም ተንኮል አስተማሪ የሆኑት በአቶ መለስ ዜናዊ ስም በየቦታው ዘርፋችሁ የሰየማችሁት ፓርክ መቃጠሉ ነው። ይህ ደሞ የግፍ ንብረት ስለሆነ መላ ሕዝቡን እሰየው ያሰኘ ነው ። ይልቁኑ አቶ መለስ ዜናዊ በስማቸው የቆመ ፓርክ ነው የተቃጠለው ነገር ግን ይህ ግፍ ያስመረረው ህዝብ አንተን ቢያገኝህ ምንህን ሊያቃጥልህ እንደሚችል አንተው እራስህ ገምት።

በመጨረሻም በመደጋገም ጋንኤልን የጠራ የጠርራውን ጋንኤል ስለመቆጣጠሩ እርግጠኛ አይደለም። የተጠሩት አጋጋንት ከጠራቸው ጠንቁዋይ አቅም በላይ ስለሆኑ እያሉ ያለ እረፍት ለጋዘጠኞች ስለጋኔልና ስለ ጠንቁዋይ ባህሪ በእርግጠኝነት ሲናገሩ ምን ያህል ከጠንቁዋይና ከጋኔል ጋር አብሮ እየሰሩ እንዳለ ያሳያል። ይህ ደሞ የማትክዱት ሀቅ ነው ምክንያቱም ቦንብ ህጻናት ላይ መወርወር, እናት እባካቹ ልጄን አትግደሉብኝ ብላ እየለመነች እሷንም ልጇንም አንድላይ መግደል, አዛውንቶችን መግደል, እርጉዝን ገድሎ መጣል, እህቶችን አስገድዶ ደፍሮ መግደል ወዘተ የአጋንት ወይም የሰይጣን ባህሪ ነው። እንደሚታወቀው ይህን ድርጊት የፈጸሙት ደሞ ፌደራልና አጋዚ የተባሉት አጋንንቶች ናቸው። የነዚህ አጋንንት አሰልጣኝ ደሞ እርሶና እርሶን መሰል የሕወሐት ባለስልጣናት ናቸው። ስለዚህ የአብዬን ወደ እምዬ የሚለውን ተውትና በኦሮሞ ህዝብም ይሁን በመላው የኢትዮዽያ ህዝብ እርሶ የአጋጋንቶች ቁንጮ ነው የሚባሉት።

ማስተር ጥፋቱ ቆሟል የሚባለው የማደናገሪያ ሀሳባችሁ ላይ ደሞ ሰሞኑን እመለስበታለሁ!!!!!!

Letter of the Day: Seeking justice for the Oromo people of Ethiopia

 

Tullu Milki, Salale ( North Shawa) Jan 8, 2016
Hawi Fantaye(The Tampa Tribune) — I was born in Ethiopia and came here nine years ago. I am 19, and I go to Hillsborough Community College. I am writing because of the situations going on in Ethiopia.

I don’t know if you are aware, but the Ethiopian government is having a war with its own people. This war has been going on for over 25 years. The ongoing discrimination against the Oromo tribe has become too much to handle. Recently, the Ethiopian government set out a “Master Plan” — expanding the capital and building meaningless buildings that will only benefit the government. Their goal is said to be to develop the country.

Although this seems like a favorable act, there are many things happening behind the scenes due to this master plan. For one thing, farmers in neighboring cities of the capital will be stripped of their land, with no compensation. Ethiopia is known for having vast land for agriculture. Many people rely on farming to support their families. When the government takes the Oromo people’s land with little to no compensation, these people have nothing left. My family is a victim of this land grab.

Recently the government took my grandmother’s land, which was about half an acre. They said they needed to build a road. They gave my grandmother $50 for all the land she lost. My grandmother used to grow crops and sell them in the market to support her grandkids. Now she is struggling and reaching out for help.

These kinds of cases have been going on for years in Ethiopia. This is my ancestors’ land, and it is sad to see it all being taken away.

The Master Plan is just a fraudulent scheme to take the Oromo people’s land. If the government really wanted to develop the country, then it would have worked on other pressing matters. For example, the water system and electricity are horrible in Ethiopia, especially in the Oromo region. There are times when people don’t get water for a whole week. And there are times when electricity is shut down for days and days. Also, there is a huge drought going on in the Oromo region. Instead of working on these issues, the government decides to just ignore the public’s concerns. This shows that the so called Master Plan is not really taking into consideration the Oromo people and what they are losing.

Recently, many university and high school students went on a peaceful protest against the Master Plan. Many students were upset and wanted to show their frustration. With the democratic state that Ethiopia claims to be, peaceful protest should be allowed; after all, we all have the right to protest. Shockingly, the Ethiopian government did not like the protest so they sent out federal soldiers to kill and arrest protesters. There have been over 131 deaths and 3,500-plus arrests in just the past month. There were many people wounded due to the government throwing bombs at its people. When these innocent protesters tried to go to the hospitals, many were denied care and left there to die.

As an Oromo, I am deeply saddened with what is going on in Ethiopia. No government should ever do such cruel acts against its own people. This is not a democracy!

The Ethiopian government is controlled by the Tigray people, who account for only 15 percent of Ethiopia’s population. The Tigray region of Ethiopia is one of the most successful — industrialized — due to the government supporting its own tribe of people. The Oromo people account for more than 50 percent of Ethiopia’s population, yet they are the most discriminated against. They are seen as being inferior.

I would like to raise awareness about what is going on in Ethiopia. I want to get some justice for my people. They have been treated wrong for many years, and it is time for them to prevail and be free.

Addressing Post-TPLF Fears

By Dr. Ebissa Ragassa

There is great fear reverberating among Ethiopianist/Unionist that the sudden fall of TPLF will lead to Ethiopia’s disintegration. What Ethiopia may become after the fall of TPLF is a worrying scenario for many Ethiopianist however, in delaying to join Oromo’s peaceful uprising will not help the impending situation on the ground. Ethiopianist must see Oromo’s protest as people’s revolt against a regime that is bent on destroying the very foundation of our existence. Capitulation, hesitation on the part of Ethiopianist will only delay the removal of TPLF from power, in addition jeopardizing the hope of reviving Ethiopian unity post-TPLF.

Ethiopianist must stand in solidarity with their Oromo brothers and sisters who are waging a peaceful resistance in a face of a merciless enemy. Unless done so quickly when TPLF is scrambling to get a handle on the situation on the ground, Ethiopia’s fate will depend on what we do from this point on. Failure to take part in the uprising will undoubtedly raise a fundamental question whether Ethiopia is an idea worth preserving or is a facade. If Ethiopia’s unity is so fragile that the removal of TPLF will endanger our unity, then Ethiopia unity is in greater jeopardy than we imagine and we must quickly rethink the long-term strategies.

Already, the Oromo peaceful resistance has exposed TPLF’s vulnerabilities awaiting a joint effort to fully remove it from power. The uprising has damaged TPLF beyond repair, they can no longer continue to rule as they did before nor can they continue to rule by inciting ethnic fear, as such the primarily objective is to removal TPLF from power and make Ethiopia a common project. TPLF as an organization has de-evolved to the point of exclusively becoming an agent for foreign corporations by neglecting fundamental Ethiopia’s interest as evident by the lack of progress for past 25 years. The hope of transforming Ethiopia through TPLF is structurally and ideologically impossible. Given what is happening on the ground now, three possible outcomes could unfold post-TPLF.

The first scenario is that TPLF will fall and Ethiopia remains an intact country, this is not a remote possibility as will be discussed further. The second scenario would be Ethiopia will go through a referendum and each nation and nationalities will determine their own fate. The third scenario is that we do nothing, TPLF will continue to sell our lands to stay in power in the name of development and soon than later Ethiopia will become a failed state this a more likely, given the inherent ideology of TPLF.

Ethiopia has lost more than its gained under TPLF dictatorship. Eritrea had seceded fundamentally altering Ethiopia’s territorial integrity with TPLF spearheading the effort. Ethiopia had lost its port, a vital access to the sea that was purposely designed to cripple Ethiopian economically for years to come. TPLF had fundamentally lost internal legitimacy, thereby its continued existence is predicated on foreign military support and financial aid. Finally, Ethiopia is on the verge of becoming a failed state joining her neighbor Somalia where TPLF is acting as mercenary for western interest increasing regional instabilities. in any scenarios, TPLF is no longer a viable option.

There is no doubt that TPLF will fall, it is a matter of time, the eventuality of this should not be taken lightly, as such we must begin to think what kind of Ethiopia we wish to live in. There is more evidence and consensus among people as well as political leaders that Ethiopia will emerge stronger post-TPLF, provided Ethiopianist see Oromo’s peaceful protest as an opportunity rather than a threat. Failing to join the peaceful uprising by the unionist would undoubtedly lead to a catastrophic, a strategic mistake that will both derail the possibility of forming unified country and exacerbate the fragile nature of Ethiopia.

Skeptics may question this possibility of unified Ethiopia post-TPLF given our history and different political ideologies. It is indeed true history has not been kind to us, in fact, it has hindered the development of progressive state and allowed an opportunistic organization to emerge and dictated the term of Ethiopia without taking into account the history of all our people. Ethiopia’s definition changes based on who is in power, what it means to be Ethiopian under Haile Selassie is totally different than under TPLF, as well as Ethiopia’s history interpretations changes based on who is power. What it means to be Ethiopian post-TPLF will change as well, however, unlike the past where a narrow definition of Ethiopia is imposed on others, post-TPLF, the totality of our people’s experience, history, and contribution will be recognized.

Ethiopianist fear what Ethiopia may become, even fear whether it will even exist post-TPLF, knowing each regime that has taken power has manipulated Ethiopian history by championing narrow Ethiopia narrative to appease their power base to extend their rule. This has not only created conflict among peace loving people even after the demise of each regime but also created fertile ground for a dictatorship to reign thereafter. That is why many Ethiopian movements even with best of intentions had failed to transform themselves into ruling democratically once in power. The current Oromo revolt is not only about removing TPLF from power, but to end the rule of dictatorship, which would be a turning point in Ethiopian history.

As such the current Oromo revolt must be seen as a transformative process, that will lay a fertile ground for democracy. The participation of Ethiopianist in the current revolt is not only required to remove TPLF but also is a necessary step in post-TPLF democratic processes. If the unionists join in the struggle without delay, unity has already begun on a victorious ground in which all people had contributed to removing TPLF from power, alleviating the fear of returning to dictatorship post-TPLF. As such, a new beginning would in ensue, in which the people themselves take credit for removing TPLF from power laying seeds for representative democracy. Hence, a unified action will change Ethiopia’s trajectory, from which armed group had always claimed victory, in turn, subjected our people. Removal of TPLF through popular uprising will not only end tyrannical rule over our people but will change our people’s psyche, perception, that will undoubtedly deter undemocratic rule for generations to come, at the same time deploying a well-equipped citizens that develops itself through its own means and decide its own fate. A unionist joining peaceful struggle would only lead to a win-win situation despite the uncertainty of post-TPLF.

Many Ethiopianist indecisiveness to join the Oromo uprising claiming ethnic connotation and is in direct opposition to Ethiopianism would yield undesired results. While the current Oromo uprising was initiated in Oromia, at its core, it is a question of citizenship that all Ethiopian people have been yearning for. If the unionists make a joint effort in removing TPLF, the question of citizenship will be an integral part of our future. The new Ethiopia should be based on a constitution, sets of bills of rights that guarantees our citizens peace and prosperity. Basing Ethiopian unity solely on history and common bond will have disastrous consequences not only for current struggle but for the future. As such, unionist must accept and be ready to participate in the formation of new Ethiopia that is based on higher ideas that will continue to evolve with the needs of our citizens.

Another reason the unionist are hesitant to join the struggle is the demographic power of Oromo people threatens Ethiopian unity if TPLF is suddenly removed without placing some kind of political safeguard to protect against Ethiopian disintegration. The political safeguard Ethiopianist seek would have to be a bold, courageous act in themselves that will convey to other nation and nationality that Ethiopia unity extends far beyond one language, one flag, one history, as such Oromos being a the majority will make separation a difficult case to make. As a majority, even if it’s politically feasible, practically a very difficult task to ascertain secession. Therefore, it would be easier for Oromo people to rearrange Ethiopia in the way that brings peace and prosperity to all groups in the country than seek secession. However, if TPLF remains in power, the possibility of civil war are evident as internal colonization are already taking place. The expropriation of Ethiopian people’s resource, the rearrangement of internal boundaries without consent and the of selling fertile land to foreign companies will exacerbate people’s patients, as a matter of survival secession would be become the only option.

The Oromo peaceful movement has cracked and exposed TPLF’s vulnerabilities. To deal a final blow to this military dictatorship, we all need to stand in defiance against the regime. Our failure to do so will embolden TPLF further jeopardizing our people very existence. Is the fear of post-TPLF worse than living under TPLF rule? A new Ethiopia, without TPLF, is a risk worth taking.

የገዢው መንግስት በባህር ዳር ከተማ ያደረጋቸው የምረጡኝ ስብሰባዎች ውጤት አልባ መሆናቸው ተነገረ

 

በባህር ዳር ከተማ በሁሉም ክፍለ ከተማዎችና ሙሉዓለም አዳራሽ የተደረገው ስብሰባ የተፈለገውን ግብ ሳይመታ መጠናቀቁን የስብሰባው ተሳታፊዎች ተናገሩ፡፡

ቅዳሜ መጋቢት 26/2007 ዓ.ም በተደረገው ስብሰባ የብአዴን አባላትን በጥሪ ወረቀት የከተማ ነዋሪዎችን ቤት ለቤት በመዞር በስብሰባው እንዲገኙ በመመዝገብና የተለመደውን ማስፈራሪያ በመጠቀም እስከ ቀኑ 6 ሰዓት በተደረገው ስብሰባ ተሳታፊዎች የተለያዩ

ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን በመስጠት የገዢውን መንግስት ካድሬዎች ሲያሸማቅቁ መዋላቸውን ተሳታፊዎች ለዘጋቢያችን ገልጸዋል፡፡

ያለፈውን አምስት ዓመት “ የህዝቡ ችግር ምንድን ነው? ” በማለት ሰብስባችሁ ሳታነጋግሩን ዛሬ የምርጫ ወቅት ሲደርስ በመሰብሰብ መልካም ሰርተናል ለምን ትላላችሁ?

ከምርጫ ቀን በኋላ የምትገቡትን ቃል ሁሉ በመርሳት ከጥቃቅን አገልግሎቶች ጀምሮ ህዝቡን በመልካም አስተዳደር እጦት ማሰቃየት እንደ ልማድ አድርጋችሁ የምትሰሩበት አካሄድ ሆኖ እያለ፤ ዛሬ ለምርጫ ሲባል ራሳችሁን እንደ ቅዱስ አድርጋችሁ ለምን ታቀርባላችሁ?

የገዢው መንግስት ስራውን በአግባቡ አለመስራቱን በተለያየ የአፈጻጸም ስራዎች ታይቷል፡፡ ህዝቡ በኑሮ ውድነት እየተሰቃየ ባለበት ወቅት በዘይትና ስኳር ሰበብ ህዝቡን ከአንድ አመት በላይ ለሌላ ሰቆቃ ዳርጋችኋል፡፡ይህም አመራራችሁ ከዘመኑ ፍጥነት ጋር ለመጓዝ

እንዳልቻለ ያስረዳልና አመራሩን ከታች ጀምሮ በተማሩ ሰዎች እንዲያዝ ለምን አታደርጉም?

ከክፍለ ከተማው ዝቅተኛ ሰራተኛ ጀምሮ እስከ ከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ባለሙያዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በሙስና እየተዘፈቁ የራሳቸውን ሃብት ሲያከማቹና በህዝቡ ላይ ልዩ ልዩ ተጽእኖ ሲያደርሱ ይህን በመከላከል ህብረተሰቡን ፍትሃዊ አገልግሎት እንዲያገኝ

ከማድረግ ይልቅ ዝምታን የመረጣችሁበት ጊዜ ነው፡፡ዛሬ ሙስና እንደ ህጋዊ አሰራር ተቆጥሮ ማንኛውም አሰራር ያለ እጅ መንሻ የማይፈጸምበት ጊዜ ላይ ቆማችሁ መልካም ሰራን ማለቱ ዋጋ ያሰጠዋል ወይ?

አገራችን አደገች ስትሉ በየጊዜው እንሰማለን፡፡የጥራታቸውን ጉዳይ ሳናነሳ በመንግስትና ህብረተሰቡ መዋጮ የተሰሩ የኮብልስቶን መንገዶች አሉ፡፡ሀገር አቋራጭ መንገዶችም ደረጃቸው አድጎ ተመልክተናል፡፡ በሌላ መልኩ ማንነታቸው የማይታወቁ ሰዎች ምንጩ

ባልታወቀ ሁኔታ ከመሬት ተነስተው ህንጻ ሲገነቡ እናያለን፡፡በእያንዳንዱ ቤተሰብ ኑሮ ላይ የሚታይ ለውጥ ሳይኖር አድገናል የሚለው መግለጫ ምን ማለት ነው?እድገት ሁሉን ያማከለ ነው ትላላችሁ ታዲያ እድገቱ የታለ? እኛ ሲያድጉ፣መኪና ሲቀያይሩ፣

ቤተሰባቸውን ሲያቀማጥሉና በየቦታው ህንጻ ሲገነቡ የምናያቸው በጣት የሚቆጠሩ ግለሰቦችን ብቻ ነው፡፡ሁሉን ያማከለ ዕድገት ሳይኖር አድገናል ማለቱ ህዝቡን ማታለል አይሆንባችሁም?

በከተማም ሆነ በገጠር ያለው መሬት በተወሰኑ ግለሰቦች፣ አመራሮችና ቤተሰቦቻቸው ከመያዙ ባሻገር ከዓመት ዓመት እየባሰ መሄዱ የመልካም አስተዳደርና የፍትህ እጦት ሆኗል፡፡ወጣቶች መሬት በማጣት ወደ ከተማ መፍለሳቸውና ወደ አረብ ሃገራት

መሰደዳቸው ችግር ሆኖ ቢቀጥልም የተሰጠ መፍትሄ የለም፡፡መሬት በጥቂት ሃብታሞችና ለመንግስት ታማኝ በሆኑ ግለሰቦች እጅ መሆኑ አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል በቤት ክራይ እንዲሰቃይ አድርጎት ይታያል፡፡ታዲያ ፍትሃዊነትን አስፍነናል ለማለት

የሚያስደፍር ስራ አላችሁ ወይ? የሚሉና የመሳሰሉ በገዢው መንግስት የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በድፍረት ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡

የገዢው መንግሰት ካድሬዎች በቅስቀሳው መልካም ውጤት እንገኛለን በማለት ከተለያየ መስሪያ ቤቶች የሰበሰቧቸው የመንግሰት ሰራተኞችን በሙሉዓለም አዳራሽ ፤ በክፍለ ከተሞች ለተሰበሰበው ህዝብ ለስላሳ፣ቆሎ፣ውሃናዳቦ በማቅረብ ቡና በማፍላት የ24

ዓመቱን የኢህአዴግ ጉዞ ያስገኘውን ለውጥ በማጋነን ቢያወሩም በታሰበው መልኩ የህብረተሰቡን አስተሳሰብ የሚቀይር ውጤት እንዳልተገኘ በስፍራው የታደሙ ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡

Sorce satenaw.com/amharic

POSETD BY ZENEBU GEBRU

 

በየመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ የደረሰው ጥቃት እየተጣራ ነው

በየመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ  ላይ የደረሰው ጥቃት እየተጣራ ነው

30 ኢትዮጵያውያን ከየመን ጅቡቲ ገብተዋል
በየመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ የተፈፀመው ጥቃት  በማን እንደተፈፀመ እየተጣራ እንደሆነና  ከየመን ወደ አገራቸው ለመመለስ በኤምባሲው በኩል ከተመዘገቡ ኢትዮጵያውያን ውስጥ 30 ዜጎች  ጅቡቲ መድረሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ተወልደ ሙሉጌታ ለአዲስ አድማስ ገለፁ፡፡ በየመን መዲና ሰንአ የሚገኘው  የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ ጥቃቱ በማን እንደተፈፀመ እየተጣራ እንደሆነ የገለፁት አቶ ተወልደ፤ በተፈፀመው ጥቃት በኤምባሲው ሰራተኞች ላይ ምንም የደረሰ  ጉዳት የለም ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በየመን የሚገኙ ዜጎች ተመዝግበው ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ባደረገው ጥሪ መሰረት፤ ከተመዘገቡት ውስጥ 12 ሴቶች፣ 11 ህፃናት እና 7 ወንዶች የተካተቱበት አንድ ቡድን ጅቡቲ መድረሱን ቃል አቀባዩ ጠቁመዋል፡፡
የመን ውስጥ በስደተኞች መጠለያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሳኡዲ የአየር ጥቃት ተደብድበው ህይወታቸው አልፏል በሚል የተሰራጩ ዘገባዎችን በተመለከተ አቶ ሙሉጌታ በሰጡት ምላሽ፤ “በኛ በኩል ባደረግነው ማጣራት በዚህ ሁኔታ የሞተ ሰው የለም” ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል፤ የየመኑ የሁቲ አማፂ ቡድን ከኢራን የሚያገኘውን የወታደራዊ ቁሳቁስ ድጋፍ በቀይ ባህር በኩል በማሻገርና ለአማፂያኑ የወታደራዊ ስልጠና ቦታዎችን በአገሯ ላይ በማመቻቸት በተደጋጋሚ ስሟ የሚነሳው ኤርትራ፤ ሰሞኑን ተመሳሳይ ውንጀላ በሳኡዲ የመገናኛ ብዙሀን ተደርጎብኛል በሚል በሰጠችው ምላሽ፤ ውንጀላው መሰረተቢስ እንደሆነ ገልፆ የወሬው ምንጭም የአፍሪካ ቀንድ አገራት ናቸው ስትል አጣጥላለች፡፡
አብዛኛውን የየመን ክፍሎች በመቆጣጠር የአገሪቱን መሪ ከስልጣን ያስወገደው የሁቲ አማፂያን ቡድን፤ ከኢራን ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚደረግለት የሚነገር ሲሆን የሚያገኘውንም ድጋፍ በማስተላለፍና ለወታደራዊ ስልጠና ቦታ በመስጠት ኤርትራ በተደጋጋሚ ስሟ እንደሚነሳ አገር እንደሆነች ይታወቃል፡፡ የመካከለኛው ምስራቅ የሚዲያ የምርምር ተቋም ከጥቂት አመታት በፊት “ኢራን በቀይ ባህር የእንቅስቃሴ አድማሷን እያሰፋች ነው” በሚል ርዕስ  ባወጣው መረጃ፤  ኢራን ለሁቲዎች የምታደርገው የወታደራዊ ቁሳቁሶች ድጋፍ በኤርትራ በኩል እንደሚያልፍ ጠቁሞ ኢራን ሁቲዎችን የምታሰለጥንበት ካምፕ ኤርትራ ውስጥ ከየጊንዳዕ ከተማ በስተምስራቅ ደንጎሎ የሚባል ቦታ እንደሚገኝ አስታውቆ ነበር፡፡ ሰሞኑን የሳኡዲ የመገናኛ ብዙሀን፤ ሁቲዎች ከኢራን ለሚያገኙት ድጋፍ ኤርትራ ትብብር ታደርጋለች ሲሉ ዘግበዋል፡፡
“ዘገባው ከሙያዊ ስነምግባር ያፈነገጠ ነው” በማለት ባለአስር ነጥብ መግለጫ ያወጣው የኤርትራ መንግስት፤ ዜናውን መሰረተ ቢስ ሲል ያጣጣለ ሲሆን የመረጃው ምንጮችም የአፍሪካ ቀንድ አገራት እንደሆኑ ገልጿል፡፡ “ሻባይት” የተባለው የኤርትራ መንግስት ድረገፅ በበኩሉ፤ የዚህ መረጃ ምንጮች አንዳንድ የስለላ ተቋማትና የኢትዮጵያው ህወሓት ነው ብሏል፡፡
የኤርትራ መንግስት ባወጣው ባለአስር ነጥብ አቋም ውስጥ፤ የየመን ጉዳይ የራሷ የውስጥ ጉዳይ ስለሆነ የትኛውንም የውጭ ሀይል በመደገፍ ኤርትራ እንደማትሰለፍ አስታውቋል፡፡
የሳኡዲ መንግሥት በበኩሉ፤ የሁቲ አማፅያን እንቅስቃሴ ለአገሬ ስጋት ናቸው በሚል  በየመን ወታደራዊ ድብደባ እየፈፀመ እንደምገኝ የሚታወቅ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስትም የሳኡዲን አቋም እንደሚደግፍ አስታውቋል፡፡

Radio Afuura Biyyaa: Interview with Ob. Leenco Lata of ODF (March 28, 2015)

sorce Gadaa.com

Oromo Activists in Norway Demonstrate Against the TPLF Ethiopian Regime’s Human Rights Violations Against Oromos (Bergen, March 21, 2015)

The Crumbling Palace of Abbaa Jifaar; Oromia’s Historic Heritage Under Attack: the TPLF-led Ethiopian Govt Stalling Plan to Restore the Abbaa Jifaar Palace

These days, TPLF is busy trying to deceive the public that its satellite organization in Oromia has been a caretaker of Oromo’s historic, cultural and environmental heritages in Oromia. The truth is TPLF has been the #1 enemy of Oromia’s historic, cultural and environmental heritages over the last few decades: more damages have been launched on Oromo’s heritages in the last twenty years than ever before – such as, the crumbling palace of Abbaa Jifaar; the banning of the Oromo indigenous religion – Waaqeffannaa; the burning forests of Chilalo, Bale, Cuqqaalaa and others; the banning of Oromo horse-riding competitions (Oromo equestrian races); the banning of the Macha-Tulama Association; the banning of the Irreecha at Mount Cuqqaalaa; the banning and elimination of Oromo music stores — these are just some of the overt and covert attacks on Oromo heritages over the last twenty years under the TPLF regime. TPLF is the #1 enemy of Oromia’s historic, cultural and environmental heritages, not the caretaker as it’s trying to vuvuzela today for the election.

sorce Gadaa.com

posted by zenebu gebru

ቦሩ በራቃ:- ከኣቶ ያሬድ ጥበቡ ኦሮምያን ለሁለት የመግመስ ነፍጠኛዊ ‘ጥበብ’ በስተጀርባ

በቦሩ በራቃ*

ስማቸው የተጠቀሰው ኣዛውንት ደርግን ለመጣል በተደረገው ትግል ውስጥ በወጣትነታቸው የተካፈሉ ናቸው። ሁዋላ ላይ ግን ከተሰለፉበት ሃይል ተለይተው፣ ጉዋዶቻቸው ቱባ ቱባ ባለስልጣናት ሲሆኑ እርሳቸው ስደት ላይ መሆናቸውን የግል ድረ-ገጻቸው ላይ ይነግሩናል። ኣቶ ያሬድ ጥበቡን ለማስተዋወቅ ጊዜዪን የማባከን ግዴታ የለብኝም። ባጭሩ ግለሰቡ ቀደም ሲል ወያኔ ዛሬ ደግሞ ኣደገኛ ኒዮ(Neo)-ነፍጠኛ መሆናቸውን በየመጣጥፎቻቸው ሁሉ የሚያንፀባርቁት ኣስተሳሰባቸው እየነገረን ነው። የሚገርመው ደግሞ ኣልፎ ኣልፎ የኦሮሞ ፖለቲከኞችን ሲያገኙ እኔኮ እገሌ የሚባለው የኦሮሞ ዘር ነኝ እያሉ ማወናበድም ይታይባቸዋል። ለነገሩ በዛሬው ዘመን የምናያቸው የነፍጠኛው ስርእት ኣቀንቃኞች ወጣት ኣዛውንት ሳይለይ ኣንድ የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር ይሄው የተነቃበት ስልታቸው ነው። ኦሮሞን ለማታለል ሲከጅሉ ‘እኔምኮ በኣባቴ ወይም በእናቴ ኦሮሞ ነኝ’ ኣይነት ኣሰልቺ ፈሊጥ ተያይዘዋል።

ዛሬ ትኩረቴን የሳበው ኣቶ ያሬድ ጥበቡ ሰሞኑን ‘ምን ይሻላል?’ በሚል መጠይቃዊ ርእስ የፃፉት ጉዳይ ነው። በዚህ ፅሁፋቸው የራሳቸውን ብቻ ሳይሆን በመሰሎቻቸው ዘንድ ውስጥ ለውስጥ ሲብላላ የኖረን ውጥን ገሃድ ስላወጡት ምላሽ የሚያሻው ጉዳይ ሆኖ ኣገኘሁት። እናም ይህ ፅሁፍ ያነጣጠረው በዋነኝነት ለኣቶ ያሬድ ጥበቡ ስብእና ክሬዲት ለመስጠት ሳይሆን እንደ እሳቸው ሁሉ ከኣንድ ኣይነት የትምክህት ፋብሪካ ተፈብርከው ኦሮሞነትና ኦሮምያን ለማጥፋት ደቦ ለሚጠራሩት ሁሉ ምላሽ እንዲሆን ነው።

እነ እቶ ያሬድን በጣም ኣስጨንቆኣቸውና ኣስጠብቦኣቸው ‘ምን ይሻላል?’ ያስባላቸው ኦሮምያ በፍንፍኔ ላይ ያላት የባለቤትነት መብት ጉዳይ ነው። ወያኔ ካልተገበርኩት ብሎ የፎከረውን “የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን” በተመለከተ ነው የነኣቶ ያሬድ ጭንቀት። ታዲያ ግለሰቡ ‘ምን ይሻላል?’ ብለው ፅሁፋቸውን መጀመራቸውን ብቻ ያየ የዋህ ሰው ምናልባት እኒህ ሽማግሌ የኦሮሞ ህዝብ በማስተር ፕላኑ ሳቢያ ከቀዬው ላይ የመፈናቀሉ ጉዳይ ኣሳስቦኣቸው የኣረጋዊነት ኣስታራቂ ኣስተዋፅኦ ለማበርከት ኣስበው ይሆን ብሎ መጠየቁ ኣይቀርም። ነገሩ ግን ወዲህ ነው። የነፍጠኛውን ተጠባቢ ያሬድ ጥበቡን ያስጠበባቸው እንዴት ኦሮሞ በሸገር ላይ የይገባኛል ጥያቄ ያነሳል የሚለው እንጂ የኦሮሞ በገዛ ኣገሩ ላይ መበደልና መገፋት ኣይደለም። ታዲያ ኣሃዱ ብለው ፅሁፋቸውን የጀመሩትም እንዲህ በማለት ነበር።

“የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች በብዙ ጉዳዮች የሚለያዩ ቢሆንም፣ ፊንፊኔ መናገሻችን ናት በሚለው ጉዳይ ግን ይስማማሉ። ለዚህም ይመስላል በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጉዳይ፣ ኦሮሞ ፈርስትና ኦፒዲኦ እጅና ጓንት ሆነው ሃገሩን ያተራመሱት። ለመሆኑ ፊንፊኔ የኦሮሞ መናገሻ ነበረች? ኦሮሞዎች ከየት መጡ?”

በዚህ ኣባባላቸው ሁለት ድንጋዮችን ኣንስተው ኦሮሞ ላይ ወርዉረዋል፣ ግለሰቡ። ኣንደኛው፣ የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች ልዩነቶች እያሏቸው ነገር ግን ኣንድ የሚያደርጋቸው ጉዳይ መገኘቱ ኣቶ ያሬድን በጽኑ እንዳበገናቸው ከዚህ ኣባባላቸው እንረዳለን። ሌላው ደግሞ ግለሰቡን ክፉኛ የወገራቸው የነፍጠኝነት ጠኔ ኦሮሞ ኣገሩ እዚህ ኣይደለም የሚለው የበሰበሰና የበከተ የኣባቶቻቸው ተረት ተረት ነው። ለዚህም ነው ‘ለመሆኑ ፊንፊኔ የኦሮሞ መናገሻ ነበረች? ኦሮሞዎችስ ከየት መጡ?’ እያሉ ቆርፋዳ ጥያቄ የሚያነሱት።

ኣቶ ያሬድ የኣባቶቻቸውን ስልት በመከተል ኦሮሞን በኦሮሞ ለመምታትም ሞክረዋል። መርዛቸውን ለመትፋት ዋቢ መጥራት የፈለጉት የፊውዳል-ነፍጠኛ ስርዓትን ሲያገለግሉ የኖሩት የይልማ ዸሬሳን ቅዠታዊ ድርሰት ነው። ስለ ኣቶ ይልማ ዸሬሳ ማንነት ለጊዜው ኣሁን ማንሳት ኣልፈልግም። ኣቶ ያሬድ ይቀጥላሉ። ዋነኛ መከራከሪያቸውም ኦሮሞ ኣገሩ ኣሁን ካለበት መሬት ላይ ኣይደለምና የፍንፍኔን የባለቤትነት መብት እርግፍ ኣድርጎ መተው ኣለበት ነው። እኛ እዚህ ኣካባቢ ላይ የ3000 ኣመት ታሪክ ሲኖረን እናንተ ኦሮሞዎች ግን 500 ኣመት ኣልደፈናችሁም ሊሉን ዳድተዋል። እዚህ ጋር ሳቄ መጣ። የ3000 ኣመቱን የጥንታዊት ኩሽ-ላንድን (ኦሮሞና ኑቢያን ያካተተ) ስልጣኔ ሴማዊያኑ ሃበሾች ትላንት ከደቡብ ኣረቢያ ፈልሰው መጥተው በመንጠቅ የታሪኩ ባለቤት የሆነውን የኩሽ ታላቁ ግንድ ኦሮሞን ኣገርህ እዚህ ኣይደለም ሲሉት መሳቅ ነው ኣንጂ የምን መገረም! በመጽሃፍ ቅዱስ ሁሉ ሳይቀር በእብራይስጥ ቁዋንቁዋ ‘Cush shall soon stretch her hands unto God’ የተባለውን ይሉኝታ-ቢሶቹ ሃበሾች ጠምዝዘውት ባለታሪኮቹን ኩሾች ወደ ጎን በመተው ራሳቸውን የስልጣኔ ማማ ላይ ማስቀመጣቸውና ‘እኛኮ ስማችን መጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ ሳይቀር የተጠቀሰ ክቡር ዘሮች’ ነን ሲሉ ነው የሚያስቀኝ። ታላቁ ኣባታችን የሚሉት ዳግማዊ ምኒልክ ‘እኔ ኣፍሪቃዊ ወይም ከጥቁር ነገድ ኣይደለሁም’ በማለት እሱና ዘር-ማንዘሩ ለከተሙበት ሸገርም ሆነ ኣገር እንግዳ መሆናቸውን በራሱ ኣንደበት ሲመሰክር ኣልሰሙም ወይም ኣላነበቡም ይሆናል ጠቢብ ነኝ ባዩ የኣቶ ጥበቡ ልጅ።

Gadaa.com

posted zenebu gebru

 

በአምባገነኖች ዛቻ እና ማስፈራሪያ የመብት ጥያቄ እና የነፃነት ትግል አይቆምም!

በከልለው ኡርጋ*

EnoughWithTPLF20152

በምስራቅ አፍሪካ በመብት ጥሰት አቻ ያልተገኝላት፣ አምባገነኖች በንፁሀን ሕዝቦች ላይ ያሻቸውን አፈና፣ እንግልት፣ ግድያ፣ እስር፣ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያገዘፉ እና እያበራከቱ የመጡባት ብቸኛዋ ሀገር – ኢትዮጵያ ናት። ሲፈልጉ ወገኖቻችንን በተናጠል ያፍናሉ፣ ያስራሉ፣ ይገድላሉ። በሌላም ጊዜም፣ በጅምላ ይጨፈጭፋሉ። ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ስልጣኑን በበላይነት ይዘው እና ተቆጣጥረው፣ የፈለጉትን እና ያሻቸውን ያደርጋሉ። የሀገራችንን ሀብት ከመሟጥሟጣቸውም በላይ፣ ትልቁ ንቀታቸው፣ የተወሰኑትን የስርዕቱ አቀንቃኞች ለመጥቀም፣ በሚሊዮን የሚቆጠረውን ጭቁኑን የኦሮሞ አርሶ-አደር ሕዝብ ከቀዬው ለማፈናቀል እና ማንነቱን ለማጥፋት በማቀድ እና በማሴር ከግብ ሊይደርሱ ማሰባቸው ነው።

ሕዝብን ይዘልፋሉ፣ ያስራሉ፣ ይገርፋሉ፣ ይገድላሉ – አምባገነኖቹ!

በአንድ ወቅት፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ስርዓቱ በፈጠረው ምክንያት ስራ-አጥ ወጣቱን “አደገኛ ቦዘኔ” በማለት በመሳደባቸው፣ ውጤቱ ምን እንደነበረ በ97ቱ የምርጫ ወቅት በሚገባ አምባገነኖቹ አይተውታል። ዛሬ ደግሞ፣ የአምባገነኖቹ ቁንጮ የህወሓት ሥራ አስፈፃሚ ኮሜቴ አባል እና የሀገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስትር አማካሪ አቶ አባይ ፀሐዬ “ልክ እናስገባቸዋለን!” የሚለው ዛቻ ምን ሊያስከትል እንደሚችል ሳይገነዘቡት ቀርተው አይመስለኝም። አቶ አባይ ፀሐዬ ከ40 ሚሊያን በላይ ከሚገመተውን ከኦሮሞ ሕዝብ፣ ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር ተያየዞ የተናገሩት ንቀት ያዘለ ዛቻቸው የመጀመሪያው ገፈት ቀማሽ አምባገነኖች እንደሆኑ ሳይውል ሳያድር የሚያዩት ጉዳይ ይሆናል። በኦሮሞ ሕዝብ ማንነት እና ህልውና ጉዳይ ላይ ለተሰነዘረው እና ለተቃጣው ዛቻ እና ማስፈራሪያ፣ ምላሹ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም። ዛሬ በአምባገነኖች ዛቻ እና ማስፈራራት የሚበረከክ ትውልድ ሳይሆን፣ ጨቋኞቻችንን የሚያንቀጠቅጥና ለሕዝብ ትልቅ ለውጥ የሚያመጣ ታላላቅ ጀግኞች እና ብዙ “ሞት አይፈሬ” ወጣት ትውልድ የተፈጠረበት ዘመን ነው።

በተለያየ ጊዜም፣ ይህ የታየበት ሁኔታ አለ። የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ጨምሮ ሰላማዊ በሆነ መንገድ በመቃወም፣ ወጣቱ ቁርጠኝነቱን እና ጀግንነቱን አሳይቷል። ምንም እንኳን አምባገነኖች በግፍ ላይ ግፍ በወንጀል ላይ ወንጀል መደራረብ የለመዱ ቢሆንም፣ የተጨቆነው ሕዝብ የግፍ አገዛዝ ‘አይበቃም ወይ’ እያለ ያለበት ዘመን ነው። በማንነት እና በህልውና ላይ ለተቃጣው ዛቻ እና ማስፈራሪያ ለአምባገነኖቹ ማፈሪያ እና ውድቀት እንጂ ለተበደለ፣ ለተከፋ፣ ለተጨቆነ፣ ለታፈነ እና ለተበዘበዘ ደግሞ የበለጠ ለነፃነቱ ትግል የሚያነሳሳ ነው። ትውልዱ ያደረገው እና እያደረገው ያለው ተጋድሎ፣ የከፈለው እና እየከፈለ ያለውን መስዋትነት ለመገመት አስቸጋሪ አይደለም። አሁንም የተቃጣብንን የማንነት-ማጥፋት ዘመቻ ለመመከት ከምን-ጊዜም በጠነከረ መልኩ በተመሳሳይ የአምባገነኖቹ ግፍ እየደረሰበት ካሉ ሌሎች ሕዝቦች ጋር በጋራ በመሆን ለትግሉ ቁርጠኝነት ያሳየበት ወቅት ነው።

በዚያች ሀገር ለመኖር የግድ የገዝው ፓርቲ አባል ወይም ደጋፊ መሆን ያስፈልጋል፤ ያልሆነ ግን በጥርጣሬ ይታያል። የአገር ሀብት አትመንዝሩ፣ መልካም አስተዳደር ይምጣ፣ የዲሞክራሲ እና የሰብዓዊ መብቶች ይከበሩ፣ ለህግ ተገዢ ሁኑ ብሎ የገዥውን ፓርቲ በግልፅ የሚናገር ወይም የሚመክር ግለሰብም ሆነ ድርጅት ደግሞ ፀረ-ሰላም፣ ፀረ-ልማት፣ ፀረ-ሕዝብ፣ ፀረ-ዲሞክራሲ የሚል ታፔላ ይለጥፉለታል። በዚህም አያበቁም አፍነው ይገድላሉ ወይም በሐሰት ክስ ወደ ከርቸሌ ወይም ወደ ዘብጥያ ያወርዳሉ።

በዚያች ሀገር ሰላምን እና ነፃነትን ለማምጣት እና ለመኖር የኦሮሞ ሕዝብ ከሌሎች ከተጨቆኑ እና በተመሳሳይ ያአምባገንኖች የግፍ አገዛዝ ያንገሸገሻቸው ብሔር፣ ብሔረሰብ እና ሕዝብ ከጎኑ አሰልፎ እና ተባብሮ አንድ ወጥ ትግል ታግሎ በመጀመሪያ ጨቆኙን እና አምባገነኑን ወያኔ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ማስወገድ ነው። አምባገነኑ የወያኔ መንግስት ከተወገደ በኋላ ለሁሉም፣ የምትስማማ ሰብዓዊ፣ ዲሞክራሲያዊ እና የሕግ የበላይነት የሚከበርበት ምቹ ሀገር መፍጠር ያስፈልጋል። ይህ የሚሆነው ልክ እንደ ኦሮሞ ሕዝብ የግፍ አገዛዝ ያንገሸገሻቸው ብሔር፣ ብሔረሰብ እና ሕዝቦች ከኦሮሞ ሕዝብ ጎን በመቆም መታገል ሲችሉ ብቻ ነው።

ድል ለኦሮሞ ሕዝብ!

* ከልለው ኡርጋ:- kiyu297@gmail.com

Source- Gadaa.com

Posted By- Zenebu Gebreu