Category Archives: TPLF news

ሰበር መረጃ – የአባይ ግድብ እና የቦንድ ገንዘብ ዘረፋ (ወያኔ)

dam-467

(Satenaw) — የአል ጀዚራ ባልደረባ የሆነዉ ሃሰን ሁሴን  (Hassen Hussein) እንደዘገበዉ ጃንዋሪ 8 ላይ ግብጽ የአባይ ግድብ ግንባታ እንዲቋረት ጠይቃለች ይህዉም በሁለቱ ሐገራት መካከል ዉስጥ ለዉስጥ እየተካረረ የመጣ ዲፕሎማሲያዊ ጸብ ወደ ተለያየ አቅጣጫ እንደሚሄድ ሲነገር ቆይቶ ሰንብቶ ነበር። በ2017 ይጠናቀቃል የተባለዉ የአባይ ግድብ የተለያየ ችጎች ሲገጥሙት ቆይተዉ በስተመጨሻ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ከግብጽ ጋር ሚያደርጉት አለመግባባት ከተካረረ ግብጽ በኤርትራ የሚገኙ ተቃዋሚዎችን በማስታጠቅ ትጎዳናለች ወደሚል ስጋት ስለጣላቸዉ ብቻ   የካዮዉን መንግስት (Cairo’s collaboration)  ለድርድር በመጥራት እሹሩሩ ጀመረች በስተመጨረሻም ግድቡን ዉሃ ላለመሙላት በመስማማት አጭብጭባና ተጨብጭባ ወደ ወደምትዋሸዉ ህዝብ ተመለሰች።  ከዚህ ጋር በተያያዘ ሳሊኒ የተባለዉ ግድቡን ሊሰራ የተዋዋለዉ ድርጅት በተባለዉ ወቅት አጠናቆ ለመዉጣት እንደማይችል በመረዳቱ ጓዙን ጠቅልሎ ተሰናብጧል አልጀዚራ እንዲህ አስቀምጦታል  ( Salini Construttori, circumventing its own contract procedures and international standards on procurement. The construction is reportedly lagging behind schedule and faces several unresolved technical problems )

ዛሬ የአባይን ግድብ በተመለከተ አዲስ መረጃ አግጥጦ እየወጣ ይገኛል ይህዉም በቦንድ እና በልግስና ከሐገር ዉስጥ እንዲሁም ከሐገር ዉጭ የተሰበሰበዉ ገንዘብ በሙስና እንደተመዘበረ የዉስጥ መረጃዎች እየመሰከሩ ነዉ፡፤ በሰሞኑ በዚሁ ዙሪያ ላይ በተደረገ ግምገማ በቢሊዮን የሚቆጥር ገንዘብ በብር መመዝበሩን ተጋልጧል! በዚሁ መሰረት በተለይም ከደቡብ አፍሪካ ለመሰብሰብ ከታቀደዉ ገንዘብ መካከል እንደተገመተዉ ባዮንም ከከንባታና ሐዲያ ማህበር እና በዚያ ከሚኖሩ የወያኔ ደጋፊዎች የተሰበሰበዉ በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ከደቡብ አፍሪካ ወደ ቻና ተሸጋግሮ ከቻይና ወደ ኢትይጵያ ተልኮ ያለምንም ቀረጥ ለመስፍን ኢንጂነሪንግ እቃ ተገዝቶ መላኩን እና መስፍን ኢንጂነሪንግ ገንዘቡን አለማወራረዱን እማኞች ሲመሰክሩ በደቡብ አፍሪካ በከፍተኛ ሁኔታ ስደተኛዉን በማስተባበር ገንዘብ ለመሰብሰብ የተባበረ አንድ በወንጀል የተጨማለቀ ግብረ ወያኔ! ስሙን ለጊዜዉ መግለጽ ያልተፈለገ ግለሰብ የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ተሰጥቶት የገንዘብ ዝዉዉሩን እዳከናወነዉ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአባይ ግድብ ስም ከምስኪኑ የኢትዮጵያ ህዝብ የተመዘበረዉ ገንዘብ ባጠቃላይ የወያኔ ካምፓኒዎች ማለትም የኤፈርትን አቅም በሚያጎለብት መልኩ ብቻ ተግባራዊ እንዲሆን በታቀደዉ መሰረት የመሶበ ሲሚንቶ ፋብሪካ አሁን በስራ ላይ ላልሆነዉ የግድቡ ኮንስትራክሽን ቅድመ ክፍያ ከ2.7 ቢልዮን ብር በላይ መሰጠቱን እና ባጠቃላይ የኤፈርት ካምፓኒዎችና ተዛማችነት ያላቸዉ ቤተሰባዊ ወያኔ ለሆኑ ድጅቶች ወደ ጥቅም ያልተወራረደ ከአንድ መቶ ሃምሳ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉ ሲጋለጥ ለዚሁ ሁሉ መሰረታዊ ምዝበራ ግንባር ቀም ሚና የሚጫወቱትም ተጠቅሰዋል።

በመሆኑም ከባለስልጣናቱ መካከል በተለይም ስብሃት ነጋ የተባለዉ ግለሰብ የሴት ልጁ ባለቤት በግድቡ ዙሪያ ላይ በሚወጡ የስራ ፕሮፎርማዎች ላይ ማንኛዉንም መመሪያና ትእዛዝ እየተቀበለ እንዲሁም ስራዉ ለማን መሰጠትና ማን ተጠቃሚ እንደሚሆን ተራ በተራ የህዝብን ንብረት በመመዝበር ላይ መሰማራታቸዉን የደርሰን መረጃ ያመለክታል።

ቄሮ የኦሮሞ ወጣቶች ለነፃነት ንቅናቄ ድምፅ – የሳምንቱ ዜና – March 13, 2015

የውጭጉዳይ ሚ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም አሁንም በስብሰባ ላይ ሲዋረዱ የሚያሳይ ቪድዮ ይመልከቱ

የውጭጉዳይ ሚ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም አሁንም በስብሰባ ላይ ሲዋረዱ የሚያሳይ ቪድዮ ይመልከቱ

http://www.zehabesha.com

ከወያኔ ጋር ክርክር አጉል ጉንጭ ማልፋት

እንደው አሁንስ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች በቀቢጸ ተስፋ እንዲህ ሲለፉ ሳይ በጣም እያሳዘኑኝ መጡ፡፡ ድሮ እናቴ ስትነግረኝ “ለማይገባው ሰው ነገርን መንገር ድንጋይ ላይ ውሃ ማፍሰስ ነው“ ትለኝ ነበር እውነትዋን ነበር፡፡ ገዥው መንግስት ላለፉት ሃያ ሁለት አመታት ሲያስተዳድር አንድም ቀን ቀጥተኛና ፍትሃዊ ነገርን ሳይናገርና

ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ ወይም ቪዲዮውን ለማየት እዚህ ላይ ይጫኑ።

http://www.zehabesha.com

ይድረስ ለጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ

 

mot

 

 

 

ግሩም ተ/ኃይማኖት
ይድረስ ያልኩት በቀጥታ ባይደርሶትም መስማትዎ እንደማይቀር እገምታለሁ። ሰላም የምሎት ሰላምታ የእግዚአብሔር በመሆኑ ነው። እንጂ ጫንቃችን ላይ ተጎብራችሁ የዜግነት ክብንርን አውርዳችሁ የዜግነት ክብር የምታዘምሩ በሆናችሁ፣ በብሔር፣ በጎሳ ከፋፍላችሁ … ሰብዓዊ መብታችንን ገፋችሁ … ኑሮን መቋቋም እንዳንችል አድርጋችሁ ለስደት ስለዳረጋችሁን

ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ ወይም ቪዲዮውን ለማየት እዚህ ላይ ይጫኑ።

http://www.ethiopianreview.info

ህወሓት አይድንም፤ እያቃሰተ ነው (አስገደ ገብረስላሴ ከመቀሌ)

hulut

‹‹የሕ. ወ.ሓ.ት ትንሳኤ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ድላችን የማይቀር ነው ›› ስብሓት ነጋ

አቶ አሰገደ ገ/ሥላሴ

በጌታቸዉ አረጋዊ የህ... ኣባልና የድምፅ ወያነ ጋዜጠኛ «ውራይና » የሚል በትግርኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ለአራተኛ ጊዜ በነሃሴ ወር 2005 / የታተመ መፅሄት ስብሓት ነጋ የህ... ፈላስፋ ቃለ መጠይቅ ያደረገበት መፅሄት በፅሞና ኣነበብኩት። የመፅሄቱ ዋና ይዘት ‹‹... እናድናት›› ነዉ የሚለዉ ስብሓት ነጋ በመፅሄቱ የተካተቱ ብዙ ስንክሳራዊ ሃተታ ተናግሯል

አሁን ማለት የፈለግኩት በመፅሄቱ የተካተቱ በሙሉ መልስ ለመስጠት አይደለም፡፡ ምክንያቱም የስብሓትን ስንክሳር መልስ ለመስጠት ከፈለኩ ግዜ አይገኝም መፅሃፍም ሊሆን የሚችል ነዉ። በመሆኑም አለፍ አለፍ በማለት የስብሓትን አንኳር አንኳር ነጥቦች መልስ ለመስጠት እሞክራለሁ።
ሌላ ይህ ፅሁፍ መልስ ለመስጠት የተገደድኩት የ ህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች ለትግርኛ ቋንቋ ማዳበርን በትግርኛ ስነ-ፅሁፍ ለማስፋት ብለዉ በፅሁፍ ቢናገሩ እጅጉን የሚደገፍና የትግራይ ህዝብ መስዋእት ነበር። ይህ ደግሞ ማንም ኢትዮጵያዊ ይድግፈዋል፤፤

የ ህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች ግን ከረጅም ጊዜ ጀምረዉ ለትግራይ ህዝብ በጠባብነት ለመነሳሳት ሲፈልጉ ወይ መምቻ ሃይል ሊጠቀሙበት ሲፈልጉ የሚናገሩት የሚፅፉበት ኢትዮጵያዊ አጀንዳ እያለና ያለ ትግራይ ህዝብ የሚነገር የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጉዳይ አድርገዉ እንደመናገር ፈንታ በድብቅ ይናገራሉ።

ስብሓት ነጋም በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ሃገራችን ብዙ ደንቃራ ሁኔታዎች ተደቅነውባትና ህዝቡ በብዙ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፖለቲካዊ ችግሮች አጋጥመውት እያሉ ለትግራይ ለአንድ ክልል ከ4-5 ሚሊዮን ህዝብ ያላት ለብቻዋ የሚወከል ህ.ወ.ሓ.ት ትንሳኤ መተንበይ ሌላዉ የኢትዮጵያ ህዝብና ክልሎች … በሂወት ካሉት በታች ከሞቱት በላይ የሆኑ ህዝቦችና ክልሎች እንደማሰብ ትግራይን ጨምሮ ማለት ነዉ። ለትግራይ ብቻ ማሰብ ለስብሓት ነጋ ጠባብ ሊያስብላቸዉ የሚችል ይመስለኛል።

በሌላ በኩል የስብሓት ነጋ ትንሳኤ ሙዉታን ሲለን የህ.ወ.ሃ.ት ትንሳኤ ሙታን ለመመለስና የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ከመሰነጣጠቅና ከመክሰም እንዴት እናድነዉ ጭንቀቱ እንጂ የትግራይ ህዝብ ባጠቃላይ የሃገራችን ህዝቦች ብሄር ብሄረሰቦች ከዲሞክራሲና ሰብኣዊ መብቶች ነፃነትና አፈና አስተዳደር እንዴት እናድናት አይደለም ጭንቀቱ፤፤ ይህ ካልኩ በኃላ ወደ መፅሄቱ ላይ የሰፈረዉ አንዳንድ መልስ ለማስቀመጥ እሞክራለሁ።

ስብሓት ነጋ በአሁኑ ጊዜ ያለዉ የህ... አመራር ለነዚህ ለአመታት እያጠራቀማቸዉ የቆየ ችግርን በፍፁም ነፃነት በፍፁም አባታዊነት በትክክል ከተረዳቸዉ መረዳትም ያለበት ነዉ።‹‹ ... ትንሳኤ ጊዜ ይወስዳል እንጂ ድላችን የማይቀር ነዉ።›› ይላል ውራይና መፅሄት ነሃሴ 2005 ገፅ 4 ሶስተኛ አምድ አዲስ መስመር ሁለት

sebhat

ስብሃት ነጋ ከእንግዲህ ወዲህ የምናውቀዉ ህ.ወ.ሓ.ት ከነበሩበት ብዙ ችግሮች ሲያሳየዉ የነበረ መገላበጥ የተሳሳቱ ሃገራዊና አህጉራዊ አቋሞች በተለይ ደግሞ በሃገር ሉኣላዊነት የሚመለከት ሃገራዊ ሃላፊነት የጎደለዉ ብዙ ስህተትና ጥቁር ነጥብ ቢሰራ በፀረ-ደርግ የነበረዉ አቋም የኃላ ኃላ ለስልጣኑና የግዛቱን ማስፋፋት ሲል ያመጣዉ አገር አቀፍ አመለካከት ለኢትዮጵያ ህዝብ ለጊዜዉ ከፋሽስታዊ ደርግ አፈና አድኖታል። ተነፃፃሪ ሰላም ያመጣ ይመሰል ነበር ሆኖም ግን የህ.ወ.ሓ.ት አመራርና እሱን እሚመስሉ እሱ የፈጠራቸዉ የህ.ዋ.ሓ.ት ስሪት ፓርቲዎች ልክ ደርግ መጀመሪያ ወደ ስልጣን ሲመጣ ኢትዮጵያ ትቅደም ያለ ምንም ደም እንዳለና ቀስ በቀስ ወታደራዊ ባህሪዉ አገርሽቶበት ፍፁም ለኢትዮጵያ ህዝብ ፋሽስትና ፀረ ህዝብ የሆነዉ የህ.ዋ ሕ.ት መሪዎች የትግራይ ህዝብና ልጆቹ በሃገር ደረጃ ደርግ ከተደመሰሰ ብቻ ነዉ ሰላም፣ ፍትህ፣ ዲሞክራሲ፣ ነፃነት፣ የህግ የበላይነት ይመጣል እያለ በመቶ ሺዎች ዜጎች የሰጡትን ደርግን አስወግዶ ወንበሩን ከተቆናጠጠ በኃላ ትላንትና ሽሮ አለ መረቅ አለ እያለ ወደ እሳት እየማገደዉ የመጣ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከዳ የትግራይ ህዝብ ነበር። ውጤቱ ደግሞ የትግራይ ህዝብ ሳይሆን መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ በአሁኑ ጊዜ አግኝቶት ያለ ምንድነዉ ?

ስደት በየአህጉሩ ተበታትኖ ሞት መታረድ በባህር የአሳ ቀለብ መሆን ሁሉም አይነት መብቶች ማጣት አንድነት መላላት ሉአላዊነቱን መደፈር ነዉ። በተለይ ደግሞ የህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች አመራር ትንሳኤ መውታን ካልተረጋገጠ የትግራይ ህዝብ አይኖርም የምትሉት 22 አመት ሙሉ ለውጥ ያላመጣ ችሎታ አሁን በሁሉም ነገር ከፈረጃችሁ በኃላ ‹‹ከገባንበት አዘቅት አውጡን›› ብትሉን አቶ ስብሃት ማን ያምንሃል የትግራይ ህዝብ ለናንተ ተንከባክቦ አምጥቶ ምን ጥቅም አገኘ ። የትግራይ ህዝብ ልጆች ተምረዉ ስራ አጥተዉ የሚላስ የሚቀመስ አጥተዉ የስብሓትና የጓደኞቹ ልጆች ግን ዘር መንዘራቸዉ በቻይና በእንግሊዝ፣ ኣሜሪካ በሌሎች ምእራብ አገሮች ተምረዉ በተቀማጠለ ኑሮ ነዉ የሚኖሩት፤፤ ይህ እኮ የኢትዮጵያ ህዝብ አበጥሮ ያውቀዋል። ስለዚህ በኔ እምነት በአሁኑ ጊዜ ስብሓት እንደ ምትለዉ የ.ህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች ትንሳኤ ሙታን በአሁኑ ጊዜ አያስፈልግም፡፡ አዲስ ትውልድ የአዲሱ ትውልድ የህ.ወ.ሓ.ት አመራር ንኪኪ ያልተበላሸ ኢትዮጵያዊ አመራር ያስፈልጋል። ይህ ነዉ ሃቁ።

« ስብሃት ነጋ የህ... አመራር እዚህ ግባ የማይባለዉ አቅም ተነስቶ ለትግራይ ህዝብ አሳልፎ እጅጉን ጥልቀት ካለዉ አድሃሪ አሰላለፍ አሸንፎ ለማመን የማይቻል ሃገራዊ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት በመፍጠር ወሳኝ ሚና ተጫውቷል። አሁንም አሁን ያለዉ የህ... አመራር የትግራይ ህዝብ በመያዝ ... አይፈጠርም አንልም። ‹‹በመሆኑ ቅድምና በቅርቡ ከህ... /ኮሚቴ የወጡ የህ... አመራር ነበር እንደ አዲስ በመደራጀት አሁን ላለዉ /ኮሞቴ የሚያግዝበት መንገድ መፈለግ አለበት ይላል»

‹‹ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ›› ይባላል አይደለ አቶ ስብሃት የህ.ወ.ሓ.ት አመራር 40 አመት ሙሉ ቆይቷል፤፤ ስብሃት ነጋም 39 አመት በአመራር ቆይተሃል በህ.ወ.ሓ.ት ከ1967፣ 1969፣1970 ዓ/ም የነበሩ የህ.ወ.ሓ.ት የሃሳብ ልዩነት በፀረ ዲሞክራሲ የግጭት አፈታት ስብሃትም ነበርክ በ 1982 ዓ/ም አባይ ፀሃዬ ከስልጣን በማውረድ መለስን ወደ ስልጣን ካስወጡ አንዱ አንተ ነበርክ ።በ1993 ዓ/ም ከህ.ወ.ሓ.ት መሰናጠቅ ጋር ተያይዞ ህ.ወ.ሓ.ት በሁለት አንጃ ሲሰናጠቅ አንተም ስልጣን ከያዘዉ አንጃ ጋር ሆነህ ለወጣዉ አንጃ በማውገዝ በዋናነት አንተ ነበርክ። አሁንም በቅርቡ የነበረዉ የህ.ወ.ሓ.ት መተካካት የሚባልም የተኩ ይሁኑ የተተኩ በሁሉም ነገር እዚህ ግቡ የማይባሉ ናቸዉ፤፤ መሪ የነበረ ሲወርድ አንጃ የነበረዉ ነዉ ወንበሩን የያዘዉ፤፤ ስለዚህ ህ.ወ.ሓ.ት ከሲቪል ብቁ መሪ አላፈራም ብቁ ምሁር የማስጠጋት ባህል አልነበረውምና፤፤ በቅርቡ ከህ.ወ.ሓ.ት የወጡ አመራሮች በመሰረቱ የሚበቃቸው ነገሮች ስለያዙ ነዉ እንጂ ስልጣን ጠልተዉ አይደለም፤፤ እነሱ ቢመለሱም እያቃሰተ ያለዉ ህ.ወ.ሓ.ት ሊያድኑት አይችሉም። አቶ ስብሃት ወንበር ብትይዝም አንደኛ ተቀባይነት የለህም፡ ሁለተኛ እድሜዉም ገፍቷል እነርሱም በቅን ይሁን በተንኮል እየሰሩ አቅማቸው ተጨርሷል። ስለዚህ በቅርቡ ከ ህ.ወ.ሓ.ት የተቀነሳችሁ ህ.ወ.ሓ.ት ልታገግም ለማድረግ አትችሉም፤፤ ህ.ወ.ሓ.ት እኮ በስም እንጂ በአካል የለችም ይህ ትክክልኛ ነዉ።

1993 / የተገነጠሉ አንጃዎች በስብሀት አይን እነሱ ከተመለሱ ... ትነሳለች ነዉ እያለ ያለዉ?

duba
በኔ እምነት የወጡ አንጃዎች አብዛኞቹና የቀረዉ አንጃ የስልጣንና የሃብት ማካበት ልዩነት እንጂ መሰረታዊ የሆነ የህዝብ ጥያቄ አልነበራቸዉም እነዛ የህዝብ ጥያቄ የሃገር ሉአላዊነት አልተከበረም ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች አልተከበሩም በኢኮኖሚ ፖሊሲ፣በፖለቲካዊ አስተሳሰብ(አይዶሎጂ) ልዩነት የነበራቸውና አሁንም ለህ.ወ.ሓ.ት ኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግ እየታገሉ ያሉ ከ3 ሰዎች አይበልጡም።

ሌሎች ግን ትላንትና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ወጣት ግቡ እያሉ ወደ ጦርነት እያስገቡ አዲስ አበባ እንደገቡት እንደጥርስ መፋቂያ ተጠቅመዉ የጣሉት አሁን በወጣቱ መስዋእት ስማቸዉ ገኖ በአለም አቀፍ ታዋቂነት አግኝተዉ በንግድ አለም ተሰማርተዉ ከነቤተሰቦቻቸዉ በመላዉ አለም እየናጠጡ ይገኛሉ። በሃገር ውስጥ ያላቸዉ ሃብትም ለዘር መንዘራቸዉ የሚበቃቸዉ ነዉ። ስለዚህ ስብሃት እያልከን ያለሀዉ እነዚህ አንጃዎች ተመልሰዉ ወደ ህ.ወ.ሓ.ት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ከመጡ ህ.ወ.ሓ.ትን አድነዉ በሃገራችን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ያመጣሉ ነዉ እያልከን ያለሀዉ ? ይህም የዋህነት ይመስለኛል አሁንም 1ኛ የመንግስትን ያህል ሃብት የሰበሰቡ ናቸዉ ፤

ሁለተኛ እድሜም ገፍቷል፤ ሶስተኛ ተቀባይነት የለም፤፤ ስለሆነም እዚህ ላይም የስብሃት አባባል ውድቅ ነዉ።

እነዚህ ሰዎች በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ህዝብ ዲሞክራሲ ልማት ፍትህ አጥቶ ከላይ እንደገለፅኩት ህዝቡ ተቸግሮ በአለም ተበታትኖ የከፋ ኑሮ ሲገፋ ስለህዝብ ችግር አጀንዳ አንስተዉ ሊነጋገሩስ ይቅርና ጭራሹም በዚህች አገር ምን ችግር እንዳለ ግምት ላይ አያስገቡም እንዳውም ከዚህ ድሃ ህዝብ የተወለዱ አይመስሉም፤፤ ከልዩ ፍጥረት የተፈጠሩ ነዉ የሚመስሉት ። እነዚህ በኔ እምነት በተለያዩ ጊዜ ከህ.ወ.ሓ.ት ተገንጥለውና በመተካካት የተቀነሱ በስልጣን ያሉ የህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች ቢሰባሰቡ ህ.ወ.ሓ.ትን አክመዉ ለሞት ከመቃሰት አያድኑትም። ስብሃት ነጋ ያልተረዳዉ ነገር ቢኖር ህ.ወ.ሓ.ት የምትባል ፓርቲ አቶ ስብሃት ያለበት ፈራጅ ቡድን በ 1985 ዓ/ም የዲሞክራሲ ጥያቄ የሉአላዊነት ጥያቄ በማስነሳቱ በግፍ የታሰሩ የተባረሩ በዛ እንደወጡ የቀሩ እለት ነዉ ህ.ወ.ሓ.ት የሞተች መለስም አንተም በ1993 ዓ/ም ለነበረ የህ.ወ.ሓ.ት የሁለተኛ አንጃ መሰንጠቅ ለመምቻ ተብሎ ያመናችሁበት ነበር እሱም የ1985 ዓ/ም ታጋዩ ያስነሳዉ ጥያቄ ትክክል ነበረ ግን ምን ይሁን ኮለፍነዉብላችሃል።

« ስብሃት ነጋ አሁን ደግሞ የ ህ ወ.ዋ.ሓ.ት አባልና የትግራይ ህዝብ ታግሎ ያመጣውን ስርአት ማክበር ብቻ ሳይሆን ታግሎ ለመጣዉ ስርአት ቀዳሚ ግንባር በመሰለፍ ሊከብርና ሊያስከብር ሊያገኝ ሌሎችም እንዲያገኙ ማክበር አለበት» በገፅ 4 ሶስተኛ አምድ አንቀፅ ሁለት መስመር 25፤፤ አቶ ስብሃት የትግራይ ህዝብ ከሌሎች የኢትዮጵያ ወገኖች ጋር ታግሎያመጣዉ ስርአት ነበር ግን በናንተ ተቀምቷል፤፤ አይቶ አጥቷል የትግራይ ህዝብ የደርግን ሁሉም አይነት ግፍ ያልፈራ በእናንተ ግን የመግስት ሰራተኛ ነጋዴዉ ፣ አርሶ ሰደሩ ፣ ወዛደሩ፣ ተማሪዉ ፈርቶ ተሸማቅቆ እንዲኖር ተርቦ እያለ አልራበኝም ታሞ እያለ አልታመምኩም ውሃ ጠምቶት አልጠማኝም እንዲል አድርጋችሁታል፤፤ ለባለስልጣን መውቀስ ሂስ ካደረገ ወደ ላይ አትንጠራራ ብሎ ጭንቅላቱን ደፍቶ እንዲሄድ ተደርጓል። ሌላዉ አቶ ስብሃት የትግራይ ህዝብ ታግሎ ያመጣውን ስርአት ፊት ተሰልፎ መጠበቅ አለበት ተብሏል፤፤ የማንና የማን ሃብት ህንፃ ሊጠበቅ ነዉ ይህ ማታለል ነዉ። የትግራይ ህዝብ በአሁኑ ጊዜ በወንዝ ተከልሎ ማሰብ ትቶ ተሻግሮ በሩቅ አይቶ የኢትዮጵያ አንድነትና ሉኣላዊነት ነዉ ሚታየዉ ያለዉ እምቢ ለጠባብነት እያለ ያለዉ።

የአቶ ስብሃት ጠባብ አመለካከት አልፏል ድሮም የህ... አፈና ደርግን ለመጣል ሲባል ተሸፍኖበታል እንጂ ስለ አንድነት ጉዳይ ስለ ባህር በር ስለ ኤርትራ ጉዳይ ብዙ ጥያቄ አንስቶ እነ ስብሃት ምን አይነት መልስ ትሰጡት እንደነበራችሁ ራስህም ታውቀዋለህ። ስለዚህ የትግራይ ህዝብ ሃሳብህን አይቀበልህም።

ሌላዉ የትግራይ ህዝብ ይሁን መላዉ የኢትዮጵያ ህዝባችን የህ.ወ.ሓ.ት በ1983 ዓ/ም ደርግን አስወግዶ ወንበሩን ሲቆነጠጥ የህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች ህዝቡ ታግሎ ባመጣዉ ድል ተጠቅማችሁ ከደርግ ተለይታችሁ ለመታየት ብዙ ዲሞክራሲ የሚመስሉ መግለጫዎች ትሰጡ ነበር።በመሬት ላይ የነበራችሁ ፖሊሲም ለምእራብ ሃገሮች ፖለቲካ ፍጆታ ብላችሁ ነፃ ኢኮኖሚነት መብት የምትጠብቁ ትመስሉ ነበር ቀስ በቀስ ግን የፀረ ዲሞክራሲ ባህሪያችሁ አገርሽቶበት እንደ ወትሮ ሆናችሁ የቻይና ታማኝነታችሁ አረጋግጣችሁ መሬት ለምን የህዝብ አላችሁ።

በአሁኑ ጊዜ የህ.ወ.ሓ.ት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መሪዎች የከተማም ሆነ የገጠር መሬት የኔ ነዉ 90 ሚሊዮን ህዝብ የመሬት ጢሰኛ ነህ ብላችሁ ፍፁም ዜግነቱ ቀምታችሁታል፤፤ ኢትዮጵያዊ ዜጋ መሆኑ እንዲጠራጠር አድርጋችሁታል፤፤ ታዲያ ስብሃት ነጋ የትግራይ ህዝብ የታገሉለት አላማ እንዳይቀማ ፊት ተሰልፎ ለህ.ወ.ሓ.ት ይጠብቃት ስትለን በ 17 አመቱ የትጥቅ ትግል የከፈለዉ ሂወትና ቁሳቁስ ያልጠቀመዉ አሁን እንደገና የህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች ልጆቻቸዉ እንዲሁም ምንጩ የማይታወቅ የሰበሰቡት ሃብት ሊጠብቅ ነዉ የምትፈልገዉ? አይታሰብም ዋና ችግራችሁ ለሁሉም ስራችን መስተዋታችን ህዝብ ነዉ ስትሉ የነበረ በመክዳት በአሁኑ ጊዜ ህዝብ ምን ይላል የሚል መረጃ አለመኖራችሁ ነዉ እንጂ ህዝቡ ለውጥ ፈልጓል የህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች ልክ ከባህር እንደወጣ አሳ ከልብ አውጥቶ ጥሏቹሃል። አሁን ግን ትልቁ ችግር ሆኖበት ያለዉ የመንግስት የፍትህ አካላት በደህንነት በፖሊስና ፌዴራል ፖሊስ በአቃቤ-ህግ ታፍኗል፤፤ በአሁኑ ጊዜ በሃገራችን ያለዉ አስተዳደር በአዋጅ ወታደራዊ አስተዳደር ስላልተባለ ነዉ እንጂ በተግባር ወታደራዊ አንባገነናዊ ስርአት ነዉ ያለዉ። ታዲያ ስብሃት ነጋ ለትግራይ ህዝብ ለዚህ ስርአት ጠብቀዉ ነዉ እያለ ያለዉ ደግሞ በባዶ ሆዱ እንዴት ብሎ ይታሰባል;

« የትግራይ ህዝብ ታግሎ የሚያታግለዉ የሚጠቅመዉ አብዮታዊ መሪ ድርጅት ያስፈልጋል›› ስብሃት ነጋ ገፅ 4 በአርእስት የተፃፈ» (በትግርኛ ህዝቢ ትግራይ ተቓሊሱ ዘቃልስ ዝጠቕሞ ወያናይ ውድብ ክረክብ ይግበኦ)

ስብሓት ነጋ እያልከን ያለሀዉ የትግራይ ህዝብ ታግሎ የሚያታግለዉ አብዮታዊ ፓርቲ ያስፈልገዋል ነዉ። በዚህ አባባል እኔም እስማማለሁ አዎን አብዮታዊ ፖለቲከዊ ድርጅት ያስፈልገዋል ።ግን የትኛዉ አብዮታዊ ፓርቲ; ህ.ወ.ሓ.ት ከማቃሰት እናድነዉ ከሆነ በትግራይ ክልል ህዝብ ይሁን ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ህ.ወ.ሓ.ት ኢ.ህ. ኣ.ዴ.ግን አይፈልግም፤፤ በወታደራዊ አስተዳደር ስለታፈነ በምርጫ ጊዜ ለፈለገዉ ቦታ የመረጠዉ ካርድ ስለተቀማ ከክልል እስከ ጎጥ በአንድ ለአምስት የደህንነት መዋቅር ስለታፈነ ብቻ ነዉ። ስለዚህ ከእንግዲህ የትግራይ ህዝብ ለስብሃትና ጓዶቹ ሎሌ ሆኖ አይኖርም፤፤ በሰላማዊ መንገድ ትግሉን በማስቀጠል የኢትዮጵያ ህዝብ የስልጣን ሉአላዊነቱ ሊያረጋግጥ ነዉ።

ግን አቶ ስብሀት ነጋ ሁሉ ግዘ ለትግራይ ህዝብ እየተቆረቆርክ መስለህ የጠባብንት አመለካከት ታሰራጫለህ፤፤

ይህንን ያልኩበት ምክንያት 90 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ በአስከፊው የህ.ወ.ሀ.ት ኢ.ህ.አ.ደ.ግ መሪዎቹና ካድረዎቹ አፈና መዳፍ ገብቶ እያለ ለኢትዮጵያ ህዝብ እንደ ማሰብ ፋንታ የትግራይ ህዝብ ለብቻው ነጥለህ ለበሰበሰ ስርአታችሁ ዘበኛ ማድረግ አያዋጣም፤፤ የትግራይ ህዝብም አይቀበለውም፤፤ ለአንድነቱ የቆመ ነውና፤፤

‹‹ «ስብሃት ነጋ ሙስና ዋነኛዉ የስርአታችን አደጋ ነዉ›› ብሎ የተነሳ ፓርቲና መንግስት ለምን ወደዚህ የተበላሸ ሙስና አደጋ ደረሰ የሚል ጥያቄ በብቃትና በቆራጥነት ካለተፈታ በዚህች አገር ምን ሊፈጠር ነዉ? ሙስናና ብልሹነት ከቁጥጥር እየወጣ ነዉ የሚል ጥቆማ ከአገር ውስጥም ከውጭ አገር ለሚመለከተዉ ጥቆማዉ እንደ ጎርፍ ይፈስ ነበር በጊዜዉ ግን ሰሚ ጆሮ አላገኘም » ›› ውራይና መፅሄት ገፅ 3 አንቀፅ አንድ መስመር ሰባት፤፤

አቶ ስብሃት እንደምትለዉ ህ.ወ.ሃ.ት ከ1984 ዓ/ም ጀምሮ በስብሰባ በብዙሃን መገናኛ ስለሙስና ብዙ ይናገር ነበር፤፤ በተለይ ደግሞ የህ.ወ.ሃ.ት አመራሮች ሙስና በናንተ ነበር የተጀመረዉ፤፤ ምርጥ ቤት ለራስህ ለዘር መንዘርህ ለአንድ መሪ ከሁለት እስከ 3( 4 መኪና) መያዝ ነዳጅ ያለገደብ መጠቀም የራስህና የቤተሰብ ህን ኑሮ ማሻሻል ከውርሃዊ ገቢህ ጋር የማይመጣጠን በየቀኑና በየሳምንቱ በሂልተን በሶደሬ መዝናናት የቤት እቃዎች በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ወጭ ማድረግ ከባለሃብቶች ገፀ በረከት ስጦታ መቀበል፣ በየጊዜዉ ብዙ ወጭ በማውጣት ግብዣ ማድረግ ልዩ ፍጡር ሆነህ መታየት ረጅም ሳይጓዙ ወደ ይኩራሩበት የነበሩ የንጉሳዊ ቤተሰብ ቅምጥል ኑሮ እነሱን አልፈዉ ሄደዉ በየምሽቱ በአስር ሺህ ብር የሚቆጠር ገንዘብ ማባከን በልጅ ጥምቀት ፣ የልደት ቀን ሰንጋዎች ማረድ በዊስኪ መራጨት ጊዜ እየገፋ ሲሄድ በግልፅ የማይታወቅ ሃብት ማካበት በተለያየ መንገድ ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች መገንባትና ስም ቀይሮ ብዙ የደረቅና የፍሳሽ የጭነት መኪና መግዛት ሌላ ቀርቶ የመሪዎች ሚስቶች ውጭ አገር ሄደዉ እንዲወልዱና ለወደፊት በዛው የውጭ አገር ዜግነት ይዘዉ ቆይተዉ መሸሻ ቦታ ማዘጋጀት ብሎም ቤት መስራት ስልጣንህ ተጠቅመህ ዘርመንዘርህ ውጭ መላክ ነበር። ለዚሁ ማረጋገጫ በቻይና በ10 ሺህ የሚቆጠሩ የመሪዎች ልጆች የሚማሩ ኣሉ። ሌላ ዋነኛዉ በመንግስት ስራ አመዳደብ በሞያ እንደመሆን በዘመድ አዝማድ በጋብቻ በጓደኝነት አድርገህ ስራው በሞኖፖል መያዝ ሌላ ስራተኛ እንደ ሁለተኛ ዜጋ ማየት ነበር።

ኣቶ ስብሃት ይመሩት የነበረ የኢፈርት ድርጅቶች በአስር ቢሊዮን የሚቆጠር ካፒታል ያላቸውም ለስሙ በህዝብ ስም እየተነገደባቸው ለሙሰና ብልሹነት የተጋለጡ ሆነው የሄዱት ስፍር ቁጥር የላቸውም፤፤ ሁሉም ለስሙ በህዝብ ስም እየተነገደባቸዉ ለሙስናና ብልሹነት የተጋለጡ ሆነዉ የኦዲት ቁጥጥር የለባቸዉም፤፤ ሁሉም ገንዘቡን የሚያውቀዉ ስብሃት ነጋ ነበር፤፤ ቁልፉም እሱ ነበር ኃላም ስብሃት ሲለቅ ስዬ አብርሃ ቀጥሎ ኣባዲ ዘሞ በመጨረሻም አዜብ መስፍን የበላይ ጠባቂ ጠ/ሚኒስቴር መለስ ነበሩ።ስብሃት ነጋም እስከአሁን የግዙፍ ካምፓኒ የወጋገን ባንክ ቦርድ ዳይሬክተር ነህ፤፤ ይህ ባንክ ከፍተኛ አክሲዮን የህ.ወ.ሃ.ት ሃብት ነዉ ስንት ካፒታል አለዉ ማን ይቆጠቀጠረዉ የሚለዉ መልሱ ለስብሃት ነጋ ነዉ።

እንግዲህ የሙስና ጉዳይ ከተነሳ በዘመነ ህ.ወ.ሃ.ት ስርአት ሙስና በኢትዮጵያ አደጋዉ እንዲስተካከል አስተያየት የሚሰጡ ቅን አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የውጭ አንባሳደሮች መንግስታት የአለም ባንክም ምክር ይሰጡ ነበር፤፤ ለዚህ አስተያየት ከአቶ ስብሃት ጀምሮ ሁሉም የህ.ወ.ሃ.ት መሪዎች ሰሚ ጆሮ አይሰጡትም ነበር። ምክንያቱም ሁሉም የተነካኩ ናቸዉና። ስለዚህ ስብሃት ነጋ ‹‹የሙስና መረጃ እንደጎርፍ ይፈሱ ነበር ግን ሰሚ ጆሮ አልነበረም፤፤›› ስትለን አንተስ ሙስና ኣለ ብሎ መረጃ የሰጠህ ቅን ኢትዮጵያዊ እንደ ጠላት አይተህ ከስራ አላባረርክም ? በጥላቻ እንዲታይ አላደረክም ይህ አባባል ማታለያ ነዉ ። አንድ ነገር በዚሁ እድሜ በገፋበት በምፅተአለም ዋዜማ አገራችን በሰዉ ሃብት የሃገር ሃላፊነት የማይሰማቸዉ ጅቦችና ከወደመችና የአገራችን አንጡራ ሃብት ውጭ አገር ከሰፈረ በኃላ ሆነ ራሱ ግን የስብሃት ልግም እንጂ አብዮታዊ ነት አያሳይም።

ስብሃት ነጋ ‹‹የተበላሸ ሙሰኛ ሁሉ በየደረጃዉ መታረም አለበት ስርአቱን በመጣስ ቤት ከፍቶ የሰረቀ መሆኑ እያወቀና እየሰማ እርምጃ ያልወሰደ በከፍተኛ ደረጃ ጥፋት መጠበቅ አለበት። ቤት ከፍቶ አግኝቶ ትንሽ የቀመሰ ደግሞ በሁለተኛ ደረጃ የሚስተካከል መሆኑ ህዝቡን ለማረጋጋት ያስችለዋል» ውራይና መፅሄት ገፅ 5 3 አምድ አንቀፅ 3 መስመር አንድ

አቶ ስብሃት ነጋ አንደኛ ነገር አንተን ከሙስና ነፃ እንደሆንክ በሁለተኛ ደግሞ ቢሊየን የሰረቀና ሚሊዮን የሰረቀ እኩል መታየት የለባቸዉም፤፤ ምክንያቱም ትንሽ ለሰረቀ ቀላል ቅጣት ከሰጠኸዉ ህዝብ ሊረጋጋ ይችላል ብለሀናል። የትኛዉ ህዝን ነዉ? ግልፅ አይደለም፤፤ አሁን እኮ ዋና ሌባ የሚባለዉ ከቀበሌ እስከ ፌዴራል ያለዉ ባለስልጣን በሙስና ተራክሷል፤፤ ይህ መዋቅር ከህዝቡ ከ3 እስከ 5% ነዉ የሚሆነዉ ቅጣቱ ይቀላል ምትለዉ ያለህ ለማነዉ? ለምስ ነዉ የሚቀልበት? በኔ እምነት አቶ ስብሃት የምትለን ያለ ታች ሆኖ ህዝብ ያሰቃዩ ሎሌዎች ከተመቱ ለወደፊቱ በየመድረኩ እጅ እያወጣ የስ እያለ የሚውል ሰዉ አናገኝም፤፤ በምርጫ ጊዜ ኮረጆ የሚሰርቅ የለንም፤፤ ከሚል የመነጨ ነዉ ትንሽ የሰረቀ ይማር የምትለን ያለህ በሌላ በኩል ትልቁ ብልሹ ሙሰኛም ይመታ ስትለን ቁርጠኝነትህን አይደለም የሚያመለክት፤፤ አቶ ስብሃት ነጋ ትልቁ የሙስና ግንድ ከተመታ አንተም ልትመታ መሆንህ በመረዳትህ ነዉ የተድበሰበሰ ትንታኔ የተናገርከዉ። በኔ እምነት ግን በኢትዮጵያ ትልቁ ጠላት ሙስናና ብልሹ አስተዳደር ከግንዱ ብቻ ሳይሆን ከስሩ ከቀበሌ ጀምሮ መቆረጥ አለበት እላለሁ። እዚህ ላይ ግን የስብሃት አሰራር እማውቀዉ ነገር አለ፤፤ ስብሃት በስሙ ገንዘብ ይሁን ንብረት የለዉም። ብዙውን ጊዜም የሆነ ወጭ አይፈርምም ነበር፤፤ ሁሉም ነገር በውክልና ነበር የሚያሰራዉ ። ስለዚህ ትንሽ የሰረቀ ይማር ሲለንም እነዛ ወኪሎቹ እንዳይቆረጡ ካለዉ ስጋት ነዉ። የገንዘቡ ጎተራም ከነሱ ነዉ በስብሃት ወንድሞች ዘርመንዘሩ ስም የተሰሩ ህንፃዎች ምንጫቸዉ የማይታወቅ ሃብትም አላቸዉ።

ሌላዉ ስብሃት ነጋ ስለ ሙስና መረጃ ሲሰጥ ሰሚ ጆሮ አልነበርንም ብለህናል፤፤ ማነዉ የማይሰማ በግልፅነት ልትነግረን አትችልም ማነዉ ለሙስና ጨካኝ ያልሆነ ጠ/ሚኒስቴር? ውጭ ጉዳይ? መከላከያ ሚኒስቴር? የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ? ደረጃ መዳቢዎች? ያገር ውስጥ ገቢ ደህንነት? የከተማ ልማት? የአዲስ አበባ ከንቲባ ዳይሬክተር? እመቤትዋ የጥረት ዳይሬክተር? የወጋገን ዳይሬክተር? የመከላከያ ኢንጅነሪንግ ሚኒስትሮች? የክልል ውሃ ሃብት ኢንተርፕራይዝ ሃላፊዎች ? የስኳር ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር? የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ፓርቲዎች ናቸዉ ታዲያ አቶ ስብሃት ከፍተኛዉ ሙሰኛ ( ትልቁ) ቦታ ነዉ የሚገኘዉ ብለሃል፤፤ ከነዚህ የተኞቹ ናቸዉ ሙሰኞች፤፤ የአቶ ስብሃት አሽሙር አነጋገር 40 አመት ጊዜ ስለፈጀብህ በአንድ አረፍተ ነገር ይቅርና የማያውቅህ እኔም በአስር የሚቆጠሩ አመታት አብረን ተቀምጠን አሽሙርህ ሊረዳኝ አልቻለምና ለዚህ ትውልድ አሽሙር ከምናወርሰዉ ግልፅነትን እናውርሰዉ።

አቶ ስብሃት አንድ ጥያቄ ግን ልጠይቅህ በዚህ ፅሁፍ ላይ ያሰፈርከዉ ለትግራይ ህዝብ ብቻ ታግሎ የሚያታግለዉ መሪ ድርጅት ያስፈልገዋል ብለሃል በሌላ በኩል ደግሞ ህ.ወ.ሓ.ት እናድን ትላለህ እዚህ ላይ ሁለት ነገር እንድመለከት አድርጎኛል።

1ኛ ለትግራይ ህዝብ ብቻ ለምን አዲስ መሪ ድርጅት ያስፈልገዋል ? ተበላሽቶ ያለዉ የኢትዮያ ህዝብ መሪ ነኝ የሚለዉ ህ.ወ.ሓ.ት ኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግ ክህመሙ ካላጋገመ ህ.ወ.ሓ.ት ብቻውን አክመህ ይድናል ወይ ? በሙሉ ተሟል ነውና ወይስ አዲስ የትግራይ መሪ ፓርቲ በመመስረት ወደ ዱሮ የነበርክበት አስተሳሰብ ነፃ ( ትግራይ ትግርኚ) የሰሜን ኢትዮጵያ መንግስት ለመመስረት አስበህ ይሆናል የሚል ጥርጣሬ አድሮብኛል፤፤ አባባልህ ለብዙ ዜጎች የተብራራ እይደለም፤፤ ደግሞ በቅርብ ጊዜ አሜሪካ ሄደህ ኤርትራዊ ነኝ ከማለትህ እጅጉን ተጠራጠርኩህ፤፤

2ኛ ለምን ህ.ወ.ሓ.ት ኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግና አጋሮቹ እናድን ተበላሽተዋልና ብለህ በሃገር ደረጃ ላሉ ጓዶች ችግር ማየት ለምን ተሳነህ ? ወይ የህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች ብቻ ነዉ የታመማችሁት ? አሁን ያለዉ ችግር እኮ የህ.ወ.ሓ.ት ኢ.ህ.ኣ.ዴ.ግ መሪዎች በሙስና መበላሸትና የመበስበስ አደጋ ነዉ አጋጥሟችሁ ያለዉ፤፤ አቶ ስብሃት በጥልቀትና በስፋት ብታስብበት፤፤ በአሁኑ ጊዜ ህ.ወ.ሓ.ት ብዙ ነገር ተበላሽቶባቸዋል፤፤ አንድ እርምጃ ለመራመድ ተስናችሁ በመቃሰት ላይ ናችሁ፤፤ በሰለጠኑ አገሮች እንደምናየው ከሆነ ይቅር እና እናንተ በስብሰባችሁ እንዳላችሁት ስብሰባዉ አንድ ቃል በውሸት ተናግረዉ ህዝብ ካወቃቸዉ ወይ ባገራቸዉ ከባድ ወንጀል ከተፈፀመ ከስልጣን ይወርዳሉ፤፤ እናንተ ግን አገር ያህል የባህር በር የሌላት አስቀርታችሁ የዘሂግ ፍርድ ቤት ውሳኔ ተሸንፋችሁ እያላችሁ አሸንፈናል ውሳኔዉ የኛ ነዉ ብላችሁ በመድረክ ዋሽታችሁ ይሀው ቁማችሁ ትሄዳላችሁ። በተጨማሪ የመላው ህዝብ ተቃውሞ እልባት ለማድረግ አልቻላችሁም፤፤ ይህም ከስልጣን ያወርዳል፤፤ እንደ ጃንሆይ ተጎትታችሁ ከወንበሩ ከምትወርዱ ለምን ይቅርብን ብትሉና ህዝብ የፈለገዉን መሪ ቢመርጥስ ?

ስብሃት ነጋ ከአሁን በኃላ የህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች ከህመማችሁ አገግማችሁ ህ.ወ.ሓ.ት እናድናት ማለትህ የዋህነት ነዉ። ዋና ችግርህ የህዝብን ፍጎትና ልብ ትርታ ኣለመረዳትህና የትግራይ ክልል ህዝብ ከህ.ወ.ሓ.ት መሪዎች የተፋታ መሆኑን አልደረስክበትም፤፤ በሸራተን ሆነህ ስለ የትግራይ ህዝብ ከመናገር እስቲ ወደ ገጠር ህ/ሰብ ስሜቱን አጥና ። እናንተ ህዝቡን ለማደናገር ብላችሁ የምትናገሩትና የምትሰሩት አበጥሮ ያውቃልና።

http://www.zehabesha.com

Norway: Ethiopians demonstrating against the systematic torture of political prisoners in the country

 

Norway (BA) – We demonstrate in order to put pressure on the Norwegian government and the international community, so they can put pressure on the regime in Ethiopia , says EBSS Tesema to BA.

He explains that many of them are asylum seekers from the region of Oromia in Ethiopia , where the systematic injustice taking place.
Ethiopian Norway
WHIPPED AND HUNG

Opposition politicians , journalists and regime critics are subjected to systematic torture at a police station in Addis Ababa , according to a Human Rights Watch report that was presented last week.

The police station is located in the heart of the capital Addis Abbeba in Oromia region .

Torture methods used include blow to the body with hard objects and flogging . Prisoners are also hung from the ceiling in very painful positions, writes Aftenposten.

Merciless

Ethiopia’s ruling party , Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front ( EPRDF ) , has ruled the country for over 20 years. Following the disputed elections in 2005 , the authorities have turned down hard on the opposition.

Anti -terror laws since 2009 have been used to imprison both journalists and dissidents .

It is these conditions Ethiopians in Bergen will have an end.

With banners with slogans like ” Stop the torture of Oromo ” and ” Stop lavishing “, and the use of megaphones , spread the message to people in the downtown streets.

Source – ba.no

– See more at: file:///C:/Users/Eier/Desktop/Norway%20%20Ethiopians%20demonstrating%20against%20the%20systematic%20torture%20of%20political%20prisoners%20in%20the%20country%20%20%20Zehabesha%20%E2%80%93%20Latest%20Ethiopian%20News%20Provider.htm#sthash.g61mhn8M.dpuf

ባለፈው ሳምንት በቦሌ የተከሰተው የቦምብ ፍንዳታ በወያኔ የተቀነባበረ መሆኑ ተረጋገጠ

 

ፖሊስ ምርመራውን አልያዝኩትም የማውቀው ነገር የለም ብሏል::

ባለፈው ኦክቶበር 13 2013 በኢትዮጵያ እና በናይጄሪያ መካከል በአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታ ከመደረጉ ቀደም ብሎ በቦሌ ኡዋንዳ አከባቢ የደረሰው ፍንዳታ ሆን ተብሎ ህዝብን ለማሸበር በወያኔ የተቀነባበረ መሆኑን ሁኔታውን በቅርብ የተከታተሉ የአይን እማኞች ተናግረዋል::

እንደ እማኞቹ መረጃ ከሆነ ከፍንዳታው አንድ ቀን ቀደም ብሎ ቅዳሜ ለሊቱን ከምንሊክ ሆስፒታል ሁለት አስከሬኖች ተዘጋጅተው ወደ ፍንዳታው ሚፈጸምበት ቤት በደህንነት ሃይሎች የተወሰዱ ሲሆን ለዚሁም ስራ ይረዳ ዘንድ ቀደም ብሎ መኖሪአ ቤቱን ከሶማሌ ክልል በደህንነት ሃይሎች ተገዝተው በመጡ ሶማሊዎች እንዲከራዩት ተደርጎ የተዘጋጀ እና የሬሳዎቹን መግባት ተክትሎ ተከራዩ የተባሉት የሶማሌ ተወላጆች ከፍንዳታው ቀደም ብሎ በስውር ወተው ከአከባቢው መሄዳቸው ታውቋል::

ይህንን ዘገባ ያጠናከረው የምርመራ ቡድን እንዳገኘው መረጃ ፍንዳታውን ያቀነባበሩት በሕወሓት የመረጃ ባለስልጣን ደብረጺሆን እና በደህነነት ሹሙ ጌታቸው አሰፋ የሶማሊ ተወላጆችን ቀጥታ ከክልልሉ በመግዛት በሕወሓት ልዩ ስሙ 03 ተብሎ በሚጠራው የደህንነት እና የስለላ ቡድን ስር ፍንዳታው እንዲፈጸም ያደረጉ መሆኑ ተደርሶበታል::

Ethiopoian Review ያነጋገራቸው የአከባቢው የፖለስ ጣቢያ የጸጥታ ሰዎች እና መርማሪዎች ጉዳዩን እንዳልያዙት እና ምንም መረጃ እንዳሌላቸው የተናገሩ ሲሆን የቤቱን ባለቤት ጨምሮ ማንም ሰው ላይ ምርመራ እንዳላደረጉ እና ምንም ማስረጃዎች እንዳሌላቸው ተናግረዋል::

የበለጠ መረጃ እና ከዚህ ቀደም ወያኔ ያደረጋቸውን የሽብር ወንጀሎች ከፈለጉ ይህንን ሊንክ ተጭነው ያገኙታል::

http://www.ethiopianreview.info

የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በውጥረት ላይ ነው – አካባቢው በፌደራል ፖሊስ ተወረረ

(ዘ-ሐበሻ) በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና በመንግስት መካከል የተፈጠረው አለመግባባት እየተካረረ መሄዱ ታወቀ። የሃይማኖት ልብስ ለብሳችሁ ወደ ዩኒቨርሲቲው መግባት አትችሉም በሚል መንግስት በክርስቲያን እና በሙስሊም ተማሪዎች ላይ ባወጣው አዲስ መመሪያ የተነሳ ተናሪዎቹ የምግብ ጥራትን እና ሌሎች ጉዳዮችን አክለው በትምህርት ቤቱ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ እንደነበረ ዘ-ሐበሻ ከቀናት በፊት መዘገቧ ይታወሳል። ዛሬ ከደብረ ማርቆስ በፎቶ ግራፍ ተደግፎ በደረሰን መረጃ መሰረት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ የሚገኝ ሲሆን የትምህርት ቤቱ አካባቢም በፌደራል ፖሊሶች ተወሯል። ፎቶቹ የሚከተሉት ናቸው። ዝርዝሩን ተከታትለን እንዘግባለን።

polci polcei

“ኢህአዴግ፤ የምትቃወሙትንም እኔ ነኝ የምሰጣችሁ እንዳይለን” – ተቃዋሚዎች

“ኢህአዴግ፤ የምትቃወሙትንም እኔ ነኝ የምሰጣችሁ እንዳይለን” – ተቃዋሚዎች

Written by  ኤልያስ

        “የኢህአዴግን የሥልጣን ዘመን አጭበርብረሃል” የሚል ወቀሳ ደርሶብኛል “ሥልጣን ለኢህአዴግ የምርጫ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው!” ውዲቷን ኢትዮጵያ ላለፉት 12 ዓመታት በርዕሰብሔርነት የመሯት (ወይስ መራቻቸው?) የ90 ዓመቱ አዛውንት ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ፤ ከጥቂት ቀናት በኋላ ሥልጣናቸውን በአደራ ለሰጣቸው ኢህአዴግ አስረክበው ከቤተመንግስት በመውጣት ኢህአዴግ ወዳዘጋጀላቸው መኖርያ ቤት ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። “ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ይደረጋል” ሲባል ሰማሁ ልበል? ወይስ ጆሮዬ ነው? (ጆሮዬ በሆነ!) ለምን መሰላችሁ? መቼም እሳቸው ከሥልጣን አልወርድም ብለው ከኢህአዴግ ጋር ሙግት ሊገጥሙ አይችሉም። ይሄማ ውለታ ቢስ መሆን ነው። እናላችሁ —- “ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር” ከሚለው ይልቅ “ሰላማዊ የሥልጣን እርክክብ” ቢባል የተሻለ ሳይሆን አይቀርም የሚሉ ወገኖች አሉ። በነገራችሁ ላይ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በሥልጣን ዘመናቸው ከህመማቸው በቀር በሌላ በሌላው እድለኛ ናቸው ማለት ይቻላል። እንዴት ብትሉ—- ስንቱ ቱባ ቱባ የኢህአዴግ ሹማምንት በጋዜጠኞች ሲሞለጩና ሲተቹ፣ በፓርቲያቸው ሲገመገሙና “ሂሳችሁን ዋጡ” ሲባሉ፤ እሳቸው ግን ለ12 ዓመት እንደተከበሩ ኖረዋል። (ከተሳሳትኩ እታረማለሁ!) የፕሬዚዳንቱ አማካሪ አቶ አሰፋ ከሲቶ፤ “ውጤታማና እድለኛ ናቸው” ያሉት ለዚህ ይሆን እንዴ? በእርግጥ አልተሳሳቱም፤ሰውየው እድለኛ ናቸው። ባለቀ ሰዓት ግን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ባልሾመ አንጀታቸው የትችት መዓት አወሩዱባቸው እንጂ።

ባለፈው ሳምንት በዚሁ ጋዜጣ ላይ ስለፕሬዚዳንቱ የ12 ዓመት የሥልጣን ዘመን አስተያየት የሰጡ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችና ምሁራን በአንድ ድምፅ “ውጤታማ አልነበሩም” ብለዋቸዋል። እኔ ፕሬዚዳንቱን ብሆን (ምኞት እኮ ነው!) ምን እንደምል ታውቃላችሁ? “የእኔን እድል ይስጣችሁ” (እርግማን እኮ አይደለም!) “እንደእኔ ፕሬዚዳንት ሆናችሁ እዩት” ለማለት ነው። ልክ ነዋ! ኢህአዴግ በፕሬዚዳንትነት የሾመው ሰው ያለው ሥልጣንና ሃላፊነት የቱ ድረስ እንደሆነ ሳያውቁ እኮ ነው ተመቸን ብለው የሚናገሩት። ኢህአዴግ የሾመው ከኢህአዴግ ፍላጎት ውጭ ተዓምር እንዲሰራ መጠበቅ “ፌር” አይደለም። (በኢህአዴግ ደግሞ ትግል እንጂ “ተዓምር” መስራት አይፈቀድም!) ከፓርቲው አፈንግጦ ተዓምር ለመስራት የሚወራጭ ካለም የቀድሞው ፕሬዚዳንት የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ዓይነት እጣ ፈንታ ይገጥመዋል። ከቤተመንግስት ወጥቶ ጣራው የሚያፈስ የኪራይ ቤቶች ቤት ውስጥ ይገባል።

ይሄም ታዲያ እጁን ከፖለቲካ ሰብስቦ ከተቀመጠ ብቻ ነው። ነጋሶ ግን እጃቸውን ሰብስበው አልተቀመጡም። በግላቸው በምርጫ ተወዳድረው በማሸነፍ ፓርላማ ገቡ። ራሴ ባረቀቅሁት ህገመንግስት ውስጥ የሰፈረውን ፖለቲካዊ መብቴን ከማስወስድ የሚያፈስ ቤታችሁን ውሰዱልኝ አሉ። (“የነጋሶ መንገድ” በሚለው መፅሃፋቸው እንደነገሩን) በነገራችሁ ላይ ፕሬዚዳንት ግርማ “ውጤታማ አልነበሩም” የሚለውን የተቃዋሚዎች ትችት እየተቃወምኩም ሆነ እየደገፍኩኝ አይደለም። (“አይቻልም ወይ መኖር የማንም ሳይሆኑ” ያለችው ድምፃዊት ማን ነበረች?) እኔ ግን ጥያቄ አለኝ – በፕሬዚዳንቱ ላይ በተሰነዘሩት አስተያየቶች ዙሪያ። ፕሬዚዳንቱ ይሄን ሁሉ ዘመን ኖረው ኖረው ከቤተመንግስት ሊወጡ አንድ ሐሙስ ሲቀራቸው “ውጤታማ ነበሩ? አልነበሩም?” የሚለውን የጦፈ ሙግት ምን አመጣው? ምናልባት ኢህአዴግ አዲስ ለሚሾመው ፕሬዚዳንት ይጠቅም እንደሆነ እንጂ ለተሰናባቹ እኮ የሚተርፋቸው ፀፀት ብቻ ነው። (The damage is already done! አለ ፈረንጅ) እውነቱን ለመናገር— ተቃዋሚዎች ስለፕሬዚዳንቱ የሰጡት አስተያየት የድሮ ተረት ከማስታወስ ያለፈ ፋይዳ አለው ብዬ አላስብም (“ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ” አሉ) የሚገርመው ደግሞ ከአስተያየት ሰጪዎቹ መሃል ጠንካራና ደካማ ጎኖቻቸው ወይም ስኬትና ውድቀታቸው ብሎ ከፋፍሎ ለማየት አንድ እንኳን የሞከረ የለም። ተቃዋሚዎቹ “የማርያም ጠላት” ያደረጓቸውን ያህል በፓርላማ የኢህአዴግ ደጋፊና ብቸኛው የግል ተመራጭ ዶ/ር አሸብርም እንከን የሌለባቸው ፍፁም ፕሬዚዳንት አድርገው ነው ያቀረቧቸው። (“ወልደህ ሳትጨርስ—”የሚለው ተረት ትዝ ብሏቸው ይሆን?) የፕሬዚዳንት ግርማ አማካሪ አቶ አሰፋ ከሲቶ እንኳን የቱንም ያህል መላዕክ ቢያደርጓቸው አይፈረድባቸውም (ሥራቸው ነዋ!) እኔ ተቃዋሚዎችን ብሆን ግን ትችቴን አንድም ኢህአዴግ ላይ አሊያም የፕሬዚዳንቱን ሥልጣን በገደበው ህገመንግስቱ ላይ ነበር የማነጣጥረው።

(“አህያውን ፈርቶ ዳውላውን” አሉ!) እኔ የምለው ግን— ጀግናው አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ በፕሬዚዳንት ግርማ ላይ የወረደውን የትችት ውርጅብኝ ሰምቶ ይሆን? ከሩጫ በኋላ ፕሬዚዳንት የመሆን ፍላጎት አለኝ ስላለ እኮ ነው! (ፍላጎት ነው ምኞት?) በኋላ ከሚቆጨኝ ለአትሌታችን ምክር ቢጤ ጣል ባደርግለት ደስ ይለኛል። ለፖለቲካ ዲሲፕሊንና ልምምድ ብቻ በቂ አይደሉም። (ሩጫና ፖለቲካ ለየቅል ናቸው!) እንግዲህ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ባለፉት 12 ዓመታት ሰሩም ተባለ አልሰሩ በቅርቡ ከሥልጣናቸው ይሰናበታሉ። ከወር በፊት ይመስለኛል— ፕሬዚዳንቱ ከ“ሚት ኢቲቪ” አዘጋጅ ተፈራ ገዳሙ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፣ ለሁለተኛ ጊዜ ሲመረጡ የፍርሃት ስሜት አድሮባቸው እንደሆነ ጠይቋቸው፣ በመጀመርያው ጊዜ እንጂ በሁለተኛው ምንም ዓይነት ፍርሃት እንዳልተሰማቸው ገልፀው፣ለሦስተኛ ዙር በፕሬዚዳንትነት መቀጠል አለመቻሉ ትንሽ እንደሚያናድድ ተናግረዋል – በቀልድ መልክ። (ከአንጀታቸውም ሊሆን ይችላል!) ግን አያችሁልኝ— የኢህአዴግን ምስጢር ወዳድነት። እስካሁን እኮ ቀጣዩ ፕሬዚዳንት ማን እንደሚሆን ፍንጭ እንኳ አልሰጠንም። (ኢህአዴግ “ሰርፕራይዝ” ማድረግም ነፍሱ ነው አሉ!) እናላችሁ— ችግር የለም፤ ቀኑ ሲደርስ አዲሱን ፕሬዚዳንት በፓርላማ አቅርቦ ሰርፕራይዝ ይለናል – እንደ ልደት ስጦታ (ስጦታውስ ለኛ ሳይሆን ለተሿሚው ነው!) ባለፈው ሳምንት “ታጋይ ደከመኝ አይልም እንጂ ኢህአዴግ ድክም ብሎታል” በሚል ርዕስ ያቀረብኩትን ፅሁፍ ያነበቡ አንድ ደንበኛ ስልክ ደውለው እንዴት እንደወቀሱኝ አልነግራችሁም። ወቀሳው ምን መሰላችሁ? “የኢህአዴግን የሥልጣን ዘመን አጭበርብረሃል” የሚል ነው። በመቆርቆር ግን አይመስልም፤ “23 ዓመት አንቀጥቅጦ ገዝቶን እንዴት 21 ዓመት ብቻ ትላለህ? ሁለቱን የት ደብቀህለት ነው?” ነበር ያሉኝ።

እኔ እንኳን መደበቄ አልነበረም። ሁለቷ ዓመት የልምምድ ጊዜ ናት ብዬ ነበር የተውኳት (ለካስ ሂሳብ ማወራረድ ተጀምሯል!) እኔ ግን 30 እና 40 ዓመት የመግዛት ራዕይ ላለው ፓርቲ ገና ወገቡ ላይ ሆነን ሂሳብ መተሳሰብ ፋይዳው አልታየኝም። ባይሆን 30ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ ሲገባ የሥልጣን ዘመኑን መቆጣጠር እንጀምራለን፤ አሁንማ ምን ተነካና። በነገራችሁ ላይ — ኢህአዴግ የሥራ ብዛትና ጫና ስላደከመው ከመውደቁ በፊት የአንድ ዓመት እረፍት ይውሰድ በሚል ያቀረብኩትን ሃሳብ አብዛኞቹ የኢህአዴግ አባላት ክፉኛ እንደተቃወሙትና እንዳወገዙት ሰምቻለሁ – “ታጋይ አይደክመውም” በማለት። ከዚህ ሃሳቤ የማልታቀብ ከሆነም በቅርቡ የተቃውሞ ሰልፍ ለመውጣት እንደዛቱብኝ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ሹክ ብለውኛል። ከሁሉም የገረመኝ ግን ምን መሰላችሁ? አንዳንድ የኢህአዴግ ካድሬዎች በእኔ ላይ ለሚደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ገና ካሁኑ መፈክሮች ማዘጋጀት መጀመራቸው ነው። (የሰልፍ ፈቃድ ሳያገኙ?) እስቲ ከመፈክሮቹ ጥቂቶቹን እንያቸው – “ኢህአዴግ ደክሞታል በሚል ማደናገርያ ሥልጣን በአቋራጭ መያዝ የህልም እንጀራ ነው!” “ሥልጣን ለኢህአዴግ የቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው!” “ኢህአዴግ አረፍ እንዲል የሚፈልጉት የኒዮሊበራል ተላላኪዎች ናቸው!” እኔ ግን እንደነሱ አይደለሁም።

ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ቀንደኛ አቀንቃኝ ስለሆንኩ በዛቻውም ሆነ በመፈክሮቻቸው ቅያሜ አላደረብኝም። እንደውም ያለውዝግብ የሰላማዊ ሰልፍ ፈቃድ ካገኙ ከእነሱ ጋር ሰልፍ ለመውጣት ሁሉ አስቤአለሁ – ተቃውሞው በእኔ ላይ ቢሆንም። ከገዢ ፓርቲ ጋር ተቃውሞ ሰልፍ ማድረግ ምን ዓይነት ስሜት እንደሚፈጥር ማወቅ እፈልጋለሁ (ለጠቅላላ እውቀት እኮ ነው!) በዚያ ላይ ተቃዋሚዎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሚጠሩት በእያንዳንዱ ሰልፍ ከአዲስ አበባ መስተዳድር ፈቃድ ክፍልና ከፖሊስ ጋር የሚጋቡትን እልህና ውዝግብ ሰበብ ለማወቅ እፈልጋለሁ። ኢህአዴግስ ተመሳሳይ ውዝግብና እልህ ውስጥ ይገባል ወይስ ነገሩ አልጋ በአልጋ ይሆንለታል? (የባለቤቱ ልጅ መሆኑ እኮ አልጠፋኝም!) ይሄን ሁሉ የመፈተሽና የማጥናት ፍላጎት አለኝ። ስፖንሰር ተደርጌ እኮ አይደለም። (የሃገሬ ጉዳይ አያገባኝም እንዴ?) ባለፈው እሁድ ሰማያዊ ፓርቲ በመስቀል አደባባይ ሰልፍ ለማድረግ ጠይቆ፤ ቦታው በኮንስትራክሽን ሥራ ላይ እንደሆነና “ለልማት ነው ቅድምያ የምንሰጠው” የሚል ምላሽ እንደተሰጠው ገልጿል።

በዚሁ ሰበብ ፖሊስ ከቢሮው ንብረቶች እንደወሰደበት እንዲሁም እሁድ እለት ሰልፉን ሊያካሂዱ ሲሉ መንገድ በመዝጋት ሰልፉን እንዳቋረጠባቸው ፓርቲው በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። አንድነት ፓርቲም በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ጠይቆ፤ ሌላ አማራጭ ቦታዎች አቅርብ ከተባለ በኋላ ያቀረበው ሁሉ ውድቅ ሆኖ ሰልፉን ጃንሜዳ አድርግ እንደተባለ አስታውቋል። በዚሁ ሰሞን ሰላማዊ ሰልፍን የሚገድብ አዲስ መመሪያ ከአዲስ አበባ መስተዳድር መውጣቱን የሚናገሩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ የተቃውሞ ሰልፉ የሚደረግበትን ቦታና ጊዜ የሚወስነው መስተዳድሩ እንደሆነ ጠቁመው፤ “አሁን የቀራቸው የምትቃወሙትንም የምንሰጣችሁ እኛ ነን” ማለት ብቻ ነው ሲሉ ክፉኛ አሽሟጠዋል። አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊ አዲስ ወጣ በተባለው መመሪያ ተናዶ ምን እንዳለኝ ታውቃላችሁ? “እንደዚያ ከሆነማ ለምን ሰልፍ የሚወጣውንም ህዝብ እነሱ አይመድቡልንም?” በአሁኑ ጊዜ ኢህአዴግ የተቃዋሚዎች ሰልፍ በጣም አስፈርቶታል የሚለው ይሄው የተቃዋሚ ደጋፊ፤ “በመኪና ለመቀስቀስ፣ ፖስተር ለመለጠፍ፣ በራሪ ወረቀት ለመበተን፣ ወዘተ— ለሁሉ ነገር አስፈቅዱኝ እያለ ነው፣ ለምን መፈክሮቹንም እሱ አያዘጋጅልንም” በማለት አዲስ የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ለገዢው ፓርቲ አበርክቶለታል። “እናም ኢህአዴግ በቅርቡ “ሰላማዊ ሰልፍ እናዘጋጃለን፣ የተቃውሞ አጀንዳዎችን እንቀርፃለን፣ ለሰልፍ የሚወጣ ህዝብ እንመለምላለን፣ በራሪ ወረቀቶችን እናዘጋጃለን፣ የተቃውሞ ሰልፍ ቅስቀሳ እናደርጋለን ወዘተ– የሚል ልዩ ማስታወቂያ በኢቴቪ ሲያስተላልፍ ልንሰማ እንችላለን” ብሏል – የተቃዋሚ ደጋፊው። (ግን ወዴት እየሄድን ይሆን? ለሁሉም የቀረበ ወቅታዊ ጥያቄ ነው!)

http://addisadmassnews.com