ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ – አለበለዚያ…

 

መላኩ ገለታ (ፈልማ ዱጋ)

Power outage hits while Hillary Clinton gives a speech at the African Union in Addis Ababa

Power outage hits while Hillary Clinton gives a speech at the African Union in Addis Ababa  – June 13, 2011

(በእኔ ግምት የእመቤት ክሊንተን መልዕክት ለአፍሪካ-በተለይ ለኢትዮጵያ)

እመቤት ክሊንተን ከሰሞኑ ወደ «መከረኛዋ» አፍሪካ ብቅ ብለው አሜሪካ ለአፍሪካ ያላትን ዕልም ጆሮ ያለው ይስማ በሚለው ቢሂል መሰረት ለአፍሪካ መሪዎች በጥቅሉ ለአፍሪካ ሕዝቦች ደግሞ በዝርዝር አድርሰው በመጣ እግራቸው ተመልሰው ሄደዋል፡፡ ከዚህ በፊት ታንዛኒያ እና ዛምቢያ ነበሩ፡፡ ደስ የሚል ግዜ ማሳለፋቸውን መስክረዋል፡፡

የዛሬው የኔ ብዕር አመጣጣቸውን እና አካሄዳቸውን በማካተት በዝርዝር ቁም ነገሮች ዙሪያ ያተኩራል፡፡ ሂላሪ ለአፍሪካ መሪዎች ምን የተሰኙ የተስፋ ቃሎች ተናገሩ? ምን በተሰኙ ጉዳዮች ዙሪያ የአሜሪካን መንግስት አቋም ግልፅ አደረጉ? አሜሪካ ምን በተሰኙ ጉዳዮች ዙሪያ የአፍሪካ መንግስት ላይ ተስፋ መቁረጧም አስታወቁ? እና የመሳሰሉትን እናያለን፡፡ በተለይ ደግሞ በተናጠል ኢትዮጵያን የሚመለከቱ ጉዳዮችን ከእመቤት ክሊንተን መልዕክት አንፃር እንፈትሻለን፡፡ የኢንተርኔት እና የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ተጠቃሚ ኢትዮጵያዊ ቁጥር ከጠቅላላው ሕዝብ ውስጥ ከ3 በመቶ በታች በሆነ አገር «ነገሩን ከፈረሱ አፍ» በሚለው ብሂል መሰረት ከእመቤት ክሊንተን አንደበት እንደወረደ የሰማውትን ለተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ማድረስ የዚህ ፅሑፍ ዋነኛ አላማ ነው፡፡ ከውዥንብር የፀዳ የአሜሪካን መንግስት አቋም ማወቅ በተለይ በዚህ ወሳኝ ወቅት እጅግ እጅግ ጠቃሚ ብሎም አስፈላጊ ነው፡፡

መነሻ

እመቤት ክሊንተን ወደ አፍሪካዋ መዲና ብቅ ያሉበት ወቅት ከዓለም የፖለቲካ የኢኮኖሚ የሰብዓዊ መብት እና የዲሞክራሲ ስርዓት መመሰቃቀል አንፃር ወሳኝ የሆነ ወቅት ነው (high time) በእሳቸው አገላለፅ ( Arab spring) የአረብ አለም አብዮት እየተንቀለቀለ ያለበት ሰዓት ነው፡፡ ይህ ወላፈን ወደ አፍሪካ እና ወደተቀረው ዓለም የተሻገረ ለመሆኑ «የአፍሪካ መሪዎችን» ሳይደብቁ ነግረውልናል፡፡

መልዕክት 1

ይህ ወቅት ለአፍሪካ መሪዎች በተለይም ደግሞ አምባገነን መሪዎች መንቃት አለባቸው ብለዋል፡፡ አሁንም በእሳቸው አገላለፅ «በየትኛውም መልኩ በዲሞክራሲ መስፈርት ውጭ ስልጣን ላይ ሙጭጭ ያሉትን ሚስኪን ሕዝቦቻቸውን ያሳቀቁ በድህነት ውስጥ መኖር ጥበብ የተካኑትን በደሃ ሕዝቦች ሐብት ራሳቸውን፤ ቤተሰባቸውን እና የአላማ ተጋሪዎቻቸውን የናጠጡ ሚሊየነሮች ያደረጉትን» በማለት ለእንደዚህ መሰሎች መሪዎች የአሜሪካ መልዕክት አንድ እና አንድ ነው ብለዋል፡፡ «ይህንን ታሪካዊ የሕዝቦች ለውጥ የመሻት እንቅስቃሴ መረዳት ከተሳናቸው በያዛችሁት መንገድ በመቀጠል የገዛ ሕዝባችሁን እያወረዳችሁ ለመጓዝ ከወሰናችሁ አስረግጬ እነግራችኋለሁ አሁን በታሪክ ፊት በተሳሳተ ጎዳና ላይ ናችሁ በማለት መንግስቴ ያምናል፡፡ ብትቀበሉትም ባትቀበሉትም አሉ በማከል አሜሪካ ሳትሆን መጪው ግዜ ያረጋግጥላችኋል፡፡»

መልዕክት 2

እመቤት ክሊንተን በዚህ ንግግራቸው ውስጥ አሜሪካ ከተረገጡ ከተጨቆኑ በአምባገነን አገዛዝ ግራ የተጋቡ ሕዝቦች ጎን መቆሟን አምባገነን የአፍሪካ መሪዎች ፊት የመሰከሩት «በሞቅ» መንፈስ ውስጥ ሆነው አልነበረም፡፡ (በሞቀ መንፈስ ውስጥ ሆነው አምባገነን መሪዎች የሚናገሩትን ቅጥ አምባሩ የጠፋበትን ንግግር ልብ ይሏል) እመቤት ክሊንተን ግን አምባገነን የአፍሪካ መሪዎች አይናቸውን በጨው አጥበው በስልጣን ላይ የሚቆዩበትንና ሊቆዩ የሚጠቀሙበትን ስለልት ቁና ሙሉ የአፍሪካ አምባገነን መሪዎች በሚገኙበት በሚከተለው መንገድ ገልፀዋል፡፡ «ዲሞክራሲ ማለት በአሜሪካ እምነት አንድ ነጠላ ምርጫ ማካሄድ ማለት አይደለም ካሉ በኋላ ምርጫ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ግን በቂ ነው ብሎ መንግስቴ አያምንም፡፡ ከምንም በላይ የመልካም አስተዳደር መገለጫ የሆኑት ነፃ፤ ገለልተኛና ግልፅ የሆነ የምርጫ ስርዓት መኖር አለበት፡፡ ነፃ የሚዲያ አገልግሎት በተግባር መታየት አለበት፡፡ ገለልተኛ የሆነ የፍትሕ ስርዓት ተዋቅሮ የተግባር ስራውን ሲያከናውን መታየት አለበት፡፡ ብዙሃኑም ሆነ አናሳው የሕብረተሰብ ክፍል ተገቢ ከለላ ሕገመንግስታዊና ዲሞክራሳዊ ጥበቃ ሊደረግለት ይገባል፡፡ ዲሞክራሲ በዚህ ብቻ አያልቅም ብለዋል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ የሚያልፈው ሕዝብ የኢኮኖሚ ደረጃ መሻሻል አለበት፡፡ ሥራ ሊኖረው ይገባል፡፡ የመኖር ዋስትናው የተረጋገጠ እና ቀጣይነት ያለው መሆን አለበት፡፡» በማለት ፍርጥ አድርገው ተናገሩ፡፡

መልዕክት 3

እመቤት ክሊንተን በአፍርካ የዲሞክራሲእና የልማት መርዕዎች ላይ ጨለምተኛ አልነበሩም፡፡ ከዲሞክራሲ አንፃር ቦትስዋናን፣ ጋናን፣እና ታንዛኒያን ጠቅሰው በሞዴልነት አወድሰዋቸዋል፡፡ እነዚህ የአፍሪካ ተምሳሌትነታቸው ብቻ ሳይሆን በዓለም ተምሳሌትነታቸው ተከተሏቸው ብለዋል፡፡ ከተከተሉት እና ውጤታማ ከሆነው የልማት እና የዕድገት መርህ አንፃርም ዛምቢያን፤ ማሊን፤ ጋናንና ሩዋንዳን አወድሳለሁ፡፡ ልብ በሉ ከ50 በላይ የአፍርካ መሪዎች ከተገኙበት መደረክ የአፍሪካ ዲሞክራሲ እና ልማት በዚህ መልክ ተወራርዷል፡፡ ይህ በአፍሪካ አገሮች አገዛዝ ላይ አንድ ዓመት፤አምስት ዓመት ፤አስር አመት፤ ሃያ ዓመት እና ከዚህ በላይ በሥልጣን ላይ ለቆዩት ሁሉ ትርፍ እና ኪሳራቸው የተወራረደበት ታላቅ ትዕይንት ነበር፡፡

መልዕክት 4

እመቤት ክሊንተን ከዚህ ማወደስ ጎን ደግሞ ጥቂት ያሏቸውን (ምንአልባትም ተለይተው ለታወቁ አምባገነን መሪዎች) የሚከተለውን እውነት ፍርጥ አድርገው ነግረዋቸዋል፡፡ እንዲህ ነበር ያሉት፤«አንዳንዶች ደግሞ በዲሞክራሲ ያምናሉ ካሉ በኋላ ለእነዚህ ዲሞክራሲ ማለት አንድ ምርጫ ማካሄድ ማለት ነው፡፡ በቃ! ከዚህ በኋላ ላልተወሰነ ዓመት በሥልጣን ላይ መቆየት! ለእነዚህኞቹ ቁርጥ ያለውን የመንግስታቸውን አቋም ያረጋገጡት ይህ አካሄድ በዓለም ላይ በዚህም በዚያም ተቀባይነት እያጣ መምጣቱን በመንገር ነበር፡፡» እናንተኞቹ መሪዎች እንቅልፍ ላይ ካልሆናችሁ በስተቀር በሰሜን አፍሪካ ውስጥ ተቀጣጥሎ ወደእያንዳንዳችሁ አገር እየገባ ያለውን ለውጥ የመሻት ነውጥ፣ ትንቅንቅ እና ንቅናቄ ሌላ ሳይሆን ሕዝቦች  በረዥም ዓመት የአነባገነን አገዛዝ ስር ተጠፍረው ተይዘው ከዛ ለመላቀቅ የሚያደርጉት ክብር የምንችረው የተፈጥሮን ግዴታ ለመወጣት የሚደረግ ትግል ነው፡፡ ይህ ማለት ሕዝቦች ከጨቋኝ ገዚዎች ለመላቀቅ እየታገሉ ነው ማለት ነው፡፡ በተረፈ የተቸራቸውን የመናገር መብት ይፋ ለማውጣት የፀጥታን ዘመን ለመስበር የጀመሩበት ወቅት ነው፡፡ ጥቂቶች ቤተሰባቸውን እና ወገኖቻቸው ተንደላቀው በሚኖሩባት አገር ብዙሃኑ የበይ ተመልካች ሆኖ ለመቀጠል ይፈቅዳሉ ብሎ ማሰብ ሲበዛ አምባገነንነት ሲያንስ ደግሞ ተላላነት ነው፡፡ ፍርጥ አድርገው ሲናገሩ እናንተ አምባገነኖች አስተውሉ የእነዚህ ሕዝቦች መልዕክት አንድ እና አንድ ብቻ ነው፡፡ ካሉ በኃላ እየተላለፈ ያለው መልዕክት«አሮጌው ዘመን አልፏል ከዚህ በኋላ ከቶም ሊሰራ ይችልም»«The «status quo is broken» ስለዚህ አሉ እመቤት ክሊንተን ዘመኑ ጠልቷችኋል ሕዝቦች አልተቀበሏችሁም እናም  « it is time for them to go » አሁን ሂዱ፡፡ ስፍራውን ልቀቁ ብለዋል፡፡

መልዕክት ለኢትዮጵያ፡፡

መቼም እመቤት ክሊንተን በኢትዮጵያ ምድር እና በኢትዮጵያን ጓዳ እና ጎድጓዳ ውስጥ የታጨቀውን የተፈፀመውን የአጥያት ዓይነት በአፍሪካ ጉባኤ አዳረሽ፤ በአፍሪካዊያን መሪዎች ፊት እያጣቀሱ ይንገሩን ብለን ሙጭጭ እንደማንል እሙን ነው፡፡ ከንግግራቸው ውስጥ ግን የራሳችንን ጉዳይ ፈልጎ ማግኘት፤ አድኖ የመልቀም ኀላፊነት የራሳችን መሆን አለበት፡፡ ይህን ያህል ተጉዘው መጥተው  እንዴት እና ምን እንዳሰቡ ከነገሩን (ክብር የኦባማ አስተዳደር እንዲሁመ፣ ክብር ለእመቤት ክሊንተን ) «አንድ ለእናቱ» የሆነው የኢትዮጵያ ቴሌቭዢን፤ የኢትዮጵያ ሬዲዮእና የኢትዮጵያ ኤፍ ኤም ከቶውንም ያልተባለውን ተብሏል ብለው ሊያጭበረብሩን አይችሉም፡፡ ለዚህ የሚዲያ ተቋምም «status quo is broken» የተባለው ሊነገረው ይገባል እላለሁ፡፡ እመቤት ክሊንተን ግን አንድ ተልዕኮ ከዳር አድርሰው መመለሳቸውን የአገሬ ሕዝን ልብ ይል ዘንድ እጠይቃለሁ፡፡ እሳቸው «በቮልካኖ ይሳበብ በአርጃኖ» ከአሜሪካ መንግስት የተሰጠ መግለጫ ስላልነበረ ማለቴ ነው፡፡ በሻንጣው ወደ አውሮፕላናቸው ወደ አየር ውስጥ ከገቡ በኃላ «ማኙ ፓርላማችን በሽብረውተኞች ላይ ያወጣውን የአዲስ ሕግ ቅላፄ እያሰላሰልን የእመቤት ክሊንተን መልዕክቶችን በግልባጩ ማዳመጥ የእኛ ጉዳይ መሆን አለበት፡፡» ለምን የእሳቸውን ንግግር ተከትሎ አዋጁ ታወጀ ብላችሁ አትጠይቁኝ ፡፡ ለዚህ መልስ የለኝም፡፡

እንደ እውነቱ ከሆነ በየኔ የግል ትንታኔ  ደረጃ  የእመቤት ክሊንተን መልዕክት እና የኦባማ አስተዳደር አቋም ከአቶ መለስ ዜናዊ መንግስት እና ከፓርቲያቸው አቋም ጋር (መለስ ስለራሳቸው  መንግስታቸው ስለራሱ) ካለው ግምቴ አንፃር እምብዛም የሚጣጣም ሆኖ አላገኘሁትም፡፡ (የኢትዮጲያ ቴሌቪዢን ገፅታን ለማሳመር ካደረገው ጥረት ባሻገር ያለውን እውነት በዝርዝር እንፈትሽ)

ፍተሻ 1

«status quo is broken» ይህ ምን ማለት ነው ለአቶ መለስ አስተዳደር፡፡ አቶ መለስ 20 ዓመት ሙሉ «የዲሞክረሲ ምርጫ» አድርጌአለሁ በማለት ያምናሉ፡፡ በአንፃሩ በዓለም አቀፍ የምርጫ መስፈርት መሰረት የአቶ መለስ አገዛዝ ያካሄደው ሁሉም ምርጫ አንዴም እሰይ አልተባለም፡፡ ተጭበርብሯል፤ ፍትሃዊ አልነበረም፤ ሥርዓቱ የተዋቀረው አቶ መለስን እና አገዛዛቸውን በስልጣን ላይ ለማቆየት ነው ተብሎ በካርተር ማዕከል ፤በአውሮፓ ሕብረት፤ በሲቪክ ማዕበራት ተወካዮች፤ የአምነስቲ እንተርናሽናል፤የሂውማን ራይትስዎች፤ወዘተ ከበቂ በላይ ተብጠልጥሏል፡፡ በዚህ ሁሉ ሂደት ሺዎች ታስረዋል፤ተገድለዋል፤ ከአገር ተሰደዋል፡፡ በምርጫ እና በምርጫ ዙሪያ፡፡ እንግዲህ የኢትዮጵያ ሕዝብ ባልመረጣቸው ገዢዎች አገዛዝ ስር ለመቆየት ዋና ምስክር ነው፡፡ «እንዳለመታደል ሆኖ» እመቤት ክሊንተን በአፍሪካ ሕብረት አዳራሽ ፊት ቆመው ስለዲሞክራሲ ሲመሰክሩ ኢትዮጵያን እና የአቶ መለስን አገዛዝ በሞዴልነት አልጠቀሱም፡፡ ከዚህ ጋር አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ ምርጫ ላይ የተሳለቁትን ስላቅ ብጠቅስ የበለጠ የሚያብራራ ይመስለኛል፡፡ «ኢትዮጵያ ምርጫ ታደርጋለች፤ ለምርጫ ገንዘብ እና ወረቀት አባክናለች የሰዎችንም ግዜ እንዲሁ ይህ ሁሉ ሆኖ መለስ ሃያ ዓመት በስልጣን ላይ ላይ ቆይቷል፡፡ ኤርትሪያ ምርጫ አታካሂድም ገንዘብ እና ወረቀት አታባክንም የሰዎችንም ጊዜ እንዲሁ ይህ ሁሉ ሆኖ ሃያ ዓመት በስልጣን ላይ ነኝ፡፡ ታዲያ ልዩነቱ የት ላይ ነው? አሉ የተባለውን ለማለት ነው፡፡ በእርግጥ የኤርቲሪያ አምባገነን አገዛዝ ቢያንስ «አትራፊ» እንደነበር መገመት ይቻላል፡፡ እመቤት ክሊነተን በስልጣን ላይ  የመቆየት አባዜ ሕዝቦች መጠየፋቸውን፤ በዚህም ሳቢያ ሕዝቦች ለፍትሕ የሚደርጉትን ትግል መንግስታቸው ለመደገፍ መወሰኑን ሱያሰምሩበት ነው፡፡ « it is time for them to go »  ያሉት፡፡ ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡

ፍተሸ 2

ከአሁን በፊት ሃሞት በሚሰልብ መልኩ፤ በምሁራኖቻቸን እና በፖለቲካ ፓረቲዎቻችን ጭምር አግድም እየተተረጎመ ይነገር የነበረው የኢትዮጵያ እና የአሜሪካን ወዳጅነት ሽብርተኝነትን በመከላከል ረገድ» በዚህ ፍተሻ ሁለት ስር በተን አድርጎ መመልከቱ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ በዚህ በእመቤት ክሊንተን ተልዕኮ ውስጥ የአቶ መለስ መንግስት በተለይ ደግሞ አቶ መለስ የመሪነት ሚናቸውን ጎላ አድርገው ለማሳየት ሃያ አመት ሙሉ የደከሙላቸው የንዑስ አእጉራዊ ድርጅቶች ሚስጢር ከፍተን እናያለን፡፡ እንደ ሰንዓ ትብብር ፎረም ፤እንደ ኢጋድ ፎረም፤የመሳሰሉትን ለማለት ነው፡፡ እንዚህ ሁለቱ ድርጅቶች እና መሰሎቻቸው በአቶ መለስ እና በየግዜው የሚለዋወጡት መሪዎች አማካይነት የረባ አስተዋፅኦ እንዳልነበረው (ዲሞክራሲ ለማስፈን፤ልማትን ለማምጣት እና አእጉራዊ ትብብርን ለማረጋገጥ) ለማለት ነው፡፡ ኢጋድና የሰንዓ ፎረም ትብብር ሲታወሱ በዓለም ፍርድ ቤት በወንጀለኛነታቸው የሚፈለጉት የሱዳኑ መሪ አልበሽር፤ በሕዝብ የተጠሉት ሌላው የየመኑ አብደላህ ሳላህ ይወሳሉ፡፡ እነዚህ መሪዎች በአገራቸው ዛሬም ሰው ይገላሉ፡፡ ዛሬም ሰው ያስራሉ፡፡ መለስ ለእነዚህ መሪዎች ጓደኛ ብቻ ሳይሆኑ የእነዚህ የጥቃቅን ንዑስ አህጉራዊ ድርጅቶች መሪም ሆነው ሰርተዋል፡፡ «የኢትዪጵያን ጦር » ከአገር አገር በማንከራተት ተልዕኮውን ይወጣ ዘንድ እረፍት በማጣት ሰርተዋል፡፡ በሱማሊያ ውስጥ የነበራቸውን ተሳትፎ ለምሳሌ ማንሳት ይቻላል፡፡ ይሁን እንጂ ውጤቱ ተደምሮም ተቀንሶ በእመቤት ክሊንተን የተወራረደው በሚከተለው መንገድ ነው፡፡ አልሸባብንና አልቃይዳን ከማስታገስ አንፃር «የብርንዲ እና የኡጋንዳ» ጦር በሞቃዲሾ ውስጥ እያከናወነ ስላለው ተግባር በፊታችሁ ለማመስገን እፈቅዳሉ፡፡ «Tanks to heroice efferte by ugabdan ande Burundian solders» ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡ እመቤት ክሊንተን ያለነገር «it is time for them to go» አላሉም፡፡ በዚህ ተርታ አገራችን ኢትዮጵያ እንዲሁም መሪዎቻችን አቶ መለስን ጨምሮ በአሜሪካን ዘንድ ያስቆጠሩት ነጥብ እንዳልነበር ልብ ልንለው ይገባል፡፡ ሁል ጊዜ በኢትዮጵያ የጶለቲካ ግለት ፊት እንደመከላከያ ጋሻ የሚያግዙት «አሸባሪው ኢሳያስእና መንግስታቸው» እንኳን የሱማሌን ጉዳይ እና የአፍሪካን ቀንድ« ከማተራመስ» አንፃር በእዚህ በእመቤት ክሊንተን ንግግር ውስጥ ሥፍራ ተሰጥቶት አልተወቀሰም፡፡ ይህ ማለት ግን ኢሳያስን ምንም ምርጫ አላካሄድኩም በማለት« በምርጫችን» ላይ ቢያላግጡም «it is time for them to go» አይመለከታቸውም ማለት አይደለም፡፡

ፍተሸ 3

መቼም አገራችንን ኢትዮጵያ« በመወከልም »ይሁን በግላቸው የሚያደርጉት ጥረት ጠቅላይ ሚኒስቴራችን የተገኙባቸውን ታላላቅ ጉባሄዎች እና ስብሰባዎች ከደርዘን በላይ ማንሳት እና መዘርዘር የሚያስቸግር አይሆንም፡፡ በትንሿ ምሳሌ እንኳን በቡድን ስምንት ጉባኤ ላይ በተለያየ ጊዜ ተጋብዘው ተገኝተዋል ሲባል ሰምተናል፡፡ «የለበጣ ይሁን የቁንጠጣ፤ ከአንገት በላይ ይሁን ከአንገት ይሁን ባናውቅም፡፡»በዚያ ስፍራ ተገኝተው ምን ተናገሩ ብለን ባንጠይቅም «ከትላልቆቹ ተርታ» ቆመውና ተቀምጠው በፎቶ ላይ አይተናቸዋል፡፡ አሁንም ዕድሜ «አንድ ለእናቱ » የሆነው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን፡፡ በአየር ንብረት ጉዳይም «ተሟግተው»ቁና ሙሉ ዶላር ለአፍሪካ እና ለኢትዮጵያ ለማስገኘት «ታግለዋል» ይህን ሁሉ የዋሉ ሰው በክሊንተን ንግግር ውስጥ አንድም ቦታ ሲወስዱ አልሰማንም፡፡ ምን አልባት የተባበሩት መንግስት የልማት ድርጅት 8.6 ቢሊዮን ዶላር ከኢትዮጵያ ተዘርፏል በማለት ይፋ ያደረገው መረጃ በጥረታቸው ላይ ውሃ ከልሶበት እንደሆነ አላውቅም፡፡

ወዲህ አገር ውስጥ ደግሞ የሰፈር አውደልዳይ ካድሬ ሁሉ ሳይቀር የኢትዮጲያን ዕድገት እና ልማት በአሀዝ እያስደገፍኩ በነገርኳችሁ መሰረት «ዋጡ» እያለ በዛሬው ቀን እየስጨነቀን ነው፡፡ እመቤት ክሊንተን ግን መንግስታቸው ካለው መረጃ እና እርሳቸው ከያዙት ስልጣን አንፃር የኢኮኖሚያችንን ጉዳይ፤ መሪዎቻችን በነገሩን መንገድ ሳይሆን እኛ በምንኖረው ኑሮ እና ህይወት መጠን ፍርጥ አድርገው ነግረውናል፡፡ በዚሁ በመዲናችን በአዲስ አበባ፤ በዚሁ በታላላቅ የኢኮኖሚ ጉባኤ ላይ ከመገኘት ባልቦዘኑት የአፍሪካ እና ብሎም የኢትዮጵያ የእድገት አቅጣጫ «ከመተንተን » ባልተቀቡት ጠቅላይ ሚኒስተራችን እና ታላላቅ ባለስልጣኖቻችን ቁጭ ብለው ባዳመጡት ጉባኤ ፊት እመቤት ክሊንተን ምስክርነታቸውን የሰጡት በሚከተለው አገላለፅ ነበር፡፡ «Countries such as zambia,Ghana, and Rwanda have had strong successes with their approaches to delomement »በአማሪኛ ስንከልሰው የተሳካላቸው አገራት የተባሉት እነዚህ ናቸው፡፡ ልብ በሉ ከላይ የተጠቀሱት አገራት «የህዳሴ ዜማዎች » «የህዳሴ መዋጮዎች»ለመኖራቸው የተነገረ ነገር የለም፡፡ ይሁን እንጂ ለአፍሪካ ልማት ተምሳሌት ተብለው በኦባማ አስተዳደር ተመስግነዋል ፡፡ በመልካም መንግስታቸው በእነዚህ አገራት እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ ቃል መግባቱን አስረግጠው ተናግረዋል፡፡ ደጋግመው እንዳረጋገጡት መንግስታቸው ሙሰኝነትን አምርሮ እንደሚታገል ገልፀዋል፡፡ ጎበዝ የእኛ ባለ ሁለት ዲጅት እድገት ውሃ በላው ማለት ነው? እኛ እንደማናምንበት ሁሉ የኦባማ አስተዳደርም በኢትዮጵያ ውስጥ በተመዘገበው ልማት እንደማያምንበት መገንዘብ ይቻሎል፡፡ በዚሁ ሁሉ ንግግራቸው ውስጥ ስለ ኢትዮጵያ አንድ ነገር ላይ ብቻ አድናቆታቸውን ገልፀዋል፡፡ በእኔ አረዳድ እመቤት ክሊንተን ጎንደር ሳይዘልቁ ቅኔ መቀኘት መቻላቸውን የተገነዘብኩበት ክፍል ነው፡፡ «Ethiopia has mobilized an army of 30,000 health workers» ነበር ያሉት ፡፡ ለዚህ አድናቆታቸውን ችረዋል፡፡ የጤናው ሰራዊት ለሕዝቡ እየሰጠ ስላለው ግልጋሎት የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያውቀው ጉዳይ ቢሆንም ለኢትዮጵያ መንግስት የሃያ ዓመት ድካም በኦባማ አስተዳደር የተቆጠረለት ነጥብ ይህ ብቻ መሆኑን አንባቢ እንዲያስተውል እጠይቃለሁ፡፡

ፍተሸ 4

ከወራት በፊት በኢትዮጵያ ቴሌቪዢን መስኮት ቀርበው የማረጋጋት መልዕክት ያስተላለፉት አቶ መለስ ዜናዊ« የአረቡ ዓለም አብዮት» አያሰጋንም በማለት ተረጋግተው ሊያረጋጉን ጥረት አድርገዋል፡፡ በዚህ መግለጫ መሰረት መረጋጋት እና አለመረጋጋት የኢትዮያ ሕዝብ ጉዳይ ቢሆንም የአረቡ ዓለም አቢዮት ቋያ ወደ አፍሪካ የተሸጋገረ ለመሆኑ እና ከዚህ አንፃር ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው መሪዎች ይህንን መንፈስ ከቶ ማቆም እንዳማይቻላቸው እመቤት ክሊንተን እንደሚከተለው ገልፀውታል፡፡ «በዓለማችን በየትኛውም ክፍል የሚገኙ አምባገነን መሪዎች ሁሉ ከዚህ ለዲሞክራሲ ከሚደረግ እንቅስቃሴ ብሎም ማዕበል ተገቢ የሆነ መልዕክት ማግኘት አለባቸው ካሉ በኋላ በተለይ መልዕክቱ ለአፍሪካ ጨቋኝ መሪዎች ወቅታዊ እንደሆነ አሰምርበታለሁ፡፡ ጤናማ አህምሮ ላለው የትኛውም ሰው እመቤት ክሊንተን « The Arab spring» በማለት የገለፁት ነውጥ መሰረታዊ መነሻ አለው፡፡ ኑራችንን ተመልከቱ፡፡ ከግንቦት 17 እስከ 19 2003 ድረስ የተፈጠረው «የዘይት ሐይቅ» ግንቦር 21 2003 ላይ ክው ብሎ ደርቋል፡፡ ከዘይት ሱናሚ «መጥለቅለቅ» የተረፍነው በልዑል እግዚአብሔር እርዳታ ነው፡፡ ብንል ቀልድ አንመስልም፡፡የአንድ አገር መንግስት ለተከታታይ ሁለት ዓመት  የቴሌቭዥን ዜናውን በዘይት ፤በዱቄት፤ በስንዴ፤በስጋ ወዘተ ጀምር በእነዚህ አንገብጋቢ አጀንዳዎች ተጨንቆ  ያስጨነቀባት አገር ብትኖር ከዓለም የመጀመሪያ አገር በመሆን ኢትዮጵያ በጊንየስ ቡክ ላይ እንድትፃፍ መጠየቅ ዲሞክራሲያዊ መብታችን ነው፡፡ ብል ማጋነን አይሆንም ፡፡ ምናልባት አንድ ወገን ተነስቶ «የአገር ገፅታ በማጉደፍ ትጠየቃለህ» ካላለኝ በስተቀር፡፡ ዘይት የምናመጣው በነውጥ እየተናጡ ካሉ ዓረብ አገራት መሆኑን ላስተዋለ ዜጋ የዓረቡ አገር ነውጥ ተደምሮም ተቀንሶም ዘይት ፤ስኳር፤ሥጋ፤ ዱቄት ወዘተ አይደለም፡፡ ዲሞክራሲ ነው፡፡ እደግመዋለሁ ዲሞክራሲ ነው፡፡ እመቤት ክሊንተን እንደገለፁት የአንባገነንነትን ስርዓት ለመቀየር የሚደረግ ትግል ጉዳይ ውስጥ እነዚህ ቁሳቁሶች የሉም፡፡ እንዲህ ነው ያሉት የዚህ ትግል ጉዳይ የምርጫ ስርዓት ነፃ አይደለም፤ፍርድ ቤቶች ገለልተኛ አይደሉም፤ ሕገመንግስቱ አልተመቸንም ደህይተናል፤ ሥራ የለንም፤ ግድያና እስራቱ ተጧጡፏል ይቁም፤ መሪዎችን ለ10፤ለ20፤ለ30 ዓመት የምንሸከምበት ጫንቃ የለንም፤ ነፃ ሚዲያ ሥርዓት ናፍቆናል፤ አንጡራ ሀብታችን እየተዘረፈ ነው፤ሙስና አቆርቁዞናል፤ሌሎች ብዙ ብዙ ጉዳዮች ናቸው፡፡ እኛ ተኝተን ሳለን ዓረቦች መንፈሱን ከእኛ አገር ሰርቀው ወስደውት ካልሆነ በሰተቀር በኑሮ እረገድ እኛ እና ዐረቦች የት እየት ተገናኝተን? እናም እመቤት ክሊንተን «መንፈሱን» ከዐረብ አገር ተነሳ በማለት አለሳልሰው ይግለፁት እንጂ የዚህ መንፈስ ባለቤት አፍሪካ ናት፡፡ ዋናዋ ደግሞ ከላይ ከተዘረዘሩት ዲሞክራሲን የማስፈን ትግል አኳያ እናት ኢትዮጵያ ናት፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ቢያንስ ቢያንስ የዚህን መንፈስ የባለቤትነት መብታችንን ሊያከብሩልን ይገባል፡፡ የአፍሪካ መሪዎች በዚህ መልኩ እያስገመገመ ያለውን መንፈስ በሰበብ ባስባቡ ባይጋፉት መልካም ነው፡፡ እኔም እንደ አንድ ተራ ዜጋ እና ዲሞክራሲን እንደሚናፍቅ ኢትዮጵያዊ የእመቤት ክሊንተንን መልዕክት ጮክ ብዬ አስተጋባለሁ፡፡ «status quo is broken» አዎ ነገሮች ተቀይረዋል፡፡ « it is time for them to go »  መንፈሱ አሁኑኑ ኢዱ እያለ ነው፡፡ ልብ ያለው ልብ ይበል፡፡ የደፈረ ደግሞ ይወስን፡፡

ፍተሸ 5

እመቤት ክሊንተን ከዚህ መልዕክት በኋላ ያመሩት ወደ ጠቅላይ ሚኒስቲራችን ቢሮ ነበር፡፡ ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ባገኘሁት መረጃ 25 ደቂቃ ብቻ ቆይተዋል፡፡ ገፅን ለማሳመር የተዋጣለት የኢትዮጵያ ቴሌቪዢን ቆይታቸውን ሁለት ሰዓት አድርጓል፡፡ እዚህ ጋር «ሃሜትም»  በሉት «ግምት» በመረጃ ላይ በተደገፈ ትንተና እመቤት ክሊንተን በተከበረው መንግስታችን መቀመጫ ዋና ከተማ ተገኝተው ስለ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲ፤ ስለኢኮኖሚ ልማቷ፤ ስለ መልካም አስተዳደሯ፤ ስለ ሰብአዊ መብት አያያዟ፤ ስለ ሽምግልና አዋቂነቷ እና ብቃቷ፤ ስለአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሚናዋ አንድም የሚመሰክሩት አጥተው 30,000 የጤና ሰራዊት ማሰልጠነዋን ጠቅሰው ሲያበቁ በተለይ ደግሞ «የሻቢያን መንግስት የአፍሪካ ቀንድ አተራማሽነት» በተመለከተ ትንፋሽ ሳይወጣቸው በ25 ደቂቃ ውስጥ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ «ለአቶ መለስ እና ለአቶ ኀ/ማሪያም» በተለየ ሳሎን ውስጥ በሚስጢር አድናቆታቸውን ገልፀው ሄዱ ቢባል ለሰሚው ይገርማል፡፡ ገፅ አሳማሪው የኢትዮጵያ ቴሌቪዢ ን ግን የእመቤት ክሊንተንን ሙሉ ንግግር ላላዳመጡ፤ የንግግራቸውን መልዕክት ማግኘት ላልቻሉ እና ለማያገኙ ያለውን ብሏል፡፡ የሚገረመው ሌሎችን ብሎ «የኤርትሪያ መንግስት በጋራ ከመታገል አንፃር አብረን ለመስራት ተስማምተናል» ተባለ አለን፡፡ ጥቅል እውነቱ ግን ሌላ ነው፡፡ ወደዚያ አንለፍ፡፡

ግምት ወይም ሚስጢር አንድ

ከላይ ከተመለከትነው ከእመቤት ክሊንተን መልዕክት አንፃር በ25 ደቂቃ ውስጥ የሚከተለውን ሊሉ ይችላሉ፡፡ «ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ » በማለት ጀምረው፤ ያው እንደምናውቀው/እንደሚያውቁት በኢትዮጵያ ውስጥ ይመጣል ብለን የጠበቅነው የዲሞክራሲ ስርዓት በአጭር ዓመት የሚሳካ መስሎን ነበር፡፡ በሌሎች አምባገነን መሪዎች እንዳደረግነው ሁሉ ላለፉት 20 ዓመታት በአንድ መልኩ አምነንበት በሌላ መልኩ ሳናምንበት ድጋፋችንን ሰጥተናችኋል፡፡ በእኛ ድምዳሜ ኢትዮጵያም ሆነች አመራራችሁ አልተሳካላችሁም፡፡ ይህ እውነት ባለበት በአፍሪካ አዳራሽ ውስጥ ባደረግኩት ንግግርሬ ኢትዮጵያን እና መሪዎችዋን በተለያየ ርዕሶች ስር ደጋግሜ ባወድስ ኖሮ አንድም የኦባማ አስተዳደር «public accountability» ማንኳሰስ ነው፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ ከያዝኩት ትልቅ ስልጣን አንፃር ለተናገርኩት ቃል አለመመታመን ይሆንና ይህም በሚሊዮኖች ህይወት ላይ የጠመንጃ ቃላ እንዲሳብ የመተባበር ያህል ነው፡፡ የኢትዮጵያዊያን ያህል የተዋጣለት ቅኔ መቀኘት ባልችልም የዓረብ ዓለም መንፈስ ወደ አፍሪካ መዛመቱን ከተለያዩ የአሜሪካ መንግስት የኢንተለጀንሲ ምጮች ባለን መረጃ መሰረት እኔ እና መንግስቴ አረጋግጠናል፡፡ እንዲያውም ይህ መንፈስ ከኢትዮጰረያ ላለመነሳቱ ምንም መከራከሪያ የለንም፡፡ ምክንያቱም 20 ዓመት ሕዝባችሁ በቀን 3 ግዜ  እንደሚመገብ ቃል ገብታችሁለት  ወይም ነግራችሁት ነበር፡፡ ከ20 ዓመት በኋላ ሕዝባችሁ የተረፈው በቀን 3 ጊዜ መተንፈስ ብቻ ነው፡፡ ይህንን ከእኔ ይልቅ እናንተ በደንብ ታውቁታላችሁ፡፡ ከሌሎች የአፍሪካ መሪዎች ጋር በአደባባይ በምሳሌ አስታክኬ  እመክራችኋለሁ፡፡ ዘ« it is time for them to go » ያልኩትን በነጠላ በሥራ ላይ አውሉት፡፡

ግምት ወይም ሚስጢር ሁለት

መቼም እንደምታውቀው /እንደምታውቁት ኢትዮጵያ የብዙ ብሔር ብሔረሰቦች አገር ናት፡፡ በጊዜው ብዙ ምስቅልቅል ከመፈጠሩ በፊት ብሔራዊ እርቅ ጥሩ፡፡ ብሔራዊ እርቅ የማውረድ እድሉ በእናንተ እጅ ነው ስርዓታዊ ለውጥ አካኢዱ፡፡ የሽግግር መንግስት ፈጥራችሁ ከሁሉም ተቃዋሚዎች ጋር አቋቁሙ፡፡ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር ካሉት ጋር ማለቴ ነው፡፡ ይህ በጣም ጠቃሚ እርምጃ ሊሆን ይችላል ፡፡ ይህንን ማድረግ የተሳናቸው የቅርብ ቀን ወዳጆቻችሁ የሚገኙበትን ሁኔታ አይታችኋል፡፡ ለብዙ ማዕበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊእና ፖለቲካዊ መመሰቃቀል ተዳርገዋል፡፡ ለዚህ ሁሉ ሁኔታ መፈጠር ተጠያቂ እየሆኑ ያሉት የየአገሮቹ መሪዎች ናቸው፡፡ ይህ ሁኔታ በሚፈጠርበት ወቅት አሜሪካ ከአምባገነኖች ጋር አትቆምም፡፡ በቃ ለኢትዮያ ያለኝ መልዕክት ይህ ነው፡፡ አዝናለሁ ይህንን መልዕክት በተናገርኩበት አንደበቴ በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠት የምንችል አይመስለኝም፡፤

መደምደሚያ

እመቤት ክሊንተን በ45 ደቂቃ ንግግራቸው በአፍሪካ አዳራሽ በ25ቱ ደቂቃ ደግሞ በብሔራዊ ቤተመንግስት ያስተላለፉት መልዕክት ባጭሩ በእኔ ግምገማ እነዚህ ነበሩ፡፡ «ጨዎች ለራሳቸሁ ስትሉ ጣፍቱ..» «ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ…» የዓረቡ ዓለም መንፈስ በደጃችሁ ነው፡፡ በማጠቃለያ ያሉት የሚከተለውን ነው፡፡ እግዚአብሔር ይባርካችሁ፡፡ አሜን እኛም ተቀብለና