Monthly Archives: November, 2013

An Oromo girl in Saudi Arabia ran over by car as she was boarding the bus for deportation to Ethiopia

የሻማ ማብራት ጥሪ በኮለራዶ

http://www.ethiopianreview.info

በኮለራዶ ነገ እሁድ ከጠዋቱ በ10 ሰዓት በዳግማዊት ግሸን ማርያም ቤ/ክ ለሳዑዲው ጥቃት ሰለባዎች የሻማ ማብራት ምሽት ተዘጋጅቷል። የጥሪው ወረቀት የሚከተለው ነው፦
candle night Colorado

ከሳዉዲ ለመመለስ የተዘጋጁ ወገኖች አቤቱታ

በጅዳውስጥሸረፍያ በሚባል አካባቢ ወደሃገራችን እንግባ በሚሉ ኢትዮጵያዉያን እና በጸጥታ አስከባሪዎች መካክል ግጭት መፈጠሩ ተገለጸ።

ለቀናት በጅዳ ቆንስላ መስሪያ ቤት ተጠልለው ከነበሩበት ቦታ ወደተጠቀሰዉ አካባቢ መጠለያ የተወሰዱ እነዚህ ወገኖች ላለፉትሶስት ቀናት ወደመጠለያው መግባት አልቻልንም ሲሉ በምሬት ይናገራሉ። ከሽሜሲ ጊዜያዊ ማቆያ ግቢ ውጭ አውቶቡስ ዉስጥ ያለ ምግብና ዉሃ መቆየታቸዉን የሚገልፁት እነዚሁ ወገኖች ሕጻናትና ነፍሰ ጡሮችና፤ እንዲሁም አቅመ ደካሞች ለከፋ አደጋ መጋለጣቸውን ጄዳ ለሚገኘዉ ወኪላችን ገልጸዋል። ነብዩ ሲራክ ዝርዝር ዘገባ አለዉ፤

ነብዩ ሲራክ

ሸዋዬ ለገሠ

http://www.dw.de

Qeerroo – Gumaacha Artistii Kabajamaa fi Jaallatamaa Hirphaa Gaanfuree: “Ka’i, Oromoo!!”

እሥራኤልና የአፍሪቃውያን ስደተኞች ዕጣ

የእሥራኤል ሚንስትሮች ም/ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር የገቡ ናቸው ያላቸውን አፍሪቃውያን ስደተኞች፤ በግዴታ እንዲመለሱ ማድረግ የሚቻልባቸውን የእርምጃ ዓይነቶች ትናንት ማጽደቁ ተነግሯል። እሥራኤል የገቡ 60,000 ያህል ስደተኞች ወደ መጡበት

እንዲመለሱ ለማስገደድ የእሥራኤል መንግሥት፣ የተለያዩ የስደተኞችን እንቅሥቃሴ የሚገቱና ተስፋ የሚያስቆርጡ እርምጃዎችንም በመውሰድ ላይ ነው። ስደተኞቹ አግባብ ያለው መፍትኄ እንዲያገኙ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች ምን ማድረግ ይችላሉ? ተክሌ የኋላ ፣ በአሥራኤል የአፍሪቃውያን ስደተኞችን የልማት ማዕከል ሥራ አስኪጅ በማነጋገር ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።

ድምፅ እንዲሰጥበት ዛሬ ለፓርላማ የሚቀርበው አዲሱ የስደተኞችን ዕጣ ፈንታ የሚመለከተው ደንብ ፣ አምና የወጣውን ፤ ስደተኞች ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ እስከ 3 ዓመት እንዲታሠሩ የሚያዘውን የህግ አንቀጽ የሚሽር ነው ። ይህም የሆነው የሥራኤል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባለፈው መስከረም የመጀመሪያውን 3 ዓመት የሚለውን ደንብ ሽሮ ፣ በአንድ ዓመት እንዲገደብ ብይን በመስጠቱ ነው። ያን ያህል ውጣ -ውረድ ለምን አስፈለገ ?ስደተኞቹ ተገልለው በረሃ ላይ በአንድ መጠለያም ሆነ ማጎሪያ ቦታ እንዲቀመጡ መወሰኑስ ለምን ይሆን?በእሥራኤል የአፍሪቃውያን ስደተኞች የልማት ማዕከል ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮሐንስ ባዩ—

የእሥራኤል መንግሥት ወደ ግዛቱ ፣ ህገ ወጥ በሆነ መንገድ ገቡ ያላቸውን ሰዎች፤ በተደጋጋሚ ለሀገሪቱ ፀጥታ አስጊዎች ናቸው ነበረ ያለው። እንዲያውም ፤ በአገላለጹ ሠርጎ ገብ (infltrators)የሚለውን ቃል ነው የሚጠቀመው። የተባሉት ሰዎች እስከምን ድረስ በእሥራኤል ፀጥታ ላይ አደጋ ደቅነው ይሆን፦ በጥናት የሚታወቅ ነገር ይኖር ይሆን!

እሥራኤል ውስጥ ከሚገኙት ስደተኞች መካከል በዛ ያሉት ኤርትራውያንና ሱዳናውያን ናቸው ፤ ኢትዮጵያውያንም አሉ። አሁን እንደተባለው የእሥራኤል መንግሥት ስደተኞች አገር ለቀው እንዲወጡለት ነው አጥብቆ የሚሻውና ትኩረትም ያደረገው።

አንዱ እርምጃው፤ ለመቋቋሚያ የሚሰጠውን ገንዘብ ከ 1500 ወደ 3,500 ዶላር ከፍ ማድረግ ነው። 10 ሺ ያህል ስደተኞችን ተቀብሎ ለሚያስተናግድለት ከ 2 የአፍሪቃ አገሮች ለአንደኛው የጦር መሣሪያና ሌላም ሌላ እርዳታ ለማቅረብ ሐሳብ እንዳለው የተገለጠበት ጊዜም ነበረ። በስዑዲ ዐረቢያ የተፈጸመው ዓይነት እርምጃ በእሥራኤል የማይታሰብ ነው ቢባልም ስደተኞቹ፣ ከጭንቀት የሚገላግላቸው መላ አላገኙም ፤ አልተገኘላቸውም።

ተክሌ የኋላ

ሂሩት መለሰ

http://www.dw.de/

Seife-Nebelbal Radio: Interview with Ob. Geresu Tufa

Oromo Community in Oslo Protests Against Human Rights Violations Against Oromo Immigrants in Saudi Arabia

በሳዑዲ አረቢያ አልቃሲም ከተማ አፈሳ ተጀመረ

Saudicry
(ዘ-ሐበሻ) ከሳዑዲ አረቢያ 13 ግዛቶች ውስጥ በሰው ብዛት 7ኛ እንደሆነች በሚነገርላት አል ቃሲም ከተማ ስደተኞችን ማፈስ ተጀመረ። ከትናንት ጀምሮ ፖሊስ በየቤቱ እየሰበረ በመግባት ስደተኞችን እያፈሰ መሆኑን ከአካባቢው የዓይን እማኞች ለዘ-ሐበሻ በላኩት መረጃ ዘገበዋል።

ከዚህ ቀደም በሪያድና በመካ በርካታ ኢትዮጵያውያን ሞት፣

ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ ወይም ቪዲዮውን ለማየት እዚህ ላይ ይጫኑ።

ኦባንግ በሳዑዲ አረቢያ ዜጎቻችን ዙሪያ ከዓለምአቀፍ ተቋማት ጋር እየሠራሁ ነው አሉ

obang (1)

ዘ-ህበሻ | November 22nd, 2013

በሳዑዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን ፈር የለቀቀ አስነዋሪ ግፍ ዓለምአቀፍ ይዘት እንዲኖረው ለማድረግ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና ሌሎች ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች ጋር እየሠሩ መሆናቸውን አቶ ኦባንግ ሜቶ በተለይ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ተናገሩ፡፡ የሳዑዲ ልዑል ሰብዓዊነት የረገፈበትንና በግፍ የተሞላ የወሮበላ

ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ ወይም ቪዲዮውን ለማየት እዚህ ላይ ይጫኑ።

Gadaa.comS. Arabiyaa Keessatti Gochaa Sukkanneessaa Oromoo fi Saboota Biroo Irratti Raawatame Mormuun Oromoonni Oslo, Norway keessatti Hiriira Bahan