የአሶሳ ከተማ የቀድሞ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር ዋሉ

የአሶሳ ከተማ የቀድሞ ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 15 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ከአሶሳ ከተማ መሬት ጋር በተያያዘ በብልሹ አሰራር እጃቸው አለበት ብሎ የጠረጠራቸውን የቀድሞው የአሶሳ ከንቲባ አቶ ያሲን አሸናፊን ጨምሮ 8 የአስተዳደሩ የቀድሞ አመራሮች አመራሮች በቁጥጥር ስር አዋለ ።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር በላይ ወዴሻ ለፋናብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት በተጠርጣሪዎቹ  ከ 97 ሺ ካሬ ሜትር በላይ የአሶሳ ከተማ መሬት ባልተገባ መንገድ ጥቅም ላይ ውሏል ።

ኮሚሽኑ እንዲህ አይነት ብልሹ አሰራር ውስጥ የገቡ የአመራር አካላትን  ለህግ የማቅረቡ ስራ ተጀመረ እንጂ አላለቀም ብሏል ።

ከህዝቡ ጥቆማ በመነሳት በዚህ ችግር ውስጥ ተሳትፈዋል የተባሉ ግለሰቦች ላይ መረጃዎችን ለማሰባሰብ ኮሚሽኑ  ከ6 ወራት በላይ ጊዜ ወስዶበታል ።

ከምርምራ ቡድን አባላት ከተገኘው መረጃ በመነሳት ከ97 ሺ ካሬ  በላይ መሬት ቀደም ብሎ መታገዱን ነው ኮምሽነር በላይ አስታውሰዋል።

በ2003 አመተ ምህረት ይህ ችግር ሲፈጠር ተሳትፈዋል የተባሉት ከንቲባ ፤ አፈጉባኤ ፤ ስራ እሰኪያጅ እንዲሁም የቅየሳውን ስራ ሲያካሂዱ የነበሩት አካላት ከዛን ጊዜ በኋላ በተለያዩ የመንግስት መዋቅሮች ተሹመው ሲሰሩ ነበር ።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s