! … የፖለቲካ ፓርቲና ህዝብ ምን አገናኛቸው?! …!

“ኢህኣዴግ ራሱ ብቸኛ አማራጭ አድርጎ ለማቅረብ የመንግስትን ስልጣንና ሃብት አለኣግባብ ተጠቅሞ የህዝቦች የመናገርና የመሰብሰብ መብት በመገደብ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ያዳክማል” ብዬ ላነሳሁት ሓሳብ “ህዝብ ሌላ ፓርቲ ሌላ” (ህዝብና ፓርቲ ምን አገናኛቸው) የሚል አስተያየት ደርሶኛል።

አዎ! ህዝብና ፓርቲ የተለያዩ ናቸው፣ ግን ይገናኛሉ። እንዴት? በሰለማዊ ትግል የፖለቲካ ፓርቲዎች ስልጣን ለመያዝ (ከዛም ‘አለን’ የሚሉትን አማራጭ አቅጣጫ በመተግበር የሀገርን ሁለንተናዊ ልማት ለማፋጠን) ይወዳደራሉ። የውድድር ሜዳው ምርጫ ነው። የሚወዳደሩበት ካርድ ፖሊሲያቸው ነው። መራጩ ደግሞ ህዝብ ነው። ተቃዋሚ ፓርቲዎች ህዝብ ከደገፋቸው ጥንካሬ ይኖራቸዋል፣ ደግፎ ከመረጣቸው ደግሞ ስልጣን ይይዛሉ። ስልጣን ከያዙ አማራጫቸውን ያሳዩናል።

ይህን እውን እንዲሆን ህዝቡ የፈለገውን ፓርቲ በነፃነት እንዲደግፍ ወይ እንዲቃወም ወይም ገለልተኛ እንዲሆን መንግስት (ገዢ ፓርቲ አላልኩም) መተባበር አለበት። በዴሞክራሲያዊ መንግስት ወይ ሀገር የፓርቲዎች የጥንካሬ (እንዲሁም የስልጣን) ምንጭ ህዝብ እስከሆነ ድረስ የህዝብ ነፃነት መገደብ (በተዘዋዋሪ) ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዲዳከሙ እየተደረገ ነው ማለት ነው። ተቃዋሚዎችን ማዳከም ህዝቡ አማራጭ የፖለቲካ መንገድ ማሳጣት ማለት ነው። አማራጭ መንገድ ማሳጣት ማለት የህዝብ የልማት አቅጣጫ መዝጋት ማለት ነው።

የህዝብ የልማት አቅጣጫ ተዘጋ ማለት ህዝቡ ታገተ ማለት ነው። ህዝቡ ታገተ ማለት ደግሞ ህዝቡ እየተመራ አይደለም ማለት ነው። ምክንያቱም ህዝብ መምራት ማለት መንገድ ማሳየት እንጂ መንገድ መዝጋት ማለት አይደለም። የህዝብን የልማት መንገድ የሚዘጋ መንግስት ፀረ ህዝብ ነው።

ህዝብ የፈለገውን ለመደገፍ ካልተፈቀደለት ተቃዋሚዎችን የሚደግፍበት ዕድል አይኖረውም። ዕድሉ ከሌለ ተቃዋሚዎች ድጋፍ አያገኙም። ድጋፍ ካላገኙ ጥንካሬ አይኖራቸውም። ጥንካሬ ከሌላቸው ተዳከሙ ማለት ነው። ስለዚህ የተቃዋሚዎች ጥንካሬ ወይ ደካማነት ከህዝብ ነፃነት ጋር ይገናኛል (በበለጠ ግን የፓርቲዎች ጥንካሬ ከውስጣዊ ዓላማና ተነሳሽነት የሚመነጭ ሲሆን የዓላማ ፅናትና ትክክለኛነት የህዝብን ድጋፍ ለመሳብ ይረዳል)።

ዞሮዞሮ ግን (ፓርቲዎች ውስጣዊ ጥንካሬ ቢኖራቸውም ባይኖራቸውም) በዴሞክራሲያዊ፣ ሰለማዊ ትግል የህዝብ ነፃነትና ተሳትፎ በፓርቲዎች ጥንካሬ ጉልህ ሚና አለው። በዴሞክራሲያዊ መንግስት የስልጣን ምንጭ ህዝብ በመሆኑ ነው።

ስልጣን በሃይል (በጠመንጃ) ለሚይዙ ድርጅቶች ግን የህዝብ ነፃነትና ተሳትፎ ወሳኝ ላይሆን ይችላል (የስልጣን ምንጫቸው ጠመንጃ ነውና)። ስለዚህ ለሁሉም ፖለቲካዊ ሂደት መሰረቱ ህዝብ ነው። እናም ፓርቲዎችና ህዝብ ይገናኛሉ።

ባጭሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥንካሬ የሚለካው ባላቸው የህዝብ ድጋፍ ነው። (የህዝብ ድጋፍ ለማግኘት ግን የዓላማ ትክክለኛት ወሳኝ ነው)።

It is so!!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s