የፍትህ አካላት የመጨቆኛና የማፈኛ መሳርያዎች መሆናቸው ያብቃ!

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ)
Ethiopian People’s Congress for United Struggle (Shengo)
ሚያዝያ 25 2005
(May 3
2013)

ala

አቶ እሰክንድር ነጋና አቶ አንዱአለም አራጌን ጨምሮ በሽብርተኛነት የፈጠራ ክስ ውንጀላ በረጅም እሰራት የሚማቅቁትን ውድ የኢትዮጵያ ልጆች በቀጣይነት ለማሰቃየት በትላንትናው እለት የአዲስ አበባ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወሰደውን እርምጃ  የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ፣በጥብቅ ያወግዛል።

በመላው ዓለም የነፃ ፕሬስ መብት በሚከበርበት ቀን ዋዜማ፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የቀረበለትን ይግባኝ ውድቅ አድርጎ በእውቅ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ መሪዎች ላይ ካሁን በፊት የበታች ፍርድ ቤት ጥሎባቸው የነበረውን ፍርደ ገምድል ብይን እንዲጸናና  የስቃይ ዘመናቸው እንዲቀጥል መፍረዱ አገዛዙ ነፃ ፕሬስንና የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን  ለማጥፋት ለ21 ዓመታት እንዳደረገው ሁሉ አሁንም በዚያው አጥፊ ጎዳና  እየቀጠለ እንደሆነ የሚያሳይ ነው። የሀገሪቱ የፍትህ አካላትም ይህንኑ እኩይ ተግባር ለማሳካት ሙሉ በሙሉ የአገዛዙ የፖለቲካ መሳሪያ እንደሆኑ መቀጠላቸውን የሚያመለክት ነው።

የፍትህ አካላቱ የዜጎችን መብት ማሰከበርና መብታቸው የተረገጠባቸው ግለሰቦችም አለኝታ መሆን ሲገባቸው፣ ተራ የፖለቲካ መሣሪያ ሆነው መቀጠላቸው ለሀገሪቱ ህዝብ ብቻ ሳይሆን  በሙያው ለተሰማሩትም ሁሉ እጅግ አሳፋሪና አሳዛኝ ነው።

እራሱን በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የጫነው አገዛዝ፣ ሁሉንም ተቋማት ለአምባገነን ስርዓቱ እድሜ ማራዘሚያ አድርጎ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ ድምጽ የሚያፍን፣ የሀገሪቱን ልዖላዊነት የካደና በተግባርም በመንቀሳቀስ አካሏን ያስቆረሰ፣ ያለባህር በር ያስቀረ፤ ደንበራችንን አሳልፎ ለጎረቤት ሀገር በገጸበረከትነት የሰጠ፤ በህዝብ መካከል የተለያዩ ልዩነቶችን እየፈለገ ግጭቶችን ሆን ብሎ የሚያራግብ፤  በሃይማኖት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ምዕመናኑን ያሰቃየ፣እምነታቸውን የተፈታተነ፤ በሚናገሩት ቋንቋና በዘውጋቸው እየነጠለ ዜጎችን ለዓመታት ከኖሩበትና ህይወት ከመሰረቱበት ቀያቸው  እያፈናቀለ የሚገኝ ፍጹም አምባገነናዊና ጎሰኛ ቡድን ነው። ባጭሩ የሀገራችንና የህዛባችን አበይት ችግሮች ዋናው ምንጭ ይኀው ስርአትና አገዛዙ ናቸው፣ በመሆኑም ከዚህ አስከፊ ስርዓት ፍትሃዊነትን መጠበቅ የሚቻል አይደለም።

ስለሆነም፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ይህን ከዓመት ዓመት እየከፋ የመጣውን የመብት ረገጣና ፈላጭ ቆራጭ አምባገነናዊ ስርአት በአንድነት በመቆም አምርሮ እንዲታገል አሁንም ደግመን ጥሪ እናቀርባለን ። በተቃዋሚነት የተሰለፉ የፖለቲካ ሀይሎችም  በህዝባችን ላይ የተጫነውን  የጨለማ ዘመን ለማሳጠር  በአንድነት ቆመን በጋራ ለመታገል እንችል ዘንድ ጊዜ ሳንወስድ ወደ ተግባር እንድናመራ አሁንም ጥሪያችንን እናቀርባለን።

የዜጎች ሁሉ መብቶች በተባበረ የሕዝብ ትግል ይከበራሉ!

http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/7639

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s