ኢሕአዴግ በምርጫው በደረሰበት መደናገጥ የ5 ለ1 ጠርናፊዎቹን መገምገም ጀመረ

“ፓርቲው ህዝብ ለምርጫ ያልወጣው በጠርናፊዎች ድክመት
ነው የሚል አቋም ላይ ደርሷል” ውስጥ አዋቂ ምንጮች

ምንጮቹ ለፍኖተ ነፃነት እንዳስረዱት ኢህአዴግ አንድ ለ አምስት ህዝቡን እንዲያደራጁ ያሰማራቸውን ጠርናፊዎች በግምገማ እያተራመሳቸው ነው፡፡ እንደምንጮቹ መረጃ ኢህአዴግ በመላው ሀገሪቱ የጥርነፋ መዋቅር አደራጅቷል፤ መዋቅሩ የግለሰቦችን ዝርዝር መረጃ ለደህንነት አካላት ማስተላለፍ፣ በምርጫ ወቅት ኢህአዴግ እንዲመረጥ ማስገደድ እና ፓርቲውና መንግስት ላይ የሚነሱ ተቃውሞዎችን ለመቆጣጠር ተብሎ የተደራጀ ነው፡፡ ሆኖም ባለፈው ሳምንት በተደረገው ምርጫ አንድ ለአምስት የተጠረነፈው አብዛኛው ህዝብ ለምርጫ አለመውጣቱ ኢህአዴግን አስደንግጦታል፡፡ በዚሁ ምክንያትም ጠርናፊዎቹን “የምርጫ ሰራዊት በአግባቡ አላንቀሳቀሳችሁም” በማለት ጥብቅ ግምገማ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

banede
የፍኖተ ነፃነት የመረጃ ምንጮች እንደሚያስረዱት በተለይ በአዲስ አበባ በሁሉም ወረዳዎች ያሉት የኢህአዴግ ካድሬዎችና የህዋስ አመራሮች አንድ ለ አምስት የጠረነፏቸውን ግለሰቦች ስም ዝርዝር ለአለቆቻቸው ከቃለመሀላ ጋር አስመዝግበዋል፤ ፓርቲውም ከተጠረነፈው ህዝብ መሀከል ቢያንስ 80 በመቶ እንደሚመርጠው በካድሬዎቹ
ማረጋገጫ ተሰጥቶታል፡፡ ለኢህአዴግ በደረሰው ዝርዝር መሰረት ለምርጫ ያልወጡ ተጠርናፊዎችን ዝርዝር ከፍተኛ በመሆኑ ጠርናፊዎችን መገምገም ጀምሯል፡፡ ጠርናፊዎቹና ሌሎች የኢህአዴግ ካድሬዎችም ቤት ለቤት እየዞሩ የተጠረነፉ ሰዎች ለምን እንዳልመረጡ እንዲጠይቁና እንዲያስጠነቅቁ ኢህአዴግ ትዛዝ አውርዷል፡፡
በተያያዘ ዜና ባለፈው ሳምንት በተደረገው ምርጫ በርካታ መራጮች ድምፅ ያልተሰጠበት ወረቀት ኮሮጆ ውስጥ በመክተታቸው የምርጫ አስፈፃሚዎች እየተመለከቱ ባዶ ወረቀቱ ላይ ለኢህአዴግ ምልክት እየተደረገ እንደተቆጠረና የተለያዩ የተቃውሞ መልዕክቶች የተፃፉባቸው ወረቀቶችም በብዛት መገኘታቸውን ከተለያዩ አካባቢዎች ተጠናቅረው ለፍኖተ ነፃነት የረደሱ መረጃዎች አመላክተዋል፡፡

Posted by ዘ-ሐበሻ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s