ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ወደ ዝዋይ ወህኒ ቤት ተወሰደ


ፍኖተ ነጻነት

የአውራምባ ዋና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ወደ ዝዋይ ወህኒ ቤት ተወሰደ፡፡

የአውራምባ ዋና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ በፌደራል አቃቤ ህግ በሽብርተኝነት ተከሶ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት ጥፋተኛ በሚል 14 ዓመት ተፈርዶበት ከፍተኛ ጥበቃ በሚደረግበት ቂሊንጦ ወህኒ ቤት ታስሮ ይገኝ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ዛሬ ሚያዚያ 8 ቀን 2005ዓ.ም. ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከአዲስ አበባ ከ170 ኪሎ ሜትር አካባቢ በደቡብ ምስራቅ ርቀት በሚገኘው ዝዋይ ወህኒ ቤት መወሰዱ ታውቋል፡፡

የጋዜጠኛው ባለቤት እና ልጁ በሁኔታው ከፍተኛ መደናገጥ እንደፈጠረባቸው ተጠቁሟል፡፡ በስልጣን ላይ ያለው የኢህአዴግ መንግስት ጋዜጠኞችን በማሰር በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተወገዘና ያሰራቸውን ጋዜጠኞችንም እንዲፈታ በተደጋጋሚ ጫና እየተደረገበት መሆኑ የሚታወቅ ቢሆንም መንግስት ግን ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፣ ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ እስካሁንም ለመፍታት ፈቃደኛ አልሆነም፡፡

OLYMPUS DIGITAL CAMERA

 

 

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s