የገዛ ሚስቱን የሚገድል የኢትዮጵያ ፖሊስ በመንግስት ትዕዛዝ ሕዝብ ጨፍጭፍ ቢባል ከማድረግ ይመለሳል?

(የገዛ ሚስቱን የሚገድል የኢትዮጵያ ፖሊስ በመንግስት ትዕዛዝ ሕዝብን ጨፍጭፍ ቢባል ከማድረግ ይመለሳል? – ይህን ጥያቄ ለመመለስ የሚከተለውን ዜና ያንብቡ)
በቂም በቀል ተነሳስቶ የቀድሞ ባለቤቱን ህይወት በሽጉጥ እንዲጠፋ አድርጓል ሲል፤ የፌዴራሉ ዐቃቤ ህግ ክስ መስርቶበት ጥፋተኛ የተባለው ኮማንደር ግርማ ሞገስ ከትናንት በስቲያ በዋለው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት በ18 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ወሰነበት።

balena

እንደ ዐቃቤ ህግ የክስ ዝርዝር ከሆነ ተከሳሹ ለጊዜው ስሟን የማንገልፅላችሁ ሟች የቀድሞ ባለቤቱን የአብራኬ ክፋይ የሆነ ልጄን ማየትና መጐብኘት እንዳልችል ከልክላኛለች በሚል ቂም-በቀል ተነሳስቶ፤ ሟች መኖሪያ ቤት አካባቢ ድረስ በመሄድ በሰኔ 22 ቀን 2003 ዓ.ም በግምት ከጠዋቱ 2 ሰዓት 30 ሲል በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 01/02 ልዩ ቦታው ሐግቤስ መኪና መሸጫ አካባቢ፤ ከቤት ወጥታ ወደስራዋ ታመራ የነበረችውን የቀድሞ ባለቤቱን የወግ ቁጥሩ 353348 በሆነ ሽጉጥ አንድ ጊዜ ተኩሶ ግራ ጐኗን መትቶ በመጣሉ በደረሰባት ጉዳት ህይወቷ በማለፉ በከባድ ሰው መግደል ወንጀል ተጠያቂ ነው ሲል ያትታል።

በስድስት የሰው ምስክሮች፤ ከምኒልክ ሆስፒታል የቀረበ የአስከሬን ምርመራ ውጤትና ግድያው የተፈፀመበትን ሽጉጥ ለፍርድ ቤት አቅርቦ ያስረዳው ዐቃቤ ህግ፤ ተከሳሹ በተሰጠው የመከላከል ዕድል የዐቃቤ ህግን ክስ ማስተባበል ባለመቻሉ ጥፋተኛ ተብሏል። በመሆኑም የግራ ቀኙን ሀሳብ ሲመረምር የቆየው ፍርድ ቤቱ ከትላንት በስቲያ ውሎው ተከሳሽ ያቀረባቸውን ሦስት የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች ማለትም፤ መልካም ሥነ-ምግባር የነበረው መሆኑን፣ ታታሪ ሰራተኛ መሆኑንና የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ከቅጣቱ ሦስት እርከኖችን ዝቅ በማለት በ18 ዓመታት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ወስኖበታል።n (ምንጭ ሰንደቅ ጋዜጣ የዛሬ ኤፕሪል 17 2013 ዕትም)

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s