በጉዲፈቻ ስም ህጻናትን መሸጥ እንደቀጠለ ነው

ECADF News – ኢትዮጵያ ዉስጥ ህጻናትን በጉዲፈቻ ስም ለፈረንጆች አዘጋጅተው ከሚያቀብሉት የንግድ ድርጅቶች አንዱ “እናት አለም ወላጅ አልባ ህጻናት” ወይም “Enat Alem orphanage” ቀደም ሲል ድርጅቱ ህጻናቱን ምግብ በመከልከል፣ ሲታመሙ ተገቢውን ህክምና ባለመስጠትና በአጠቃላይ ለህጻናቶቹ እንክብካቤ ባለማድረግ ስሙ የተነሳ ሲሆን… አሁን ደግሞ የተገኙት መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ድርጅቱ ድሀ እናቶችን እያፈላለገ ልጆቻቸውን “በእናት አለም ወላጅ አልባ ህጻናት” በኩል ጉዲፈቻ እንዲሰጡ እንደሚያግባባ ተደርሶበታል።

gudi

ከድርጅቱ ሰራተኞች አንዱ ግርማ ቀበለ በ“እናት አለም ወላጅ አልባ ህጻናት” የጥበቃ ሰራተኛ ሲሆን ለሲውዲን ጋዜጠኞች እንደተናገረው… ሌሊቱን በየመንደሩ እየተዘዋወረ ደሀ እናቶች ልጆቻቸውን ለፈረንጆች ጉዲፈቻ እንዲሰጡ እንደሚያግባባና እስካሁን በ145 ጉዲፈቻዎች ውስጥ እጁ እንዳለበት ተናግሯል።

የወያኔ ባለስልጣናት ተሯሩጠው የተጋለጠውን ድርጅት ዘግተውታል፣ ይሁንና አብዛኞቹ በጉዲፈቻ ስም ህጻናትን ከድሀ እናቶች ላይ ወስደው በመሸጥ ስራ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች ስውር የወያኔ ባለስልጣናት እጅ እንዳለባቸው ይጠረጠራል።

በርካታ የመብት ተሟጋች ኢትዮጵያውያን ድርጊቱን አምርረው ያወግዙታል። ነዋሪነቱ በኖርዌይ የሆነው ሀያሲ (blogger) ጌታባለው በቀለ፣ ሰሞኑን “ከኮለኔል መንግስቱ እና ከአቶ መለስ ለኢትዮጵያ ሕፃናት አባት በመሆን ፋውንዴሽን ሊመሰረትለት የሚገባው ማነው?” በሚል ርዕስ ባስነበበው ጦማሩ እንዲህ ብሎ ይጠይቃል “ሕፃናት አሳዳጊ የሚያጡት ባብዛኛው የርስበርስ ጦርነት ሲኖር ወይንም ሰላም በተናጋበት ጊዜ ነው። ኢትዮጵያ ግን ጎዳና የወጡት ሕፃናቶቿ የበዙት በአንፃሩም ቢሆን ጦርነቱ ከቆመ ጊዜ ጀምሮ ነው ለምን?”።

ከዚህ ቀደም የአውስትራሊያው “ABC News” ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ቅጥ ያጣ ጉዲፈቻ ባጋለጠበት ወቅት ድረ-ገጻችን ጉዳዩን ዘግቦ ነበር። ከጥቂት ወራቶች በሗላ በዋሽንግተን ዲሲ በሚኖሩ የወያኔ አባላት በኩል የተቀጠረ ጠበቃ “የጉዲፈቻ ድርጅቱን ስም በማጉደፍ” ድረ-ገጻችንን ለመክሰስ እየተሰናዳ መሆኑን አሳወቀን። ከጠበቃው ጋር በተነጋገርንበት ወቅት “ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ስላለው በጉዲፈቻ ስም ህጻናትን የመሸጥ ጉዳይ” በአሜሪካ ፍርድ ቤቶች መነሳቱን እንደምንፈልገውና እንዲያውም የኢትዮጵያ ባለስልጣናትን የበለጠ ለማጋለጥ እንደሚረዳን አሳወቅነው ነበር። ይሁንና ጠበቃው በጉዳዩ ዙሪያ ተመልሶ አላነጋገረንም።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s