Monthly Archives: April, 2013

አባይ ለሕዝብ ወይስ አባይ ለኢሕአዴግ ? – ግርማ ካሳ

ዶር ቴዎድሮስ አዳኖምን ጨምሮ በርካታ የኢሕአዴግ ባለስልጣናት፣  በተለያዩ የአሜሪካና የአዉሮፓ ከተሞች በመዘዋወር፣ ለአባይ ግንባታ ገንዘብ ለማሰባሰብ ሞክረዋል። ነገር ግን በበርካታ ከተሞች፣ ከዚህ በፊት ከነበረዉ በተለየ ሁኔታ፣ ጠንካራ ተቃዉሞ የደረሰባቸዉ ሲሆን፣ አንዳንድ ከተሞችም፣  ተቃዋሚዎች ስብሰባዉን ሙሉ ለሙሉ እስከመቆጣጠር የደረሱበት ሁኔታም እንደነበረም ታዝበናል።

aba

በሚነሱ ተቃዉሞዎች ዙሪያ፣ በዋሺንግተን ዲስ አስተያየት የሰጡት ዶር ቴዎድሮስ  «በሃሳብ አለመስማማት በጣም ጤነኛ ነገር ነዉ። ነገር ግን እንደ ሰዉ ማመን የሚከብደኝ፣ ድህነትን ከአገራችን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያደርገዉን የልማት እንቅስቃሴ በመቃወም፣ ሳይሰለቻቸው የሚጮሁትን መታዘብ ነዉ» ሲሉ በሚነሱ ተቃዉሞዎች ላይ ያላቸውን ንዴት አዘል ዘለፋ አሰምተዋል።

በተመሳሳይ ሁኔታ አምባሳደር ግርማ ብሩ፣  በሂዉስተን ቴክሳስ፣ ባደረጉት ንግግር፣ የአባይን ግድብ ለመገንባት ለምን እንዳስፈለገ የሚያስረዱ ነጥቦችን  ካስቀመጡ በኋላ ፣  ወደ ንግግራቸዉ መጨረሻ ላይ ድህነትን ከአገራችን ለመቅረፍ የሚረዳ ፕሮጀክትን መቃወም  ከ«ጸረ-ኢትዮጵያዊነት»  ተለይቶ እንደማይታይ በማሳሰብ ነበር፣ በተቃዋሚዎች ላይ ጠንካራ ትችት ያቀረቡት።

ለአባይ ግንባታ ያለኝን የጸና ድጋፍ፣  በተለያዩ ጊዜያት በጽሁፍ ይፋ አድርጊያለሁ። ወደፊትም ይሄንን አቋሜን ከማንጸባረቅ ወደ ኋላ አልልም። አባይን መገንባት ይቻል ዘንድ፣ ኢትዮጵያዉያንን በሙሉ ማሰባሰብ እንደሚያስፈልግ፣ ኢትዮጵያውያንን ለማሰባሰብ ደግሞ፣ በፖለቲካዉና በሰብአዊ መብት አከባበር ዙሪያ ለዉጥ መደረግ እንዳለበትም አሳስቤ ነበር። ከዚህ በፊት ኢሕአዴግ ማሻሻያዎችን እንዲያደርግ የቀረበለትን ጥሪ ተቀብሎ ለብሄራዊ እርቅ ተዘጋጅቶ ቢሆን ኖሮ፣ ዳያስፖራዉ እነ ዶር ቴዎድሮስ አዳኖምን  በተቃዉሞ ሳይሆን በአክብሮት ይቀበላቸው ነበር።

አምባሳደር ግርማ ብሩም ሆኑ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቴዎድሮስ አዳኖም፣ ያጡታል ብዬ አላሳብም፤ ካጡት ግን እንዲገነዘቡ የምፈልገዉ ነጥብ አለኝ። እርሱም አባይ እንዳይገነባ የሚፈልግ ማንም ኢትዮጵያዊ እንደሌለ ነዉ። ጥያቄዉ አባይን የመገንባት አስፈላጊነት ላይ አይደለም። ኢትዮጵያዉያን «አባይ አይገንባ» የሚል መፈክር አላሰሙም።  ጥያቄዉ የፍትህ ፣ የእኩልነት፣ የዲሞክራሲና የመብት ጥያቄ ነዉ። «አባይ ይገደብ። ግን ከአባይ በፊት ዘረኝነት ይገደብ» ነዉ እየተባለ ያለዉ። የሪፖርተር አባባልን ልዋስና «አባይን የመገደብ ሥራ ዴሞክራሲን ባለመገደብ ይታጀብ » የሚል ነዉ አንዱና ዋነኛዉ የኢትዮጵያዉያን  ጥያቄ።

አባይ የሚገነባዉ እኮ ሕዝብን ለመጥቀም ነዉ። አሁን እየሆነ ያለዉ ግን ኢሕአዴግ አባይን፣  ተቃዋሚዎችን ለማጥቃት የሚጠቀምበት መሳሪያ እያደረገዉ፣ ለፖለቲካ ፍጆታና ጥቅም እየተጠቀመበት እንደሆነ ነዉ። አባይ ለሕዝብ መሆኑ ቀርቶ፣ ሕዝብ ለአባይ፣ አባይ ደግሞ ለኢሕአዴግ እየሆነ ነዉ። ከፈረሱ በፊት ሰረገላው እየቀደመ ነዉ። አንድ በሉ።

«አቶ መለስ ሞተዋል። የርሳቸዉን ነገር ለታሪክ እንተወዉ። ከልብ የሚወዷቸዉ ደጋፊዎቻቸውን ላለማስከፋት፣ ለእርቀ ሰላም በሩን እናመቻች» በሚል ሃሳብ ነዉ እንጂ ዝም የምንለዉ፣ ወደ ኋላ ተመልሰን ነገሮችን መምዘዝ ከፈለግን እኮ፣ ብዙ ስለ አቶ መለስ ግፍና ወንጀል መዘርዘር እንችላለን። ኢሕአዴጎች ግን ዝምታችንን እንደ ሞኝነት ቆጥረዉት ነዉ መሰለኝ፣ መለስ ዜናዊን «አምልኩት» ለማለት እየከጀላቸው ነዉ። የአባይንም ግድብ እንደመሳሪያ በመጠቀም የአቶ መለስን «ጀግንነት»፣ «ሕያውነት» በአይምሯችን ዉስጥ ሊቀርጹ ይፈልጋሉ። አባይን ብሎ የሚመጣዉ ሰው ሁሉ የአቶ መለስን ምስል ተሳልሞ እንዲመለስ ነዉ መሰለኝ፣ በዊዉስተን ቴክሳስ በተደረገው የአባይ ግድብ ስብሰባ፣  አምባሳደር ግርማ ብሩ ንግግር ያደርጉበት ከነበረዉ መድረክ በስተቀኝ፣ ትልቅ የአቶ መለስ ዜናዊ  ምስል እንደ ታቦት ተቀምጦ ያየነዉ።

እንግዲህ ሁለተኛው የሕዝብ ጥያቄ «አባይን የፕሮፖጋንዳ መሳሪያ ለምን ታደርጉታላችሁ ?» የሚል ነዉ። «አቦ ሰለቸን። ሱካርም ሲበዛ ይመራል!  አባይ አባይ ፣ መለስ መለስ እያላችሁ አታደንቁርን» እያለ ነዉ ሕዝቡ። ሁለት በሉ።

ኢሕአዴግ ለአቶ መለስ ዜናዊ ቀብር ስነ-ስርዓት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮች አቃጥሏል። ወደ አምስት ሚሊዮን የሚጠጉ አባላት አሉት። አብዛኞቹ አንድ ለአምስት በሚለዉ አሰራር፣ ሌላ ሥራ የሌላቸው፣  ሕዝብን የሚሰልሉና የሚያስጨንቁ ካድሬዎች ናቸው። በርካታ የኢሕአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት ዶላር እየከፈሉ ፣ ልጆቻቸዉን እጅግ በጣም ዉድ በሆኑ ዉጭ አገር ባሉ ኮሌጆችና ትምህርት ቤቶች ያስተምራሉ። የአዲስ ፎርቹኑ ጋዜጠኛ ታምራት ወልደ ጊዮርጊስ እንደዘገበዉ፣ ለአባይ ግድብ ከሚያስፈልገው ወጭ ሁለት እጥፍ የሚሆን፣ ወደ ስምንት ቢሊዮን ዶላር የዉጭ ምንዛሪ፣ ከኢትዮጵያ በሚስጥር ተዘርፎ ወጥቷል። መቼም ወደ 99.9 በመቶ የሚሆነው ድሃዉ ሕዝባችን ዶላር በእጁ ይነካል ብሎ ማሰብ አስቸጋሪ ነዉ። በአብዛኛዉ ለአባይ ግድብ ገንዘብ የሚሰበስቡ የኢሕአዴግ መሪዎች፣ አባላትና ደጋፊዎቻቸዉ ናቸው ዶላር ወደ ዉጭ አገር የሚያሸሹት። [1]

እንግዲህ አንድ፣  እነዶር ቴዎድሮስ አዳኖም የዘነጉት ነገር ቢኖር፣ የተቃዋሚዎችና የአብዛኛዉ ሕዝብ ሌላው ጥያቄ፣ በአባይ ግድብ ላይ ሳይሆን፣ «ለአባይ ግንባታ ብላችሁ፣ ከሕዝብ የምትሰበስቡት ገንዘብ፣ ለአባይ ጥቅም ሳይሆን ወደ ባለስልጣናቱ  ካዝና አለመግባቱ ምን ማረጋገጫ አለን?» የሚል መሆኑን ነው።

እነ ዶር ቴዎድሮስ፣ በዚህ ጉዳይ ሊጠይቋቸው የሚችሉ፣  እንደ አቶ እስክንድር ነጋ፣ ርዮት አለሙ፣ ዉብሸት ታዬ ያሉ ጋዜጠኞችን በሽብርተኝነት ወንጀል ከሰዋቸዋል። በሕዝቡ ፊት የኢሕአዴግ ባለስልጣናትን ቻሌንጅ ሊያደርጉ የሚሞክሩ እንደ አቶ አንድዋለም አራጌ፣ አቶ ናትናኤል መኮንን፣ አቶ በቀለ ገርባ ያሉ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችን አስረዋቸዋል።  እንደ ፍትህ፣ ፍኖት ያሉ ነጻ ጋዜጦችን ዘግተዋል። ሶስት በሉ።

ዶር ቴዎድሮስ በዋሺንገትን ዲሲ የተናገሩት፣ አንድ የምጋራላቸው አባባል አለ። «የሃሰብ ልዩነቶች መኖራቸው በጣም ጤነኛ ነገር ነዉ» ባሉት እስማማለሁ። የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣ በሃሳብ ከሚለይዋቸዉ ጋር ለመነጋገርና ለመመካከር ፍቃደኛ የሆኑም ይመስለኛል።  የሃሳብ ልዩነቶች ሊያጣሉን፣ ሊለያዩንና ሊያቃቅሩን አይገባም። ነገር ግን፣ አንድ መረሳት የሌለበት ነጥብ ቢኖር፣  የሃሳብ ልዩነትን የማያክብረዉ፣ ቅድመ ሁኔታ እያስቀመጠ፣ አገር ቤት በሰላም ከሚታገሉ የፖለቲክ ድርጅቶች ጋር አልነጋገርም በማለት ግትር የሆነዉ፣ ለወንድማማችነትና ለብሄራዊ እርቅ በር የዘጋዉ፣  «ለምን ተቃዉሞ ተነሳብኝ ? »  ብሎ ዜጎችን የሚያስረዉና የሚያስጨንቀዉ፣ የርሳቸው ድርጅት ኢሕአዴግ መሆኑን ነዉ።

የሃስብ ልዩነቶች የሚንሸራሸሩባት፣ የመቻቻል፣ የመቀባባል ባህል የሰፈነባት ኢትዮጵያን ማየት የሚሹ ከሆነ፣ ዶር ቴዎድሮስ በቀዳሚነት ድርጅታቸውን ይፈትሹ ዘንድ እመክራቸዋለሁ።  እርሳቸዉና ጓዶቻቸው፣  የሚነሱ ተቃዉሞዎችን ለማውገዝ ከሚቸኩሉ፣ ተቃዉሞዎች ለምን እንደሚነሱ ቆም ብለዉ ቢመረምሩ፣  እንደ  ከፍተኛ አመራር አባል ለሚነሱ ጥያቄዎች መፍትሄ ቢፈልጉ መልካም ነዉ እላለሁ።

እንደዉም እዉነት እንነጋገር ከተባለ የአባይ ጉዳይ እንደ ጉዳይ መነሳትም አልነበረበት፤  የለበትምም። አባይ የፖለቲክ ጉዳይ ሳይሆን የአገር ጉዳይ ነዉ።

ዶር ቴዎድሮስ ሃሳብ ሊገባቸው አይገባም። እርሳቸዉና ድርጅታቸው በነርሱ በኩል ማድረግ ያለባቸዉን ካደረጉ፣ እርግጠኛ ነኝ፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድነትና በጋራ አገሩን ለማልማት፣ አባይን ለመገንባት ይነሳል። ኢትዮጵያዉያን በአባይ ጉዳይ ቀሳቀሽና አስታዋሽ አያስፈልጋቸውም። እንኳን፣   አንዱን አባይ፣  አሥር የአባይ አይነት ግድቦች የመስራት አቅሙና ጉልብቱ አላቸው። የሚያስፈልገው ይሄንን የሕዝብ ኃይል ማዳመጥ፣ ማክበር፣ ለሚያነሳቸውም  መሰረታዊ የመብት ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ብቻ ነዉ። አለቀ። ጆሮ ያለው፣ ይስማ፣ ልብ ያለው ያስተዉል።

በተለይም የሚከተሉትን በማድረግ፣  ኢሕአዴግ ግልጽ የሆኑ የፖሊሲ አቅጣጫ ለዉጦች ከወሰደ፣  እጅግ በጣም በርካታ የአገራችን ችግሮችና እንቆቅልሾች መፍትሄ ያገኛሉ ብዬ አምናለሁ።

  1. እስክንድር ነጋ፣ አንዱዋለም አራጌ፣ ርዮት አለሙ፣ ዉብሸት ታዬ፣ ናትናኤል መኮንን፣ በቀለ ገርባ የመሳሰሉ የሕሊና እስረኞች ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ። እነዚህን ወገኖች ሽብርተኞች ናቸው ብሎ ፈርጆ ማሰር፣   አስቂኝ ከመሆኑ ባሻገር፣  አሳፋሪና አሳሪዎቹንም ምን ያህል የጫካ አስተሳሰብ ያላቸው፣ ያነሱ መሆናቸውን የሚያሳይ ነዉ።
  1.  እንደ ምርጫ ቦርድ፣ ሜዲያ፣ ፍርድ ቤቶችን የመሳሰሉ ተቋማት፣ ነጻና ዴሞክራሲያዊ ማድረግ  የሚቻልበትን መንገድ ለመመካከርና፣  ስር የሰደዱ የፖለቲካ ችግሮችን ለመፍታት ይቻል ዘንድ፣ ከተቃዋሚዎች ጋር ድርድር/ውይይት ይጀመር። ኢትዮጵያ ቻይና አይደለችም። ተቃዋሚዎችን በመርገጥና በማፈን ብቸኛ አዉራ ገዢ ፓርቲ ሆኖ መቀጠል አይቻልም።

ይሄን አባባሌን  አንዳንድ  ኢሕአዴጎች ላይስማሙ፣ በጡንቻቸዉ ተማምነው፣ «ባለህበት ቀጥል» ሊባባሉ ይችላሉ። ነገር ግን እነርሱ ዉስጥ ያሉ፣ ብስለት ሊኖራቸው የሚችል ጥቂቶች፣  የ«ባለህበት ቀጥል» ፖለቲካ እንደማያዋጣና ኢሕአዴግ በሰብአዊ መብቶች መከበርና በዲሞራሲያዎዊ ለዉጦች ዙሪያ ትልቅ ማሻሻል ማድረግ እንደሚገባ ያጡታል ብዬ አላስብም።

  1. የአባይ ግድብ ፕሮጀክት ፣  የ«ኢሕአዴግ ፕሮጀክት» ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ ፕሮጀክት ይሆን ዘንድ ከኢሕአዴግ እንዲሁም ከተቃዋሚዎች የተወጣጡ ባለሞያዎች ያሉበት፣ ገለልተኛ የሆነ፣ የግልጽነትና የተጠያቂነትን አሰራር ያለው፣ ኮሚሽን እንዲመራ ይደረግ።

ያኔ፣ በአባይ ግድብ ዙሪያ በሚደረጉ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች ላይ የሚነሱ ተቃዉሞች አይኖሩም። ያኔ ገንዘብ ለማሰባሰብ ብዙ ዝግጅቶችም ማድረግም አያስፈልግም። በአጭር ጊዜ ዉስጥ፣ የሚያስፈልገዉን አራት ቢሊዮን ዶላር፣ አገር ቤት ያለዉ ድሃ ሕዝባችን የአንድ ወር ደሞዝን እንዲከፍል ታንቆ ሳይገደድ፣ ዳያስፖራው ብቻ፣ በራሱ አነሳሽነት ሊሸፍነዉ ይችላል።

እንግዲህ ዶር ቴዎድሮስም ሆነ ጓዶቻቸው ልብ ይላሉ ብዬ አስባለሁ። የሚነሱ ተቃዉሞዎችን አናንቀዉ፣ ለኢትዮጵያዉያን መሰረታዊ የመብት ጥያቄ ችላ ብለው የሚቀጥሉ ከሆነ ወደፊት የተወሳሰበ ሁኔታ ላይ ሊወድቁ እንደሚችሉ አሳስባለሁ። የሕዝብ መብት እየተረገጠ የሚደረግ የልማት እንቅስቃሴ ዘለቄታ አይኖርም። ምናልባት እድሜ ዘመኑን በጫካ ያሳለፈ ጠባብና እንጭጭ የኢሕአዴግ አመራር አባል፣ ይሄን ላይረዳ ይችላል። እንደ ዶር ቴዎድሮስ አዳኖም፣ አቶ ደምቀ መኮንን ያሉ፣  የተማሩ፣  በሳልና ትሁት ምሁራን የኢሕአዴግ አመራር አባላት ግን ይረዱኛል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/2591

ዲያስፖራው አምርሯል!

መንግስታችን ለአመት በዓል መዋያ ነው መሰል ሰሞኑን በየሀገራቱ እርጥባን የሚጠይቁ ሰዎችን አሰማርቷል፡፡ አብዛኛዎቹ ቦታዎችም …እግዜርም የስራህን ይስጥህ እኛ ግን የምንሰጥህ የለንም… ብለው እያባረሩት ነው…!

tastademo_OPPSLAG4_JA1_1020

ትላንት በኖርዌይ ኦስሎ ለሁለተኛ ጊዜ እንዲሁም ዛሬ ደግሞ በሳንዲያጎ ደጅ ጥናት የሄዱ የኢህአዴግ ባለስልታናትን ክፍ ብለዋቸዋል፡፡

ዲያስፖራው አምርሯል!

መንግስታችን ግን… ልመና ይቁም…  የሚለን ዘርፉን ብቻውን መቆጣጠር ፈልጎ ነው እንዴ…!?

http://www.abetokichaw.com/2013/04/29/

ከፋውንዴሽኑ ጀርባ… (ክፍል ፩) – ከተመስገን ደሳለኝ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

kom

ያለ ወቅቱ በደረሰ ዝናብ እየራሰች ያለችው አዲስ አበባ ዛሬም ከመለስ መንፈስ ተፅእኖ ነፃ አልወጣችም፤ ጣራና ግድግዳዎቿ እንዲህ በምስሉ እና በድርጅቱ አርማ መዥጎርጎሯን ያስተዋለ አንድ ቀልደኛ የባህር ማዶ ወዳጄ ‹‹እኔ ከሀገሬ ከወጣሁ በኋላ የኢህአዴግ ዋና ከተማ ሆነች እንዴ?›› ብሎ ፈገግ አሰኝቶኛል፡፡ በእርግጥ ይህችን ቀልድ ስንፍቃት የምናገኘው ቁም ነገር፡ከተማዋ በመለስ ውርስ ድንዛዜ ላይ መሆኗ፣ አስተዳደሯም ያለ ቅድመዝግጅት ‹‹አፍርሼ ካልሰራሁሽ›› በሚሉ ካድሬዎች ጫጫታና ሩጫ ልቧን እያጠፋት እንደሆነ፣ አንድ ፓርቲ ተመራጭ፣ አስመራጭ፣ ታዛቢ መሆኑን እና የመሳሰሉትን ነው፡፡ የአቶ መለስ ሞትም ወቅቱን የጠበቀ ባለመሆኑ ስርዓቱን እያንገጫገጨው ነው፡፡ በግሌ በመለስ ህልፈት ያለማዘን በሥነምግባር የመዝቀጥ ጉዳይ ነው ብዬ አላስብም፡፡ ምክንያቴ ሰውየው ክፉ አምባገነን ከመሆኑም በላይ በዙፋኑ ሙጭጭ እንዳለ ህይወቱ በማለፉ ነው፤ ታዲያ ይህንን ሰው እንዴት አድርገን ነበር ከስልጣን ማውረድ የምንችለው? መቼም አቅመቢሶች ከመሆንም አልፈን በተራራና ሸንተረር ሳይቀር የተከፋፈልን ለመሆናችን ከራሳችን በላይ መስካሪ የሚያሻን አይመስለኝም፡፡ እዚህች ከሩሲያዊው ሌኒን ህልፈት ጋር የተያያዘ አንድ ነገር ትዝ ስላለኝ ልንገራችሁ፡
እንደሚታወቀው ሌኒን የሩሲያ አብዮትን የመራ ሁነኛ ኮሚዩኒስት ቢሆንም፣ ምሁራዊ ሰውነቱ ከሌሎች አብዮተኞች በእጅጉ ይገዝፍ እንደነበረ ጠላቶቹም ሳይቀር የመሰከሩለት ጉዳይ ነው፡፡ እናም ህልፈቱ ሲሰማ፣ ሩሲያን በአይነ ቁራኛ ይከታተሉ የነበሩ ምዕራባውያን ድንጋጤ አደረባቸው፡፡ ከእነዚህ ሀገራት የአንዱ መሪም ድንጋጤውን እንዲህ ሲል ገልጾ ነበር አሉ፡-. ‹‹ሌኒን ሆይ፣ ባትወለድ መልካም ነበር፤ ከተወለድክ ደግሞ ትንሽ ብትቆይ ይሻል ነበር፤ ምክንያቱም ለማን ትተኽን እንደሄድክ እኔ አውቃለሁና!›› በእርግጥም ሌኒንን የተካው ባለ ብረት መዳፉ ጆሴፍ ስታሊን መሆኑን ስናስተውል የሰውየው ቁጭት ይገባናል፤ ግና ከአስር ወር በኋላም
ሊገባን ያልቻለው የእኛው መለስ ለማን ትቶን እንደሄደ ነው፡፡ ከስታሊንም ለባሱት? ወይስ… የሆነ ሆኖ መለስን ተክተው ከጀርባ የሚዘውሩትን አንጋፋ ታጋዮች ለጊዜው ባሉበት አቆይተን፣ ገብስ ገብሱን እንነጋገር ካልን የኃይለማርያም ደሳለኝ ሹመት ወቅቱን የጠበቀ አይደለም የሚለው አያከራክረንም፡፡ የሶስቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሹመትም እንዲሁ፡፡ የእነዚህ ድምር ውጤት ነው አገዛዙን ወቅቱን ባልጠበቀ አጀንዳ እንዲወጠር ያደረገው፡፡

pol
ያለወቅታቸው ‹‹ተከሰቱ›› ተብለው ሊጠቀሱ ከሚችሉ አጀንዳዎች መካከል ‹‹የመለስ ፋውንዴሽን ምስረታ›› አንዱ ነው፡፡ በእርግጥ መለስ ባይሞት ኖሮ፤ ከሞተም በኋላ ስርዓተ ቀብሩ ትኩረት ባይስብ ኖሮ፤ ከተቀበረ በኋላም ‹‹ሌጋሲው ይቀጥላል›› ባይባል ኖሮ፤ ከሌጋሲው ውስጥም ‹‹ራዕዩ ፈለቀ›› ባይባል ኖሮ… ‹‹ፋውንዴሽን›› ጂኒ ቋልቋል… ባልተከታተለብን ነበር እያልን መቆጨታችን አይቀሬ ነው፡፡ ኢህአዴግ ከመለስ ህልፈት በኋላ ‹‹የመለስ ራዕይ›› እያለ መጮኹ አናዳጅ ብቻ ሳይሆን ‹‹እመራዋለሁ›› ለሚለው ህዝብም ያለውን ንቀት የሚያሳይ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ይህ አይነቱ ፕሮፓጋንዳም ነው ‹‹መለስ ኖሮ፣ ራዕዩ በሞተ›› የሚያስብለው (አሁን የፋውንዴሽኑ ምስረታ ዕለት የተከሰቱ ፖለቲካዊ አንድምታ ያላቸውን ጉዳዮች በአዲስ መስመር ጨርፎ ወደማየቱ እንለፍ) ፋውንዴሽኑ ደረጃውን የጠበቀ መናፈሻ፣ ቤተ መፅሀፍት (የመለስ ስራዎች በአማርኛ ተተርጉመው ይቀመጡበታልም) እና የተለያዩ መዝናኛዎችን ጨምሮ አስክሬኑ የሚያርፍበት ልዩ ስፍራ እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡ በግልባጩ ግንባታው የሚካሄድበት ቦታ አዲስ አበባ ነው ከማለት ባለፈ በትክክል የት አካባቢ እንደሆነ ተለይቶ አልተገለፀም፡፡ ሆኖም ለግንባታው ተብሎ በግዴታ በርከት ያሉ መኖሪያ ቤቶች ከይዞታቸው እንደሚነሱ ተነግሯል፡፡ በግሌ ይህ አግባብ ነው ብዬ አላስብም፡፡ ምንም እንኳ በ‹‹ስመ-ልማት›› እየተደረገ ያለውን ማፈናቀል ጠቀሜታው የሀገር ነው ብለን ልንወስደው ብንችልም፤ ይህ ግን… (አጀንዳዬ የፋውንዴሽኑን ጥቅም ወይም ጉጂ ጎን መተንተን ሳይሆን፣ በምስረታው እለት የታዩ ጥቂት ተመንዛሪ ክስተቶችን መተንተን ነው ብያለሁና ወደዚያው አልፋለሁ)
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝከዚህ ቀደም የህወሓት አመራር አባላት የመለስ ህልፈትን ተከትሎ በሁለት ጎራ ተቧድነው ‹‹ቀዝቃዛ ጦርነት›› ውስጥ መግባታቸውን ያመላክታሉ ያልኳቸውን ፍንጮች ጠቅሼ መነጋገራችን አይዘነጋም፡፡ (‹‹ቀዝቃዛው ጦርነት፡- ከአመታት በፊት ዓለም በአሜሪካን እና
ሶቭየት ህብረት ፊት አውራሪነት በርዕዮተ-ዓለም ተከፍሎ ሲፋለም ነበር፤ ያለታንክና መድፍ፤ ያለ ተዋጊ ወታደርና ያለ አዛዥ ጄነራል፤ ፍልሚያው ሟችም ሆነ ቁስለኛ፣ አሊያም ምርኮኛ አልነበረውም፤ የርዕዮተ-ዓለምን ልዩነት በበላይነት ለመወጣት ነበርና፡፡ አንደኛው ከሌላኛው ጎራ ከቻለ ሀገርን፣ ካልቻለም ስልጣን ላይ ያለ ግለሰብን ለማስኮብለል ይቀምራል፣ ያሴራል፣ ይሰልላል…፤ ይህንን ሁኔታ ነው የፖለቲካ ተንታኞች ‹‹ቀዝቃዛው ጦርነት›› (Cold War) ያሉት) ዛሬ ደግሞ የህወሓት የአመራር አባላት በእንዲህ አይነት ጦርነት መጠመዳቸውን ጆሮአችን እስኪግል እየሰማን ነው፤ ልዩነቱ የህወሓት ችግር ርዕዮተ-ዓለምን መሰረት ያደረገ አለመሆኑ ነው፡፡ በእርግጥ ህወሓት እንኳን ዛሬ፣ በትልቁ የተሰነጠቀ ጊዜም (በ1993 ዓ.ም.) ርዕዮተ-ዓለም አላጨቃጨቀውም፡፡ የስዬ አብርሃ ወደ አንድነት መግባትም ሆነ፣ የእነ ገብሩ አስራት በ‹‹ሶሻል ዴሞክራሲ›› አስተሳሰብ የሚመራውን አረናን መመስረት የልዩነቱ ምክንያት አልነበረም፡፡ እነገብሩ አረናን ለመመስረት ሲንቀሳቀሱ፣ በክፍፍሉ ወቅት ‹‹የቡድን አባታቸው›› እንደነበር የሚነገርለት ተወልደ ወ/ማርያም የአዲሱ ፓርቲ መስራች እንዲሆን ሲጠየቅ ‹‹ርዕዮተ-ዓለማችሁ ‘አብዮታዊ ዴሞክራሲ’ ከሆነ ብቻ ነው የምቀላቀለው›› አለ መባሉ መከራከሪያችንን ያጠነክረዋል፡፡
እናም የህወሓት ሰዎች (ከእነ አረጋዊና ግደይ ዘርአፅዮን ዘመን ጀምሮ) ስልጣን እንጂ፣ የፖለቲካ አመለካከት የፀብ መንስኤ ሆኗቸው አያውቅም፡፡ የዘንድሮውም ‹‹ቀዝቃዛ ጦርነት›› ቡድተኝነትና የስልጣን ፍላጎት የፈጠረው ቅራኔ ነው፤ አሊያም ከጆርጅ ኦርዌል ‹‹እንሰሳት ሁሉ እኩል ናቸው፤ አንዳንድ እንሰሳት ግን ከሌሎች ይበልጥ እኩል ናቸው›› መንፈስ የተናጠቀ ሊሆን ይችላል፡፡ እንዲሁም የፋውንዴሽኑ ምስረታ የእነአዜብን ቡድን የሚያጠናክር ፖለቲካዊ አንድምታ አለው፡፡ በእነአባይ ፀሀዬ ቡድን ውስጥ ከተሰባሰቡት አብዛኛው ለመለስ ያደሩት ፈርተው እንጂ አምነውበት ወይም ወደውት አይደለም፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ከእነርሱ ቡድን አንድም
የአመራር አባል የፋውንዴሽኑ ቦርድ አባል ሆኖ ያልተመረጠው፡፡
የሁለቱ ቡድኖች አሰላለፍ በ‹‹አባይ-ደብረፅዮ››ን እና በ‹‹አዜብ-አባይ ወልዱ›› አስተባባሪነት መሆኑን ሰምተናል (በነገራችን ላይ ከ1983-1993 ዓ.ም ኢህአዴግ ‹‹ሁሉም የግንባሩ አባል ፓርቲዎች እኩል ናቸው፤ ህወሓት ግን ከሁሉም ይበልጣል›› የሚል ያልተፃፈ ህግ ነበረው፡፡ በ93ቱ ክፍፍል አብዛኛው የህወሓት አመራር ከተባረረ በኋላ ደግሞ ያ ህግ ‹‹ሁሉም የኢህአዴግ የአመራር አባላት እኩል ናቸው፤ መለስ ግን ከሁሉም ይበልጣል›› ወደሚል ተቀይሮ ነበር፡፡ አሁን መለስ አልፏል፤ እናም አፍጦ የመጣው ጥያቄ ‹‹ከሁሉም የሚበልጠው ማን ነው?›› የሚለው ነው ብል ማጋነን አይሆንም)
የሆነ ሆኖ በ‹‹የመለስ ፋውንዴሽን ምስረታ›› ወቅት የታዩ ሁነቶች ሁለት ነገር ይፋ አድርገዋል፡፡ የመጀመሪያው በእነአዜብ ጎራ እነማን እንደተሰለፉ የሚያሳይ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ የጦር አዛዦችም ፍልሚያውን መቀላቀላቸውን ማመላከቱ ነው፡፡ የእነአዲሱ ለገሰ-ብአዴን ገና ከመነሻው ከእነአዜብ ጎን መሰለፉ ይታወቃል፡፡ በፋውንዴሽኑ ምስረታ ወቅትም ይኸው ነው የታየው፡፡ ‹‹የጠቅላይ ሚንስትር መለስ የሌጋሲ ኮሚቴ›› ሰብሳቢ የነበረው አዲሱ ለገሰ፣ የስብሰባውን አካሄድ እየተከታተለ የተጣመመውን ሲያቃና፣ ማጣመም የፈለገውን ደግሞ ሲገፋ ተስተውሏል፡፡ ለምሳሌ የብአዴኑ ካሳ ተ/ብርሃን የፋውንዴሽኑ የቦርድ አባል ሆኖ መመረጡን ተቃውሞ በእርሱ ምትክ ሌላ ሰው እንዲመረጥ ሲጠይቅ፣ አዲሱ ስራው ጊዜን የማይሻማና ቦርዱን የሚመለከት ነገር ሲኖር ብቻ ውሳኔ መስጠት እንደሆነ ጠቅሶ ካሳ መቀጠል እንዳለበት ሲናገር፣ የመድረክ መሪው በፍጥነት ሃሳቡን ቤቱ እጅ በማውጣት እንዲደግፍ ቀስቅሶ የሰውየውን ተቃውሞ ውድቅ አድርጓል፡፡ በግልባጩ የኦህዴዱ ሙክታር ከድር ሲመረጥ፣ የብአዴኑ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) የሴቶች ተሳትፎ አናሳ መሆኑን መግለፁን ተከትሎ፣ ሙክታር ‹‹ድርጅቶቹ ራሳቸው ለምን አይጠቁሙም?›› ገና ከማለቱ፣ እነአዲሱ ተሽቀዳድመው ‹‹ከአንተ ነው መጀመር ያለበት›› የሚል ግፊት በማድረግ የተመረጠውን ሙክታር ከድርን በ‹‹ድርጅታዊ አሰራር›› ከጨዋታ ውጪ አድርገው፣ አስቴር ማሞን አስገብተዋል፡፡ ሶፍያን አህመድ፣ ቴዎድሮስ አድሀኖም፣ ቴዎድሮስ ሀጎስም የቦርዱ አባል ሆነው ተመርጠዋል፡፡ በመጨረሻም አዜብ የፋውንዴሽኑ ፕሬዚዳንት ሆና ስትመረጥ፣ ምክትሏ ደግሞ የብአዴኑ ካሳ ተ/ብርሃን እንዲሆን ተደርጓል (ሁሉም በእነአዜብ ቡድን ስር ናቸው) የሁለቱም ቡድን አባላት ‹‹ቃየል››ን እንጂ ‹‹አቤል››ን መሆን አይፈልጉም፡፡ እናም የከፋ ነገር ከመጣ ‹‹ቃየላዊ›› እርምጃዎችን እስከመውሰድ ሊደርሱ ይችላሉ፡፡ በእርግጥ ይህ ሁኔታም ሊሳካ የሚችለው የታጠቀውን ኃይል ፍላጎት ታሳቢ አድርጎ ለተንቀሳቀሰ ኃይል ነው፡፡ እናም ከእርስ በእርስ ግጭቱ በበላይነት ለመውጣት እንቅልፍ አጥተው እየሰሩ (እያሴሩ) ነው (እስከአሁን ባለው ሁኔታ ብአዴን ሙሉ ድጋፍ እያደረገለት ያለው የእነአባይ ወልዱ ቡድን ‹‹የተሻለ›› ሊባል የሚችል የበላይነት አሳይቷል)፡፡ በዚህን ጊዜም ከድንገቴ አደጋ ራስን መከላከል አስፈላጊ በመሆኑ የግል ጥበቃቸውን አጠናክረዋል፡፡ ለምሳሌ በረከት ስምዖን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጠባቂዎቹን ከሁለት ወደ ስድስት አሳድጓል፤ ሁለት ተጨማሪ መኪናዎችም ከፊትና ኋላ ሆነው እንዲያጅቡት አሰማርቷል፡፡ ባለፈው ወር በተካሄደው የግንባሩ ዘጠነኛ ጉባኤ አዜብ መስፍን ‹‹መለስ በስልጣን ላይ እያለ ደሞዙ ስለማይበቃን ብዙውን ጊዜ ከወር እስከ ወር ቀለብ ሳያልቅብን ለመድረስ እንቸገር ነበር›› የሚል አንድምታ ያለው ንግግር አድርጋ ካለቃቀሰች በኋላ ‹‹በደሞዝ (በፔሮል) የሚኖረው ባለስልጣን መለስ ብቻ ነው›› ስትል ማድመጣችን ይታወሳል፡፡ በእርግጥ አዜብ ልታስተላልፍ የፈለገችውን መልዕክት አንጓ ከ‹‹ሰሙ›› ለይተን ስናወጣው ‹‹ቅልጥ ባለ ዘረፋ ላይ የተሰማራችሁ ባለስልጣናት በልዩነታችን ላይ ካልተግባባን ላጋልጣችሁእንደምችል እንድታውቁት›› የሚል ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ የበረከት ‹‹ቴሌቪዥን ጣቢያ››ም ይህንን ሃሳብ በተለየ ሁኔታ ያስተላለፈው ትርጉሙ ሳይገባው ቀርቶ አይመስለኝም፡፡ እነዚህን ኩነቶችም ስንጨምቃቸው ‹‹ህወሓት የውስጥ ችግሩ ከቀን ወደ ቀን እየባሰ ሄዶበታል›› የሚል ድምዳሜ ላይ ያደርሱናል (የአዜብን መልዕክት ባደመጥን ማግስት አራት ኪሎ አካባቢ ከአንድ የአረና አመራር አባል ጋር ድንገት ተገናኝተን ይህንን ሁኔታ አንስተን ስናወራ እንዲህ አለኝ፡- ‹‹እነርሱ ቀልደኞች ናቸው፤ በ1993 ዓ.ም የክፍፍሉ ወቅት መለስ ለቤተመንግስቱ የተመደበው ሁለት ሚሊዮን ባጀት የት እንደሚገባ ሲጠየቅ ‹ይሄ ግቢ እኮ ከምንሊክ ዘመን ጀምሮ ጮማ የለመደ ነው› ብሎ አድበስብሶ አልፎት እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ በተቀረ አዜብ ‹በመለስ ደመወዝ ብቻ ስለምተዳደር ሽሮና በርበሬ እያለቀብኝ እቸገራለሁ› ማለቷ ከእርሷ ጋር የአቋም ልዩነት ላላቸው የህወሓት አመራር በጎንዮሽ የማስፈራሪያ መልዕክት ከማስተላለፍ የዘለለ ቁም-ነገር ያለው አይመስለኝም፡፡››)

aye

ሌላኛው በዕለቱ የታየው ዓብይ ጉዳይ መከላከያን የሚመለከተው ነው፡፡ የተመረጡት ሰዎች ውክልናቸው ተቋምን መሰረት ያደረገ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በዚህ መሰረትም መከላከያን ወክለው የቀረቡት ጄነራል ሳሞራ የኑስና ጄነራል ሰዓረ መኮንን ናቸው፤ ሳሞራ ሙሉ ጀኔራል ነው፣ ሰዓረ ደግሞ ሌፍቴናንት፡፡ ስለዚህም መከላከያን ወክሎ የቦርድ አባል መሆን ያለበት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ባለ አራት ኮከብ ጄነራል የሆነው ሳሞራ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ የሆነውም ይኸው ነው፤ በዚህም ማንም አልተቃወመም-ከጄነራል ሰዓረ በቀር፡፡ ለምን? ሁለቱ ጄነራሎች በግል ስለማይግባቡ? በጥቅም ተጋጭተው? ሰዓረ ‹‹ሳሞራ አይመጥንም›› ብሎ አስቦ? እውነት ጉዳዩ የሁለቱ ብቻ ነው? ወይስ የሰዓረ ተቃውሞ መነሻ ምንድር ነው? …ይህንን ተቃውሞ የግለሰብ አድርገን እንዳንወስደው የሚያስገድዱ ገፊ ምክንያቶች የምላቸውን መጥቀስ እችላለሁ፡- ሁለቱም ተመሳሳይ ተቋም ወክለው መቅረባቸው አንዱ ነው፤ ሁለቱም ወታደሮች መሆናቸው ሌላኛው ነው (የወታደር ዲሲፕሊን በተለይም የኢህአዴግ ወታደራዊ አደረጃጀት ከታች ወደላይ ተቃውሞን እንደማያበረታታ ማንም አይጠፋውም) ሆኖም ‹‹የሳሞራን የቦርድ አባል መሆን በምን አያችሁት?›› ሲል የተቃውሞ ድምፁን አሰምቷል፡፡ በተጨማሪም ሰዓረ ያ ሁሉ ህዝብ በተሰበሰበበት አዳራሽ የሳሞራን ስም ሲያነሳ በሰራዊቱ ደንብ መሰረት በማዕረግ ስሙ አልነበረም፡፡ ለዚህም ነው በዕለቱ የተከሰተው ነገር ሁለቱ ጄነራሎች እያራመዱት ያለውን ልዩነት የሚያሳይ ነው የሚለውን መከራከሪያ የሚያጠናክረው፡፡ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ለሚከታተል የሠራዊቱን ወሳኝ ጄነራሎች ከጎኑ ማሰለፍ የቻለ ማንኛውም ቡድን ዳዊት የማይኖርበት ጎልያድ ሊሆን እንደሚችል አይጠፋውም፡፡ እናም ይህ ኩነት አንደኛ ዓመቱን ሊደፍን እየተቃረበ ላለው የሁለቱ ቡድኖች ፍጥጫ የመቋጫው ቀናት እየቀረበ እንደሆነ የሚያመላክት ይመስለኛል (በነገራችን ላይ በመከላከያ ውስጥ ከሳሞራ ቀጥሎ ባለ የስልጣን ወንበር ላይ የምናገኘው በተመሳሳይ ማዕረግ የሚገኙ ሶስት አቻ ጄነራሎችን ነው፡፡ ሁለቱ ጄነራል አበባው ታደሰ እና ጄነራል ሰዓረ መኮንን ናቸው፡፡ እነዚህ ጄነራሎች አንም ቀን ተስማምተው ሰርተው አያውቁም፡፡ ስልጣናቸውና ኃላፊነታቸው ተመሳሳይ ቢሆንም አበባው የሚመራው ቢሮ በተሰሚነት ጎላ ያለ ነው፡፡ …ሳሞራ በግልፅ ‹‹በዚህ ቀን›› ብሎ ባይናገርም ከኤታማዦር ሹምነቱ የመልቀቅ እቅድ አለው፡፡ በአሁኑ አሰላለፍም ከእነአዜብ ጎን ይመደባል፡፡ አበባውና ሰዓረ ደግሞ የእርሱን ቦታ ይፈልጉታል፡፡ አበባው የሳሞራ የቅርብ ሰው ነው፡፡ ከሰዓረ ጋር ያለው ግጭትም ከሳሞራ ጋር ካለው ግንኙነት ጋር ይያያዛል)
የሆነ ሆኖ ‹‹ቀዝቃዛው ጦርነት››ን በሚመለከት ተጨማሪ ነጥብ ልጥቀስ፡፡ ከቀኑ ስብሰባ በኋላ በሸራተን ሆቴል ለፋውንዴሽኑ ገቢ ማሰባሰቢያ አንድ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ነበር፡፡ በዚህ ፕሮግራም ላይ የጎረቤት ሀገራትን ጨምሮ የክልል አስተዳደሮች ‹‹አቅማችን ይመጥናል›› ያሉትን ያህል የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል፡፡ ከሁሉም ቀድሞ አንድ ሚሊዮን ብር ያዋጣው እነአዲሱ ለገሰ እንደግል ንብረታቸው የሚቆጥሩት ‹‹ጥረት ኢንዶውመንት›› ሲሆን፣ የአላሙዲ ‹‹ሚድሮክ ኢትዮጵያ››ም ሃያ አምስት ሚሊዮን ብር ለመለገስ ቃል ገብቷል፡፡ ትኩረቴን የሳበው ግን ይህ አይደለም፤ ገቢና ወጪው ከህዝብ ብቻ ሳይሆን ከውጪ ኦዲተርም አይን የተሰወረ ነው
የሚባለው እጅግ ባለፀጋው የህወሓቱ ‹‹ኤፈርት›› በዕለቱ ሰባራ ሳንቲም ለማዋጣት ቃል አለመግባቱ እንጂ፡፡ ለምን? ኤፈርት በእነአዜብ ስር ከመሆኑ አኳያ ለትችት ያጋልጠናል በሚል? ወይስ ገና ያልተደረሰበት እንቆቅልሽ ይኖር ይሆን? ጥያቄው ይህ ነው፡፡ የዚህን መልስ ጨምሮ ከላይ ያነሳኋቸው ነጥቦች ሲፍታቱ ልዩነቱን እና አሰላላፉን ያጎሉታል ብዬ አስባለሁ፡፡
እንደመውጫ
በሀገራችን ላይ ‹‹ለውጥ አመጣለሁ›› የሚለው የተቀውሞ እንቅስቃሴ ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣ ጀምሮ ‹‹ይህን ዓመት አያልፍም!›› በሚል ሟርት ሲጠመድ፣ ድርጅቱ ግን ሃያ ሁለተኛ ዓመቱን ሻማ ለኩሶ ሊያከብር ቀናት ብቻ ቀርተውታል፡፡ ዘንድሮም የመለስን ሞት ወይም የግንባሩን መከፋፈል ብቻ ስናመነዥክ የቋመጥንለት ለውጥ የውሃ ሽታ ሆኖ ነገሩ ሁሉ ‹‹የሞትንም እኛ፤ ያለንም…›› እንዳይሆን እሰጋለሁ፡፡ እናም በላያችን ላይ እያመፀ ያለውን ፍርሃት ማረቅ ያስፈልጋል፤ ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነት ያስፈልገናል፤ ከኢህአዴግ በኃላም ሊኖር ስለሚገባው ለውጥ መነጋገር ያስፈልጋል፤ ስርዓቱ ሀገር የሚጠቅም አለመሆኑን በበቂ ሁኔታ ገብቶናልና፣ የርዕዮተ-ዓለም ወይም የፖሊሲ ድክመቱን በምክንያትና አመክንዮ (ሎጂክ) እየተነተንን ብቻ ተጨማሪ ጊዜ ማባከኑ ፋይዳ የለውም፡፡ ፋይዳ ያለው በሰላማዊ መንገድ አደባባይ ወጥቶ የስርዓት ለውጥ ማድረግ ነው፤ ትንተናዎችም ይህ አይነቱን እንቅስቃሴ ወደ መሬት ማውረድ የሚቻልበት እና ከኢህአዴግ በኋላስ? የሚለው ላይ ሲያተኩሩ ነው፡፡

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/2570

በአዲሱ ሃይማኖቷ “የኦርቶዶክስ እምነትን ስህተት ነው” ያለችው አርቲስት ጀማነሽ ሰለሞን ታሰረች

“የኢትዮጵያን ትንሣኤ ሊያረጋግጥ ሃያል ባለስልጣን ነብዩ ኤልያስ ከብሔረ ህያዋን ጳጉሜ 1/2003 ዓ.ም ወደ ምድር መጥቶ በመካከላችን ይገኛል፣ ኦርቶዶክስ የሚባለው የሃይማኖት ስም ስህተት ነው ተዋህዶ ነው መባል ያለበት፣ ሰንበት ቅዳሜ ብቻ ነው፣ መለበስ ያለበት እግዚአብሔር ለኖህ ቃል ኪዳን የገባበትን ቀስተ ደመና ቀለማት ያካተተ ጥለት ያላቸው ነጭ አልባሳት ናቸው” የሚል አዲስ እምነት እያራመደች ያለችውና ነብዩ ኤልያስ ወደ ምድር እንደመጣ የምታምነው አርቲስት ጀማነሽ ሰለሞን አዲስ ባቋቋመችው እምነት የተነሳ መታሰሯን ከአዲስ አበባ አዲስ አድማስ ጋዜጣ ዘገበ።

jiema
በተለያዩ የመድረክ ቴያትሮች፣ በቴሌቪዥንና በሬዲዮ ድራማዎች በተለይም “ገመና” በተሰኘው ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ የእናትነት ገፀ – ባህሪን ተላብሳ በመተወን የምትታወቀው አርቲስት ጀማነሽ ሰለሞን ታሰረች፡፡ አርቲስቷ ማክሰኞ ማታ ተይዛ አራት ኪሎ የሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ከታሰረች በኋላ ረቡዕ አመሻሽ ላይ ወደ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ መዛወሯንና ከእርሷ ጋር ሌላ አንዲት ሴትና ሁለት ወንዶች መታሰራቸውን በስፍራው ተገኝተን አረጋግጠናል ያለው የአዲስ አድማስ ዘገባ አርቲስት ጀማነሽና አብረዋት የታሰሩት ግለሰቦች ሃሙስ እለት አፍንጮ በር መንገድ አዲስ አበባ ሬስቶራንት አካባቢ በሚገኝ የመጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት ቀርበው ጉዳያቸው የታየ ሲሆን በድጋሚ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡም ዘግቧል።

ጋዜጣው ዘገባውን በመቀጠል “አርቲስቷንና አብረዋት የታሰሩትን ሰዎች ለመጠየቅ ወደ ስፍራው ከመጡ ግለሰቦች ለመረዳት እንደቻልነው፤ አርቲስቷና አብረዋት ያሉት ሰዎች የታሰሩት “ማህበረ ስላሴ ዘ ደቂቀ ኤልያስ” ከተባለው ማህበራቸውና ከሀይማኖት ጉዳይ ጋር በተያያዘ እንደሆነ ጠቁመው ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ ከአርቲስቷ ጋር የታሰሩት አንድ የሃይማኖት አባት፤ ጉዳዩ በፍርድ ቤት የተያዘ በመሆኑ ከፍርድ ሂደቱ በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ፣ አሁን ምንም አይነት ዝርዝር መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ነግረውናል፡፡ አርቲስት ጀማነሽን ሊጠይቋት የመጡ ሰዎችን ለማነጋገር ስትወጣ በተመለከትናት ጊዜ በፈገግታ የታጀበች ሲሆን ጠያቂዎቿ “እንዴት ነሽ ተመቸሽ?” ብለው ሲጠይቋት “እግዚአብሔር ያለበት ቦታ ሁሉ ምቹ ነው” ስትል ምላሽ ሰጥታለች፡፡ አርቲስቷ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ “ተዋህዶ” በሚል ሃይማኖት ውስጥ ተሣታፊ በመሆን አነጋጋሪ ሆና መቆየቷ የሚታወስ ነው፡፡” ብሏል።

“ወረዳ ዘጠኝ ፖሊስ ጣቢያ በተገኘን ጊዜ የሃይማኖቱ ተከታዮች የሚለብሱት የቀስተደመና ቀለማት ያሉት ነጠላ አጣፍታ፣ ፀጉሯንም የቀስተ ደመና ቀለም ዙሪያውን ባቀለመው ሻሽ አስራለች፡፡ ማህበረ ስላሴ ዘ ደቂቀ ኤልያስ “የኢትዮጵያን ትንሣኤ ሊያረጋግጥ ሃያል ባለስልጣን ነብዩ ኤልያስ ከብሔረ ህያዋን ጳጉሜ 1/2003 ዓ.ም ወደ ምድር መጥቶ በመካከላችን ይገኛል፣ ኦርቶዶክስ የሚባለው የሃይማኖት ስም ስህተት ነው ተዋህዶ ነው መባል ያለበት፣ ሰንበት ቅዳሜ ብቻ ነው፣ መለበስ ያለበት እግዚአብሔር ለኖህ ቃል ኪዳን የገባበትን ቀስተ ደመና ቀለማት ያካተተ ጥለት ያላቸው ነጭ አልባሳት ናቸው” የሚሉትን የተለያዩ ጉባኤዎችን እያዘጋጀ የሚያስተምር ማህበር መሆኑን ያነጋገርናቸው የማህበሩ አባላት ገልፀውልናል፡፡ በተለያዩ ገዳማትም የሀይማኖቱ አራማጆች እንደሚገኙና እንደሚያስተምሩ ያገኘናቸው የሃይማኖቱ ተከታዮች ነግረውናል፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ ከፖሊስ መረጃ ለማግኘት ጥረት ብናደርግም፣ ከመምሪያው የተፃፈ ፈቃድ ያስፈልጋል በሚል የወረዳው ፖሊስ መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል፡፡” በማለት ዘገባውን አጠናቋል።

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/2561

Breaking News: Ethiopians in Norway Chased TPLF Ambassador

Norway police stopped meeting in Tasta Bydelshus

The police came out with three cars and six policemen and stopped a meeting of Tasta bydelshus where the atmosphere was becoming so very irritably among the more than 300 Ethiopian origin attendees.

The 300 attendees were Ethiopian asylum seekers or people with Ethiopian background. The police feared that it would get completely out of control when people in the audience went to the hard verbal confrontation against two representatives from the Ethiopian Embassy in Stockholm who had called for and chaired the meeting.Breaking News: Ethiopians in Norway Chased TPLF Ambassador

The police gave the first message that all protesters to leave the meeting while the two embassy people and their potential supporters can be seated. This denied the attendees protesters, and several feared it would come to an open confrontation between police and people in the audience. Then, specific efforts manager Øyvind Sveinsvoll of Rogaland police to stop the meeting and clear the room.

It was a wise decision, said several of those present protesters. They did not want the two embassy people should be left as “victors” while they were evicted.

– Our goal was to stop the meeting. We managed, says one of them to Eve magazine.

Had to isolate embassy people

The atmosphere was tense that the police chose to isolate the two embassy people from the rest of the participants. TheyBreaking News: Ethiopians in Norway Chased TPLF escorted them out to a private car that carried them away from the area. The 300 attendees were then drop out of the courtroom.

There was general consul at the Ethiopian Embassy, ​​Abay Mebrat Beyene, who would chair the meeting with embassy secretary. The main theme was collecting money in the Ethiopian exile to a very controversial prestige project for the regime in Ethiopia.

Mass demonstrations abroad

The Ethiopian authorities have tried to keep similar “recovery meetings” both in South Africa, Saudi Arabia, the U.S. and Germany, and each time meetings have ended in massive demonstrations against human rights violations in Ethiopia. People imprisoned without trial, free elections are abolished, freedom of speech likewise, newspapers are state controlled and hundreds of journalists imprisoned.

http://ecadforum.com

ግጭቱን ማን ለኮሰው? (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

ቀኑ ማክሰኞ፣ ጥቅምት 22 1998 ዓ.ም፤ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ገደማ… አንድ የከተማ አንበሳ አውቶብስ ተሳፋሪ ሳይጭን ከመርካቶ ተነስቶ ወደ ጎማ ቁጠባ አቅጣጫ በባዶ እየከነፈ ቁልቁል ወርዶ ..ተ/ሃይማኖት ቤ/ክርስቲያን አደባባይን ከዞረ በኋላ ጥግ ይዞ ቆመ። ሹፌሩ አውቶብሱን ገትሮ ወዲያው ከአካባቢው ጠፋ። ለሁለት ሰዓት ገደማ አውቶብሱ እንደተገሸረ ቆየ።…በዚህ ቅፅበት አንዲት ነጭ ቶዮታ ፒካፕ (ታርጋ የሌላት ወይም ያለጠፈች) ከሱማሌ ተራ አቅጣጫ በከፍተኛ ፍጥነት እየከነፈች ከመጣች በኋላ < በላይ ተክሉ ኬክ> ቤትን አለፍ ብላ ቆመች። ከሹፌሩ ጎን ሲቪል የለበሰና ኮፍያ ያጠለቀ ሰው የተቀመጠ ሲሆን ከመኪናው ጋር ከተገጠመው ሬዲዮ መገናኛ በተጨማሪ ሁለት ተንቀሳቃሽ ስልኮችን ይዟል።… 25 ወጠምሻዎች፣ ሁሉም ረዘም- ወፈር ያሉ ዱላዎችን፣ ገሚሶቹ ደግሞ ገጀራ እንደጨበጡ እንዲሁም ከመካከላቸው ሁለቱ አነስተኛ ጀሪካን እንደያዙ…ከመኪናዋ ዘለው ወረዱ። ሁሉም የተቀዳደ ተመሳሳይ ድሪቶ አጥልቀዋል፤ « አደገኛ ቦዘኔ» መሆናቸው ነው። ነገር ግን « ሆን ተብሎ » የተዘጋጀ ድሪቶ እንደሆነ የሚያሳብቀው ….በግልፅ የሚታየው የሁሉም ፈርጣማ ጡንቻ ከጥሩ እንክብካቤ ጋር በስፖርት የዳበረና ወታደራዊ አቋም እንዲይዝ ተደርጎ የተገነባ መሆኑ ነበር።

ho

ከመኪናዋ ዘለው ከወረዱ በኋላ ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ « አትነሳም ወይ…አትነሳም ወይ …ወያኔ…ወያኔ..» እያሉ በመጮህ አንበሳ አውቶብሱን ተጠጉ። በያዙት የብረት ዱላና ስለታማ ገጀራ አውቶብሱን እንክትክቱን ካወጡ በኋላ በያዙት ነዳጅ አርከፍክፈው አቃጠሉት፤…ተመሳሳይ ጩኸትና ቅስቀሳ እያሰሙ ሽቅብ ወደ ሲኒማ ራስ አመሩ። ነጯ መኪና ከኋላ ደርሳ ሁሉንም ጫነች…ከዛም ወደፊት በፍጥነት እየካለበች አዲስ ከተማ ት/ቤት አካባቢ ደረሰች። ወጠምሻዎቹ ..የ <አትነሳም ወይ…> ቅስቀሳቸውን ሲቀጥሉ.. እግረመንገዳቸውን በቅርብ ርቀት የሚገኘው የቴሌ መ/ቤት ላይ ድንጋይ በመወርወርና ከደጃፍ ቆመው የነበሩ ሁለት መኪኖችን መሰባበር ይዘዋል። ከዚሁ ጐን ለጎን በመ/ቤቱ ግቢ የታጠቁ ፌደራል ፖሊሶች ከድራማው መጀመር ቀደም ብሎ እንዲገቡ ተደርጎ ነበር። ያ ድርጊት ወይም ድራማ ሲፈፀም አይተው እንዳላዩ በማለፍ ቀጣዩን ይጠብቁ እንደነበረ በሰአታት ልዩነት አፈሙዝ በንፁሃን ላይ ሰድረው ይወስዱት የነበረው የጭካኔ እርምጃ በቂ ማመላከቻ ነበር፤ ዘግይቶ የሆነውም ይኸው ነው።..

በሰኔ ወር ግድያ ሲፈፀም በመጀመሪያ ኢላማ የነበረው ይህ ት/ቤት ነበር፤ በዛ ድርጊት ገና ያልሻረ ቁስል አለ። በሌሎች አካባቢዎችና ከተሞች የነበረው የተዳፈነ የተቃውሞ ቁስል ከዚህ የተለየ አልነበረም። በሕወሐት/ኢህአዴግ አስተዳደር የተንገሸገሸው ሕዝብ..እንኳን ቀዳዳ አግኝቶ ቀርቶ እንዲሁም፥ ትንሽ ነገር ቁጣውን እንደሚያገነፍለው ግልፅ ነበር። የተሰረቀ ድምፁን ለማስከበረም በፅኑ ይፈልጋል።.. በዚሁ መሰረት በአዲስ ከተማ ተማሪው ከአካባቢው ህዝብ ጋር በአንድነት ሆኖ.. <በተለኮሰው> ተቃውሞ ውስጥ ሰተት ብሎ ገባበት።.. የተዳፈነው የሕዝብ እሳት በተለያዩ አቅጣጫዎች እየተዛመተ ሔደ።

ያቺ ነጭ መኪና <ሴራዋን> ከውና በጎጃም በረንዳ በኩል ወደ ግራ ታጥፋ እየከነፈች…አባኮራን ሰፈርን እያሳበረች በዮሃንስ ቤ/ክ አድርጋ ወደ ሰሜን ሆቴል አመራች።.. <ቅልቦቹ> ተመሳሳይ የተቃውሞ ድራማ አቀጣጠሉ። ከዚህ በተጨማሪ መንግስት በቦዘኔነት <ሽፋን> ያሰማራቸው ቅልብ ሃይሎች በኮልፌ ቀራንዮ አካባቢ አሰማርቶ ተመሳሳይ <ድራማ> እያቀጣጠለ ነበር። ..የተቃውሞ እሳት የጫረችው ነጯ ቶዮታ ..የማሳረጊያ ግዳጇን በሰሜን ሆ/ል አካባቢ ከተወጣች በኋላ ወጠምሻዎቹን ጭና ቁልቁል በመውረድ ወደ ማእከላዊ ወንጀል ፖሊስ መምሪያ ቅጥር ግቢ ነበር ሰተት ብላ የገባችው። በዚች መኪና ከፊት ተቀምጦ ትእዛዝ በመስጠትና ከበላይ አለቆቹ ጋር መረጃ ልውውጥ በማድረግ ሴራውን ሲመራና ሲያከናውን የነበረው ግርማይ (በቅፅል ስሙ ማንጁስ) የተባለ የሕወሐት አባልና በፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ የደህንነት ሃላፊ እንደሆነ በወቅቱ ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን ከዚህ ባሻገር በአንዱ ስልክ ከጠ/ሚ/ሩ ጋር በቀጥታ ይገናኝ እንደነበረ ተረጋግጦዋል። (በነገርራችን ላይ ስለዚህ ጉዳይ መረጃው ለህዝብ ሳይደርስ ጋዜጦች ወዲያው ተዘጉ)

…ባጠቃላይ በዚህ መልክ በገዢዎቹ ሆነ ተብሎ በተለኮሰው የጥፋት <ሴራ> በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን በአደባባይ በጥይት እንዲቀጠፉ ሲደረግ፣ በ10ሺህ የሚቆጠሩ ደግሞ እስር ቤት ተጋዙ። የነመለስ/በረከት ቀጣዩ <ኢላማ> የቅንጅት አመራሮችንና ደጋፊዎችን፣ጋዜጠኞችን እንዲሁም ሌሎች ወገኖችን ማሰርና ማሰቃየት ስለነበር፥ ያሰቡትን ተግባራዊ አድርገዋል። ከትግራይ ሃውዜን የጀመሩት ህዝብን በጅምላ የማስፈጀት አረመኒያዊ የሴራ ተግባራቸው፥ በአርባባ ጉጉ፣ በበደኖ፣ ትግራይ ሆቴል(ፒያሳ)፣ ጋምቤላ …እያለ በመቀጠል የ97/98 ምርጫን ተራምዶ እነሆ በህዝበ ሙስሊሙና በአማራ ተወላጆች ላይ ቀጥሎ ይገኛል። ከቤኒሻንጉል እንዲፈናቀሉ የተደረጉት የአማራ ተወላጆች በተራ የወረዳ ካድሬዎችና ሹሞች ትእዛዝ እንደማይፈፀም በእርግጠኛነት መናገር ይቻላል። ለዚህ ማስረጃው በጋምቤላ አሰቃቂ ፍጅት እንዲደርስ የተደረገው በወቅቱ የፌደራል ጉዳዮች ሹማምንት በነበሩት አባይ ፀሃዬና በምክትላቸው ዶ/ር ገብረአብ ባርናባስ ቀጥተኛ ትእዛዝ ሰጪነት እንደሆነ የተረጋገጠና በወቅቱም የሁለቱ የሕወሐት ሹሞች ስም ጭምር ተጠቅሶ በኢትኦጵ ጋዜጣ ይፋ መደረጉ ነበር። እንዲያውም አባይ ፀሃዬ በግምገማ ላይ ዶ/ር ገ/አብን ጥፋተኛ ከማድረጋቸው በተጨማሪ < አብሬው መስራት አልችልም፤ ስለዚህ በአስቸኳይ ይነሳልኝ> በማለት የጋምቤላውን ፍጅት በዶክተሩ ላይ ከመደፍደፋቸው ባሻፈር ለ/ጠ/ሚሩ ጥያቄ አቅርበው ይኸው ተፈፀሚ ሆኗል። …ይህ በሆነበት ሁኔታ በቤኒሻንጉል በወገኖቻችን ላይ የደረሰውና ሆን ተብሎ እንዲደርስ የተደረገው መሰሪ ተግባር ከሕወሐት/ኢህአዴግ ቱባ ሹማምንት እውቅና ውጭ ብቻ ሳይሆን የነርሱ ቀጥተኛ ትእዝዛ ያለበት እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል።

በመጨረሻም ፥ በህዝበ ሙስሊሙ እየተካሄደ ባለው ሰላማዊ የመብት ጥያቄና ተቃውሞ ውስጥ የተስተዋለው ጉዳይ፥ ህዝብ ምን ያክል ገዢዎቹን በአስተሳሰብ በልጦ እንደሄደ የሚያመላክት ጭምር ነው። ይኸውም በአንዋር መስጊድና ሰላማዊ ተቃውሞ በሚሰማባቸው አካባቢዎች አንበሳ አውቶብሶችን ሆን ተብሎ በማቆም ሙስሊሙ እንዲሰብራቸው በገዢዎቹ ሲሞከር ታይቶዋል፤ ገዚዎቹ እንዳቀዱት አውቶብሶቹ ሲሰባበሩ… የ97/98 ድራማ ለመድገምና በለመዱት ጭካኔ በጥይት የጅምላ ግድያቸውን ለመተገበር ነው። የሃይማኖቱ ተከታዮች ግን « አንሰብርም….አንሰብርም…» እየሉ በአንድ ድምፅ የነበረከትን የሴራ ድራማ በማክሸፍ ለመብታቸው መቆምንና ሰላምዊ ጥያቄ ማቅረብን ነው የቀጠሉት። ህዝብ ምን ያክል ቀድሟቸው እንደሄደ ጥሩ ማሳያ ነው።

http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/7438

! ….. ሰበር ዜና፡ የ አስገደ ገብረስላሴ ልጅ ቶርቸር እየተፈፀመበት ነው …….!

አሕፈሮም አስገደ (የኣስገደ ገብረስላሴ ልጅ) መታሰሩንና ቤተሰቦቹ እንዲያዩት እንዳልተፈቀደላቸው ፅፌ ነበር። ከሰዓታት በፊት ግን አባቱ ኣቶ አስገደ ገብረስላሴ ልጁ እንዲያሳዩት የፖሊስ ኣዛዦችን ይጠይቃል። ፖሊሱ (የቀዳማይ ወያነ ወረዳ ኣዛዥ ኮነሬል ….. ዋና ኢንስፔክተር) ልጁ ወደ ሌላ እስርቤት መዛወሩ (ከማስፈራርያ ጋር) ነግሮታል።“ወደ የትኛው እስርቤት ተዛወረ ?” ብሎ ሲጠይቅ ኣስደንጋጭ መልስ ተሰጠው፤ “ወደ ባዶ ሽዱሽተ እሰርቤት” የሚል። “ባዶ ሽዱሽተ” (06 ዜሮ ስድስት) እስርቤት የህወሓት እስርቤት ነው። ህወሓቶች ተሰቃይቶ መረጃ እንዲሰጥ የሚፈለግ ሰው ሲገኝ ወደ “ባዶ ሽዱሽተ” ይወሰዳል። ከዛ ቶርቸር ይፈፀምበታል፤ በመጨረሻም ይገደላል (ይረሸናል)። “ባዶ ሽዱሽተ” የስቃይ እስርቤት ነው። ይሄ እስርቤት ህወሓቶች ጫካ እያሉ የሚጠቀሙበት የነበረ ነው።

ko
እስካሁን ድረስ ይሄ እስርቤት መኖሩ ገርሞኛል። (ህወሓቶች ስልጣን ይዘው እያሉም …. ለምን ኣስፈለገ???) ልጁ ቤተሰቦቹና የሕግ ኣማካሪው እንዲያዩት ያልተፈቀደው በቀዳማይ ወያነ ወረዳ ማረምያ ቤት ስላልነበረ ነው። ወላጆቹ ይሉክለት የነበረው ምግብ (ካለፈው እሮብ ጀምሮ) ለልጁ ሳይሰጥ በእስርቤቱ ተበላሽቶ ይገኛል።ሰው እንዲያየው ያልተፈቀደው ያለበት እስርቤት (ባዶ ሽድሽተ) ሕጋዊ ስላልሆነ ነው። በመቀለ ከተማ የሚገኙ ሕጋዊ እስርቤቶች ሰባት ብቻ ናቸው። “ ባዶ ሽድሽተ” ግን ሕጋዊ አይደለም፤ ፍርድቤት አያውቀውም። ወደዛ የገቡ እስረኞ ች ያለፍርድ ቶርቸር (ግርፋት) ይደርሳቸዋል (በቶርቸር ህይወታቸው ሊያልፍ ይችላል)።ባጭሩ “ ባዶ ሽድሽተ” ለቶርቸር ብቻ የተዘጋጀ ሕቡእ (hidden) እስርቤት ነው። አንዳንድ ስለ እስርቤቱ (እስካሁን መኖር የሚያውቁ) የመቐለ ኗሪዎች “ቤርሙዳ” ብለው ይጠሩታል: “እዛ እስርቤት የገባ መውጭያ የለውም” ለማለት። ። ይሄን ሕቡእ፣ ንፁህ ዜጎች የሚሰቃዩበት እስርቤት (ባዶ ሽድሽተ) ሚላኖ ሆተል አከባቢ ከባሎኒ ስታዲዮም ወደ ምስራቅ 100 ሜትር ገባ ብሎ፣ ጀወርግስ ቤተክርስትያን፣ ወደ እንዳየሱስ (ኣሪድ ግቢ መቐለ ዩኒቨርስቲ) ጠጋ ብሎ በሚገኝ (ተራራና ሸለቆ የበዛበት) ጫካ ያለበት ስፍራ ሲሆን underground prison ነው።በኣሁኑ ሰዓት እየተገረፈ እንዳለ መስማቴ ኣሳዝኖኛል። ለምን underground እስርቤት? ለምን ሕጋዊ ያልሆነ እስርቤት????

አሳዛኝ ነው።

! ….በለው ! ማስፈራራት ተጀመረ …..!

ይሄው ሓሳባችንን በገለፅን ፌስቡካችንን (ኣፋችን) ለመዝጋት ተረባረቡ። ተሳካላቸው። ፌስቡካችን DISABLED ሆነ። ከዚህ የምንረዳው ነገር ቢኖር ገዢዎቻችን በፌስቡክ ፅሑፎቻችን መሸበራቸው ነው። የኔ ፌስቡክ መዝጋት መፍትሔ የሚሆን ኣይመስለኝም። (ፓስፖርቴን በመላክ በራሴ ስም እንደምጠቀም ለማስረዳት ሞክርያለሁ። እንደሚከፈትልኝ ተስፋ ኣለኝ። )

በዚሁ ኣላቆሙም። እየደወሉም …….. ማስፈራራት ተያይዘውታል።በትግራይ የሚከናወኑ የፍትሕ ችግሮችና ሙስና ባጋለጥኩበት ፅሑፌ ብዙ ማስፈራርያዎች እየደረሱኝ ነው። የትግራይ ህዝብ ተጨቁኖ ሲያበቃ ጭቆናውን እንዳይጋላጥ መታፈን ኣለበት እንዴ??? ቢቻል ቢቻል ……. ህዝብ መጨቆን ተገቢ ኣይደለም፤ መቆም ኣለበት። ካልሆነ ግን በህወሓት መጨቆናችንና መታፈናችን ሌሎች ወንድሞቻችን ቢያውቁልን ምንድነው ችግሩ???ህወሓት ድጋፍ እንዳያጣ ተብሎ እኛ እንሰቃይ? የትግራይን ህዝብ የፍትሕ ጉድለቶች ማጋለጥ ማንነት መለወጥ ኣይደለም። እንደኔ እንደኔ የህዝብ ዓፈናዎች ማጋለጥ ለህዝብ ነፃነት መቆም እንጂ የህዝብ ጠላት መሆን ኣይደለም። የህዝብን ጠላትነት የሚገለፀው ህዝብን በመጨቆን እንጂ የህዝብን በደል በማጋለጥ ኣይደለም።ማስፈራርያው ……. (ከተወሰነ ውይይት በኋላ ችግር መነሩ ኣምኖ) “ምስጢራችንን እያጋለጥክ ለጠላቶቻችን መሳርያ እየሆንክ ነው (ምሽጥርና እናቃላዕኻ ኣደዳ ፀላእትና ኣይትግበረና)።” የህዝብ ‘ጠላቶች’ መኖራቸው እርግጠኛ ኣይደለሁም (የገዢው ፓርቲ ጠላቶች ሊኖሩ ይችላሉ)።ደግሞ ቢኖሩስ??? ‘ጠላቶች’ እንዳይሰሙ፣ ገመናችን እንዳያውቁ ተብሎ ይበልጥ መታፈን ኣለብን? መሪዎቻችን እንደፈለጉ ይጫወቱብን? ጠላቶች እንዳይሰሙ ተብሎ ህወሓቶች እንደፈለጉ ይጨቁኑን??? በዚ ኣልስማማም።

ገመናቹ እንዳይጋለጥ ከፈለጋቹ ጥሩ መስራት ኣለባቹ፤ ፍትሕ ማስፈን ይጠበቅባችኋል፣ ለሰዎች ነፃነት መፍቀድ ይኖርባችኋል። ለችግሩ መፍትሔ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት እንጂ ዓፈናን የሚያጋልጡ መረጃዎች እንዳይወጡ ማፈን ኣይደለም። ዜጎች መጨቆን ብሎም ጭቆናውን እንዳይጋለጥ ማፈን ችግሩን ማባባስ ነው።

ጭቆናን ስላጋለጥኩ የህዝብ ጠላት ተባልኩ፤ ህዝብን የሚጨቁኑ ደግሞ የህዝብ ወዳጆች ተባሉ። እንዴት ነው ነገሩ??? ህዝብን የበለጠ ለመጨቆን (በስልጣን ለመቆየት) ድጋፍን ያሰባስባሉ። ድጋፍ ኣግኝቶ የስልጣን ዕድሜ ማራዘም የኣንድ ህዝብ የህልውና (በነፃነት የመኖር) ዋስትና ሊሆን ኣይችልም። የህዝብ ዋስትና ፍትሕ ማስፈን ነው። ፍትሕ ለማስፈን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት ያስፈልጋል። ነፃ፣ ገለልተኛና ጠንካራ የመንግስት የፍትሕ ተቋማት መዘርጋት ኣለባቸው።

እንደውጤቱም የህዝብ መብት ይከበራል፤ ሰው ለነፃነቱና ህልውናው ዋስትና ያገኛል። ኣሁንም ኣልመሸም። ችግሩን ማቃለል እንጂ ሓሳባቸው በነፃነት ለሚገልፁ ዜጎች ማስፈራራት ግን መፍትሔ ሊሆን ኣይችልም። እኔ ስላስፈራራቺሁኝ መፃፌን ባቆም ችግሩ ኣቆመ ማለት ኣይደለም። እኔ ባልኖር ሌሎች ይፅፉታል።

! …… የመተካካት ሙስና በህወሓት …….!

ጥያቄ“የምትፅፈው ነገር የተወሰነ እውነት ኣለው። ግን ከውጭ ሁኖ ህወሓት ለት ተቀን ከመውቀስ በህወሓት ውስጥ ሁነው ማስተካከል ኣይሻልም?” (ኣንድ የህወሓት ኣባል)።መልስኣንድህወሓት በቤተሰባዊነትና ሙስና (ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ) የተጨማለቀ ድርጅት ሆነዋል። ኣብዛኛው መዋቅሩ በስብሰዋል። በቀላሉ ሊስተካከል የሚችል ኣይደለም። የመዋቅር ሙስናው በጭቃ እንመስለው፤ ኣብዛኞቹ የህወሓት ባለስልጣናት በሙስና (በጭቃው) ተጨማልቀዋል። ይሄንን ለማስተካከል ታድያ በ’መተካካት’ ስም ኣዲስ ሰው ወደ ጭቃው በመወርወር ጭቃው ማስወገድ ኣይቻልም። የሚያስፈልገው ኣዳዲስ ሰዎች ወደ ጭቃ መክተት ሳይሆን ጭቃው ማስወገድ ነው።

ሁለት

በህወሓት ዉስጥ ግለሰዎች ድርጅቱን የማስተካከል ዕድ ል ኣያገኙም። ምክንያቱም ድርጅቱ ከተዘፈቀበት ዓዘቅት ለማስወጣት ባለ ኣዲስ ራእይ ኣዲስ ወጣቶች፣ ኣዲስ ኣመለካከትና ኣሰራር ኣስገብተው ድርጅቱን መምራት ኣለባቸው። ኣሁን ያለው የህወሓት ኣመራር ይሄንን ይፈቅዳል???

በህወሓት ኣዲስ ራእይ (የራሳቸው ራእይ) ያላቸው ወጣቶች (የፖለቲካ ዓቅም ያላቸው ባለ ራእይ ወጣቶች) የህወሓት ጠላቶች ተደርገው ይቆጠራሉ። የህወሓት ኣባል የሆነ ሰው የራሱ ራእይ ሊኖረው ኣይገባም። ምክንያቱም የራሱ ራእይ ካለው እንዴት የራሱን ትቶ የመለስን ራእይ ለመተግበር ይሯራጣል? ኣሁን የሚፈለገው ‘የመለስ ራእይ’ የሚተገብር ብቻ ነው። ሙሉ በሙሉ የመለሱን ለመተግበር የራሱ ባይኖረው ይመረጣል።

ባለፈው ጉባኤያቸው ተሳታፊዎችን ሲመለምሉ የፖለቲካ ታማኝነት (በዝምድናና ኣመለካከት) ዋነኛው መስፈርት ነበር። ታማኝነት የሚገለፀው ‘የመለስን ራእይ እንዳለ ሳይከለስ ሳይበረዝ ለማሳካት’ የተዘጋጀ ነው። የራሱ ሓሳብ ማፍለቅ የሚችል (የፖለቲካ ዓቅም ያለው) ኣባል ኣይፈለግም (በጉባኤም እንዲሳተፍ ኣልተመረጠም)፣ ሓላፊነትም ኣይሰጠውም። ብቃት ያላቸው ወጣቶች ቦታ (ሓላፊነት) ካልተሰጣቸው እንዴት ውስጥ ገብተው ማስተካከል ይችላሉ? በህወሓት ውስጥ ጥሩ ከሚሰራ ሰው ይልቅ ለኣለቆቹ ውሸት የሚያመላልስ ኣቃጣሪ የበለጠ ተጠቃሚ ነው።

እነ ኣርከበ ዕቁባይ ቡድን የተመታበት መንገድ ….. እነዚህ ሰዎች የራሳችን በራሳችን ኣካሄድ እንስራ በማለታቸው ‘የመለስን ራእይ በራሳቸው ለመቀየር ጥረት እያደረጉ ናቸው’ በሚል ነበር። ኣሁን ያሸንፈው ቡድን የራሱ የሆነ ራእይ (የኣመራር ብቃት) ስለሌለው ‘የመለስ ራእይ እናሳካለን’ እያለ የሚዘምር ነው። ‘የመለስ ራእይ’ ምንድነው የሚለውን ጥያቄ እንኳ መመለስ የማይችል ነው። ኣብዛኞቹ የኣሸናፊው ቡድን ኣባላት በመለስ ግዜ በተለይ በ 1993ቱ የክፍፍል ግዜ ከመለስ ጎን ተሰልፈው ያ ተገንጣይ ቡድን እንዲ ሸነፍ የረዱት ስለሆኑ በፖለቲካዊ መዋቅሩ በብዛት ነበሩ።

ሦስት

ህወሓት በምን መልኩ ማስተካከል ይቻላል??? በመተካካት? ኣይመስለኝም። ለመሆኑ ‘መተካካት’ ምንድነው? መስፈርቱ ምንድነው? ብቃት? ዕድሜ ? የስልጣን ሲኔሪቲ? ወይስ የትግል ቆይታ (Former Fighter vs Civil)? ህወሓቶች የመተካካት መርሁ ወይ ሂደቱ ግልፅ ለማድረግ ኣልፈለጉም። ምክንያት ኣላቸው። የመተካካት መርህ መተግበር ስላስፈራቸው ይመስለኛል። በመልስ ግዜ (ከሁለት ዓመት ተኩል በፊት በነበረ ግባኤ) መተካካት በዕድሜና በስልጣን ሲኔሪቲ እንደሚሆን ሂንት ተሰጥቶን ነበር።

ከመለስ ሞት በኋላ መተካካት በትግል ዕድሜ እንደሆነ ተነገረን (የድሮ ታጋዮች በኣዲስ ትውልድ እንዲተኩ ማድረግ)። ይህን መስፈርት በኢህኣዴግ ደረጃ እየተሰራበት ያለ ይመስላል። በህወሓት ግን ተቀባይነት ኣላገኘም። ለዚህ ነው የህወሓት ሊቀመንበርና ምክትሉ እንዲሁም ሁሉም የስራ ኣስፈፃሚ ኣባላት የድሮ ታጋዮች የተመረጡት። በማእከላዊ ኮሚቴ ኣባላትም ከ45ቱ 9 ብቻ ናቸው ሲቪል።

‘መተካካት’ መቀያየር ወይ መሸጋሸግ ሆነ። እርስበርሳቸው ይቀያየራሉ። ኣንድ በልቶ የጠገበ የድሮ ባለስልጣን በሌላ ሆዱ ያጠበ ይቀየራል። ያልበላ ይበላል። ሁሉም ግን ኣንድ ናቸው። የተለወጠ ነገር የለም። የፖለቲካዊ ኣቅጣጫ ወይ የፖሊሲ ለውጥ ኣይኖርም። ምክንያቱም ሁሉም የነበረ ነው፣ ‘የመለስ ራእይ’ ለመተግበር ተዘጋጅተዋል። (የራሳቸው ከየት ያመጣሉና!)።

ለስልጣን ሲታገሉ ራሱ ‘እኔ ብዙ ዓመት የታገልኩ ነኝ። ስለዚ ስልጣን ይገባኛል’ ይላሉ (እኛ መተካካት ስንጠብቅ)። ባጠቃላይ ግን በህወሓት ‘የመተካካት መርህ’ ከሽፈዋል። እነዚህ ከስልጣን የወረዱም ቢሆኑ ተሸንፈው እንጂ ወደው ኣይደለም ስልጣን የለቀቁ። የሚገርመው ደግሞ ታጋዮቹ ሄዱ፣ ታጋዮቹ መጡ። ወጣቶች ሳይመረጡ ቀሩ።

ኣራት

ኣሸናፊው ቡድን (የነ ኣባይ ወልዱ) ማሸነፉ፣ ባቀደው መሰረት ጉባኤው መከናወኑ የራሱ ኣባላት እየመሰከሩ ናቸው። ትናንት ማታ ብርሃነ ኪዳነማርያም (የማእከላዊ ኮሚቴ ኣባልና የጉባኤው ቃል ኣቀባይ)ና ትርፉ ኪዳነማርያም (ስራ ኣስፈፃሚ ኣባል) ከVOA ትግርኛ ጋር ቃለ መጠይቅ ባካሄዱበት ግዜ ጉባኤው ባለሙት፣ በጠበቁበት፣ በፈለጉት ‘በድል መጠናቀቁ’ ጠቁመዋል። እኔም የተለየ ሓሳብ የለኝም። ኣዎ! እነሱ ባደራጁት መሰረት ኣሸናፊ ሁነው ወጥተዋል። (ኣርከበ “ሽልማት ኣልቀበልም” ብሎ ሳይገኝ ሲቀር ኢቲቪ “ኣቶ ኣርከበ በስራ ምክንያት ሳይገኙ ቀርተዋል” ኣለን። ይገርማል።)

‘ትርፉ ኪዳነማርያም …. የባለስልጣን ሚስት (የኣባይ ወልዱ) ስለሆነች ነው የተመረጠች የሚል ነገር ኣለና እንዴት ታይዋለሽ?’ ብሎ ሲጠይቃት፣ ‘እንደዚህ ልንባል ከሆነ ታድያ ለምን ዕድሜ ልካችን ተታገልን? የተታገል’ኮ ለእኩልነት ነው።’ ኣለች። ጋዜጠኛው ኣስከትሎ ‘ብዙ ታጋይ ሴቶች ነበሩኮ በማእከላዊ ኮሚቴ የተመረጡት ግን ስምንት ብቻ ናቸው’ ኣላት። ትርፉም ‘ የትምህርት ጉዳይ ኣለ፣ የፖለቲካዊ ኣቅጣጫ ግንዛቤ ኣለ፣ የፓርቲው values ማወቅ ነገር ኣለ …. (ምናምን)’ ኣለች። ዓቅማቸው በሚፈቅድላቸው በዞን ኣስተዳደርና በፓርላማ እንደሚሳተፉም ገልፃለች።

ከዚህ የምንረዳው ነገር እነዚህ የድሮ ታጋዮች (ለምንድነው የታገልነው ታድያ? እያሉ ) ስልጣን ለወጣቱ ትውልድ ለማስረከብ ዝግጁነት እንደሚያንሳቸው ነው። ሌላው ለእኩልነት የታገሉ ሴቶች እነዚህ የባለ ስልጣን ሚስቶች ብቻ ናቸው እንዴ??? በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች ለእኩልነት ታግለዋል። ስልጣን ለመያዝ ግን የባለስልጣን ሚስት መሆን ኣስፈላጊ ሳይሆን ኣይቀርም። (ኣዜብ የመለስ፣ ፈትለወርቅ የኣባይ ፀሃየ፣ ቅዱሳን ነጋ የፀጋይ በርሀ፣ ትርፉ የኣባይ ወልዱ፣ ሮማን ገብረስላሴ የተወልደ ዓጋመ …….) ኣብዛኞቹ ስልጣን የያዙ ሴቶች ከባለስልጣን ወንዶች ጋር የደም ወይ የጋብቻ ዝምድና ኣላቸው።

ሌላው የትምህርት ደረጃ ኣንስታለች። ከትርፉ ያነሰ የትምህርት ደረጃና የፖለቲካ እውቀት ያላት ታጋይ ሴት የምታውቁ ከሆነ ኣስረዱኝ። ይሄ ንቀት ነው ወይ ስልጣን ላለማስረከብ ተብሎ ነው። ብዙ ጎበዝ ሴቶች ኣሉ፣ ቦታ ያላገኙ።

ኣምስት

ህወሓት ብቃት ላላቸው ወጣት ሙሁራን ፈተና ነው። ደሞ ወጣቶች ገብተው ምን ሊያስተካክሉ ነው? ፖሊሲው፣ ራእዩ፣ ኣሰራሩ ምናምኑ ኣይስተካከልም ተብሏል። የመልስ ራእይ ብቻ ማስፈፀም። ስለዚ ኣይስተካከልም። በህወሓት ከተሳካልህ ልታገኘው የምትችለው ነገር ኢኮኖሚያዊ ጥቅም (በሙስና) ወይ ፖለቲካዊ ስልጣን (ከነሱ በ ደም ወይ ጋብቻ በመዛመድ) ነው። ሃብትና ስልጣን ነፃነት ሊያመጣ ኣይችልም። ነፃ ለመሆን ከሞከርክ ታገኛታለህ!!!

ስድስት

በሙስና በበሰበሰ ስርዓት ‘የመተካካት መርህ’ ዉጤት ኣያመጣም። ምክንያቱም መሪዎቹ በሙስና ከተዘፈቁ ብቁና ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ተተኪ ወጣት የመመረጥ ዕድሉ ኣነስተኛ ነው። ወጣት ተተኪዎቹ ማነው የሚመርጣቸው? ኣለቆቻቸው ናቸው (ገምግመው የሚያቀርብዋቸው)። ሲመለምሉ ታድያ ለነሱ ታማኝ ሁኖ ያገለገለ፣ ሙስና ሲበሉ የማያጋልጣቸው (ወይም የተባበራቸው ……. ኣብሮ ሙስና የበላ ቢሆን ይመረጣል ምክንያቱም በኋላ እንዳያሳስራቸው)፣ የነሱ ዘመድ የሆነ (እንደማይጥላቸው የሚተማመኑበት)፣ ባጭሩ የራሳቸው ኣምሳያ ተክተው ይሄዳሉ (ተተኪዎች የመመልመል ስልጣን ስለተሰጣቸው)።

ስለዚ መተካካት እንኳ ቢደረግ (ዘሮ ዘሮ ከእጃቸው ስለማይወጣ) ስርዓቱ የሚፈለገው የመልካም ኣስተዳደርና የኢኮኖሚ ልማት ማስመዝገብ ኣይቻለውም። ለውጥ ለማምጣት መጀመርያ ሙስና ማጥፋት ኣለባቸው፤ ሙስና ካጠፉ ደግሞ ገዢው ፓርቲ ጠፋ ማለት ነው። ምክንያቱም ፓርቲው የተገነባ በሙስና ነው። ግንቡ ከፈረሰ ፓርቲው ወደቀ ማለት ነው።

ወይ ሙስና! ደግሞ ህወሓት ምኑ ሊስተካከል???!!!

ሰባት

ባለፈው ዓመት ስለ ሙስና ኣስፈላጊነት በህወሓት የፃፍኩት እነሆ:

“It is true that you should not only be members of the ruling party but also very loyal ones …. in order to get ‘good’ jobs and ‘promising’ titles. As the government’s administrative structure is being used for party purposes, corruption (besides nepotism) has become the best (for carrot and stick) strategy of the ruling party in order to play with its members.

Corruption serves both ways: to pull members in (to the party) and push them out (of the party). Party officials directly or indirectly promise individuals that … When they join (and/or remain loyal) to the ruling party, they may get material benefits such as access to more jobs, money, power or whatsoever. Such discrimination by itself is corruption. Then corruption helps them to get more members.

When the officials want to ‘cheat’ their members, they allow (or encourage) them to engage themselves in corruption. This strategy of creating ‘conducive’ environment for new members to share the advantages of corruption helps the top officials in three ways:

(1) Through corruption, members may satisfy their own personal interests by having more material benefits. Here, corruption is serving as a pulling factor (carrot) for new members to join to the party thereby strengthening and lengthening the life span of their party.

(2) With corruption, the top officials create their own copies for when the new members become corrupt, then the possibility of (the top corrupt officials) to be exposed reduces dramatically. The new entry becomes part of the old one. Both become like-minded.

(3) If the new members are engaged in corruption, then their right to an ‘independent thinking’ is lost. These individuals would not have the chance to oppose the ruling party. If they oppose or express a different opinion, they will be charged with corruption scandals. They will be defamed and/or removed from party membership. Yet, this will not be done as long as they remain loyal to the officials.

To this end, the EPRDF party officials encourage corruption (to their members). They simply register what the new members do. Hence, corruption is important for party politics. This is why the members of the ruling party do not want to avoid it. Yet, whenever the political consciousness of the people (the ruled) rises (the people demands for good governance), the corruption scandal endangers the existence of the party in question. The people may tend to overthrow the corrupt officials.

My message goes that ……..

Dear members, please refrain from engaging yourselves in corruption. Your higher officials may keep silent for the time being (as long as you are loyal to them), but the people is watching you. I do not want you to sell your freedom for material benefits. You should always remember that EPRDF is a dying horse.

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/2515

የአማራን ዘ ር የማጥፋት እኩይ የወያኔ ሤራ

Amhara Women Cry on Eviction from her home by TPLF policy:See the picture

wen

አማራ ሆኖ መኖር በወያኔ መራሹ መንግሥት ዘንድ ወንጀል ነዉ ዋጋ ያስከፍላል በዚህም መሰረት አማራ ለ21ዓመታት በሀገሩ ላይ  ስደት ሞት ውርደት እንግልት ግርፋት መብት የለሽ ሆኖ በመኖር ዋጋ በመክፈል ላይ ይገኛል ወንጀል የሆነበት ዋናው ምክንያት  በዋናነት ኢትዮጵያን ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ከጠላት  ጠብቆ መኖሩ ነዉ ምክንያቱም አሁን በስልጣን ላይ ያለው የወያኔ አመራር አባላት ሀገር ከድተው በተለይም የጣሊያን የባንዳ ልጆች መሆናቸው ነው በቀልን ጥላቻን ይዘው ሀገርን ሰላም በመንሳት ተግተዉ እየሰሩ ያሉት በዚህም መሰረት እንደየደረጃው በተለያዩ ጎሳዎች ግፍ እየተፈጸመ  ይገኛል በቀዳሚነት አማራና ኦሮሞን መጥቀስ በቂ ብቻ ሳይሆን ከበቂ በላይ ነው በተለይ አማራ ማለት ትምክህተኛ ነፍጠኛ በሚለው የስድብ ቃል ሃያ አራት ሰዓት በወያኔ  የፕሮፓጋንዳ ማሰራጫ ጣቢያዎች ኢቲቪ ሬድዮ ፋና  ኤፍኤም በየቀኑ መስማት የተለመደ ነው

ወያኔ ከደደቢት አዲስአበባ ቤተ መንግሥት የሚደክመውና ተግቶ እየሰራ ያለው አማራን ከኢትዮጵያ  ዘሩን ጨርሶ በአማራ መቃብር ላይ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ማጥፋት በኦሮሞ ህዝብ  በጉራጌ ህዝብ በሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች ላይም ተመሳሳይ ግፍ እየተፈጸመ ያለው ኢትጵያዊነት ለማጥፋት ካለው አጀንዳ ነው

አቦይ ስብሃት እኔ ግን አቦይ የሚለውን የክብር ስም ሊጠራበት አይገባውም ይልቁንም ዕቡይ ስብሃት ተብሎ ቢጠራየተሻለ ነው እላለሁ ይህ ክፉ መንፈስ ያደረበት ሰው በተደጋጋሚ ሲፎክር እንደሰማነው  አማራና ኦርቶዶክስ ሃይማኖትን አጥፍተናቸዋል  ቦታ የላቸውም የሚል ነበር ነገሩን እንደቀላል ነገር ልናየው እንችላለን ይህ ዘመን የሰጠው  እንደልቡ ተናጋሪ የሆነ ሰው  የተናገረው የሰሩትን እውነታና እየሰሩ ያሉትን ነገር ነው

አዲስአበባ እንደገቡ ያለምንም ጥፋት ብቻ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ምሁራን በሀገራቸው ላይ ስራ እንዳይሰሩ ታግደዋል ከአዲስአበባ ዩኒቨርቲና ከተለያዩ ተቋማት ተባረዋል ይህ ሆን ብሎ የአማራን ተወላጅ ለማጥፋት ካለው መሰረታዊ አጀንዳ የመነጨ ነው በምትካቸው ከሌሎች ሀገሮች ማለትም ከሕንድ፣ከጋና መምህራኖች ቀጥሮ ያመጣው  በዚሁ ምክንያት ነው

በጎንደር በተለይም በወልቃይት ፣በጠገዴ ፣በጠለምት፣በደብረታቦር በጎጃም በሰሜን ሸዋ በደብረብርሃን ይህ ነው የማይባል የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል,በጥናት ላይ የተመሰረተ ከባድ የሆነ የዘርማጥፋት ወንጀል ዛሬም በመፈጸም ላይ ይገኛል

የበደኖ የአርባ ጉጉ ወዘተ ወንጀሎች ሁሉ ወዘተ ተመሳሳይ ወንጀሎች ተፈጽመዋል ሁሉም ጊዜውን ጠብቆ ይወጣል ሰው ሊያውቀዉ በማይችለው ሁኔታ በሕክምና ተቋማት በኩል በክትባት ስም በአማራ ሕፃናት ላይየHIV vires ጨምሮ የተለያዩ ኢሰብአዊ  ድርጊቶች ተፈጽመዋል፣ነገር ግን ለሁሉም ጊዜ አለው እንደተባለው ለጊዜ መተው ይሻላል

አማራነት ካመጣቸው ችግሮች  ትንሾቹን እንይ

ወያኔ ኢህአዴግ አዲስ አበባ እንደገባ በአማራ ላይ የተወሰዱ እርምጃዎች

1ኛ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ ከመንበራቸው ወይም ከሥልጣናቸው እንዲወርዱና እንዲገላቱ በመጨረሻም በሃገራቸው መኖር ባለመቻላቸው እንደሌሎች የአማራ ተወላጆች አማራ በመሆናቸው ብቻ ለስደት ፣ለዕንግልት፣ ተዳርገዋል,

ዛሬ ወያኔ  የራሱን ምልምል ፓትርያርክ በማስቀመጥ ዛሬ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የአንድ የወያኔ  ተቋም ሁና በመስራት ላይ መሆኗን እያየን ነው በዚህም መሰረት በዕቡይ ስብሐት  ንግግር መሰረት የኢትዮጵን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አጥፍተናታል እንዳለው ዛሬ ቤተ ክርስቲያኗ ከመንፈሳዊና ከማኅበራዊ አገልግሎት ውጭ ሁና የሚታየው መሞቷን የሚያረጋግጥልን ጉዳይ ነው

2ኛ ፕሮፌሰር አስራት ወ/ ኢየሱስን ያሳሰረ ያንገላታ ያሰቃየ ለሞትም ያደረሰ ሌላ ወንጀል አይደለም አማራነት ብቻ ነው

3ኛ አቶ ተስፋየ ማሩን በጠራራ ፀሀይ በጥይት ያስገደለ ወንጀል አማራነት ብቻ ነው

አማራ እንደማንኛውም የሃገሪቱ ዜጎች አፈር ገፍቶ አዳረ ሠራተኛ ታታሪ ሀገሩን የሚወድ ሕዝብ ነው፣ ይህ ህዝብ  ከሌሎች ኢትዮጵያውን ጋር ማለትም ከትግራይ ወገኖቹ ጋርም በሰላምም በችግርም ወቅት አብሮ የኖረ መሆኑ ቀርቶ እንደ ክፉጠላትተቆጥሮ መከራ እየተቀበለ ያለ ህዝብ ነው

አማራ ለችግሩ ደራሽ ወገን አጥቶ 21 ዓመታት የሰው ልጅ ሊሸከመው የማይችል የመከራ ጽዋን እየተጋተ የሚገኝ አሳዛኝ ሕዝብ መሆኑ ግልፅ ነው

አንድ እዉነተኛ ታሪከ ልንገራችሁ የውጭ ሀገር የትምህረት ዕድል  ይገኝና ወደ ዉጭ ሄዶ መማር የሚፈልግ ተማሪ ሁሉ መመዝገብ ይችላል የሚል ማስታወቂያ ይወጣና ሁሉም ተማረ እንደፍላጎቱ  ለመመዝገብ ወደ መመዝገቢያ ቦታው ሲሄዱ አንድ ካድሪ ተኮፍሶ ቁጭ ብሎአል ከዚያም ተመዝጋቢዎችም ቀርበው ስም ሲጠየቁ በመጀመሪያ የትግራይ ልጆች ቀርበው ይመዘገባሉ ሁሉም መመዘኛዉን አለፉ መመዘኛዉም ዕዉቀት መሆኑ ቀርቶ ብሔር በመሆኑ ሌሎችም እየቀረቡ ይመዘገባሉ በመጨረሻ አንድ የዋህ ተማሪ ተራዉ ደርሶ ይቀርባል፣ መዝጋቢዉ ካድሪ ቀና ብሎ ያየዉና ከፊቱ የቆመዉን ተማሪ ብሄር ህ ምንድ ነው  ይለዋል ተማሪዉም በፍርሃት አማራ ይላል ያኔ ካድሪዉ ቆም ብሎ በቁጣ ከአማራ የሆናችሁ ዉጡ ከአማራ ብሄር አንወስድም የምንመዘገበው ከሌሎች ብሔሮች ብቻ ነው ይላል ይህን የሰማ ወላጆቹ አማራ የሆኑ ተማሪ ሌሎች የአማራ ተወላጆች የሆኑ ተማሪዎች ሲወጡ በድፍረት ይቀርና ሰልፉን እንደያዘ ይቆያል ተራው ደርሶት ወደ ካድሪው ቀርቦ ብሄር ይጠየቃል እሱም ኮራ ብሎ ደቡብ ሕዝቦች ይላል ወዲያዉኑ ከአፉ ተቀብሎ ካድሪዉ በብሔርህ አልፈሃል ግን ለሌሎች ብሔሮች ቅድሚያ ስለሚሰጥ ምናልባት ቦታ ካለ ስምህ በማስታወቂያ መለጥፊያ ቦታ በ15 ቀናት ዉስጥ ይወጣል ተከታተል ተብሎ ሲከታተል እንዳጋጣሚ ዕድሉን አግኝቶ ወደ ዉጭ ሃገር መጥቶ ትምህርቱን በመከታተል ይገኛል ከወደ ኋላ መለስ ብሎ በማሰብ ደፋርና ጭስ መዉጫ አያጣም ሆኖ ነዉ እንጂ ያኔ መንዜ መሆኔን ቢያዉቁ በሽርብተኝነት ወንጀል  ዘብጥያ ያወርዱኝ ነበር በማለት በሃዘን ትዝታ ያጫወተኝ

በአማራ ላይ ያልተፈጸመ ኢሰብአዊ ድርጊት የለም ሌላዉ ቀርቶ ብአዴን የሚሉት ድርጅት  አማራዉን እወክላለሁ ብሎ በሕወሐት የሚመራው ፓርቲ ዉስጥ አማራዉን የሚወክል ሰዉ እንደጠፋ ሁሉ ሆን ተብሎ አማራዉን ለማጥፋት ከሚሰራዉ ሕወሐትና ከሌሎች ብሄሮች የተዉጣጡ የጸረ አማራ ስብስብ መሆኑ ግልጽ ነዉ ድርጅቱ መለያ አርማውም ሆነ አመራሮቹ የሕወሐት ሰዎች መሆናቸዉን ለአብነት እንይ ,

እኔ እስከማዉቀዉ ድረስ ዋና ዋናዎቹ የአመራር አባላት

1ኛ ተሰማ  ገ/ሕይወት 2ኛ አቶ ካሣ ተ/ብርሃን 3ኛ አቶ አዲሱ ለገሰ 4ኛ ህላዌ ዮሴፍ ወዘተ የአማራ ተወላጆች ናቸዉ የምትሉ ካላችሁ የዋሆች ናችሁ አማራ ማለት በሕወሐት ዕምነት ጠላት ነዉ ዘፈኑን  እስቲ እናስታዉስ ገረብ ገረብ ትግራይ መቃብር አምሃራይ የትግራይ ሸለቆዎች ተራራዎች የአማራ መቃብር ናቸዉ  ወይም ይሆናሉ እያለ በቅዠትም በህልምም በዉኑ ም ጸረ አማራ ሆኖ የተፈጠረዉ ወያኔ ነዉ ብአዴን ማለት

አማራ መሆን እንዲያሳፍር አንገት እንዲያስቀልስ  እንዲያሸማቅቅ ለ21 ዓመታት ሲሰራ የኖረዉ አማራ ፈሪ ነዉ በሚለዉ በኢያሱ በርሄ ዜማ አማራን እየተከታተለ ዘሩን በማጥፋትና በኢትዮጵያዊነቱ ተከብሮ ሌላዉንም አክብሮ ከሚኖርበት አካባቢ እተፈናቀለ የሚገኘዉ ከደደቢት ጀምሮ አማራን ለማጥፋት በተያዘዉ  ዕቅድ መሰረት እተፈጸመ ያለ ሂደት ነዉ ,

አማራን ከቤንሻንጉል ጉምዝ ማስወጣት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ሕሊና ያለዉ ሁሉ ሰዉ በራሱ ዳኝነት ይየዉ

አማራን መዉጫ መግቢያ በማሳጣት ከዚያች ሃገር ማጥፋት ነዉ,ከ2 4 ሚሊዮን የአማራ ሕዝብ በወያኔ አረመኒያዊ ተግባር ወንጀል ተፈጽሞበት ጠፍቷል እንዴት ጠፋ ወደፊት ኢትዮጵያዊ መንግስት ሲኖር የሚታይ ይሆናል የአማራ ወንጀል ኢትዮጵያዊነቱ እንደሆነ ግልፅ ነዉ  ይችን ሃገር ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር በመሆን ደሙን አፍሶ ከጠላት ጠብቆ መኖሩ ነዉ  ወንጀሉ ሌላ ምንም ወንጀል የለበትም

አሁን ከጉራ ፈርዳ ከቤንሻንጉል ክልሎች የሚፈናቀሉት አማራ ሆኖ መኖር ወንጀል በመሆኑ ብቻ ነዉ ይህም እየሆነ ያለዉ በህወሐት ጨካኝና ጎጠኛ ድርጅት ስለሆነ ሁሉም ኢትዮጵያዊ አንድ ሆኖ ሊጋፈጠዉ ይገባል ይህ ጊዜ ያልፋል በሚያልፍ ጊዜ የማያልፍ ታሪክ ሰርተን ማለፍ  አለብን በሰላማዊ ትግል መታገል አይቻልም በተለይ አማራ ሆኖ የማይታሰብ ጉዳይ ነው ወጣቱ ፖለቲከኛ አንዱዓለም አራጌ በሰላም መታገሉ ወንጀል ሆኖበት ቃሊቲ እንዲወረወር ያደረገዉ አማራ መሆኑ ብቻ ነው

በቤንሻጉል የዘር ማፅዳት ወንጀል ነዉ እየተፈጸመ ያለዉ ዘርን መሰረት አድርጎ ሌሎችን በማነሳሳት የሚፈጸም ወንጀል ነው በዚህ ወንጀል ሌሎች ኢትዮጵያዉያን እጃችሁን ባታስገቡ መልካም ነ ዉ ይህ ነገር ዝም ብሎ

የሚቀር   አይሆነም ዋጋ ያስከፍላል ዐይንና ጆሮ የሌለዉ ህወሃት ዛሬ አማራን ማጥፋቱን እ ንጂ ነገ ሊያመጣ የሚለውዉን  ችግር የሚያይበት ዐይን የለዉም , ምክንያቱም ዕብሪተኛ  ስለሆነ ብቻ ,ሰው በሃገሩ ላይ ከተፈናቀለ ምን ሃገር አለዉ ሊባል  ይችላል ሊባል የሚችለዉ በሀገሩ ላይ ስደተኛ የሆነ ማለት ነዉ ይህ ይህ ደግሞ ለማንም አይበጅም ተጎጂ የሚሆነዉ አማራ ብቻ አይሆንም የሁሉንም  ቤት ያንኳኩል,የትግራይ ተወላጆችስ አማራ ውስጥ የሉም ወይ እንዲያዉም ጎንደር፣ ባህርዳር፣ ደሴ የትግራይ ከተሞች እስኪመስሉ ድረስ የትግራይ ልጆች መኖሪያ መስሪያ ከተሞች ናቸዉ ሌላዉ ቀርቶ የአማራ ቲሺ አንባቢዎች   በነክብሮም ወ/ስላሴ በነ ህሊና መብራቱ የተያዘዉ አማርኛ ዜና አንባቢ ክአማራ ተወላጆች ሰው  ስለጠፋ ሊሆን እንደማይችል ተስፋ አደርጋለሁ ይህን የምለዉ በወያኔ ስሌት እንጂ በእኔ ዕምነት ትግሬዎችም በአማራም ሆነ በሌሎች ቦታዎች ሰርቶ መኖር ኢትዮጵያዊ መብታቸዉ ነው ስለዚህ የትግራይ ልጆች በአማራዉ ወንድማቸዉ እየደረሰ ያለዉን ችግር ከአማራዉ ከኦሮ

ሞዉ ከጉራጌዉ ከአፋሩ ጎን በመቆም ወገናዊነታቸዉን ማሳየት ከምንጊዜዉም በበለጠ ይጠበቅባቸዋል,ወያኔ  ሁሉንም አጋጭቶ ማለፍ ስለሆነ አላማዉ ጥላቻን አስወግደን ወያኔን ልንፋለመዉ ይገባል በአማራ ተወላጅ ላይ በወያኔ የግፍ አገዛዝ ያልሆነ ምንም ነገር የለም በቤት ዉስጥ እንዳሉ በዕሳት ተቃጥለዋል ,በተኙበት ተደብድበዉ ተገለዋል እንደእንስሳ ታርደዋል ተገለዋል ይህ ሁሉ የሆነ አንድ  ጊዜ ወይም ሁለት ጊዜ አይደለም ወያኔ ከጫካ ህይወቱ ጀምሮ እስካሁን በአማራ ሕዝብ ላይ እያደረሰዉ ያለዉ ግፍና መከራ  ነዉ

አንድ በዕድሜዉ ሸምገል ያለ ሰዉ ብሔራዊ ቲያትር አካባቢ ብቻዉን እያወራ ይሄዳል ምን እንደሚል ጠጋ ብዬ ለመስማት ወደ ሰዉዬዉ  ሄድኩ ድምጹን ከፍ አድርጎ ቢገሉህ የማታልቅ ህዝብ ነበር የሚለዉ እዉነትም ቢገሉት የማያልቅ ህዝብ ልክ እንደ አማራ ህዝብ የኦሮሞ ህዝብ በሃገሩ ላይ ተዋርዷል፣ ታስሯል ፣ተገርፏል ፣ተገሏል በሙሉ ኢትዮጵያዉያን  የዜግነት መብታቸዉን ተገፈዋል , በሀገራቸዉ እንደ ሁለተኛ ዜጋ ተቆጥረዋል,ዛሬ በኢትዮጵያ ዉስጥ በየትኛዉም ቦታ ከትግራይ ተወላጆች ውጭ በወያኔ ሥርዓት ተጠቃሚ የሆነ ከአንዳንድ ካድሪዎች ዉጭ አንድም የሌላ የኢትዮጵያ ብሔር ተወላጅ የለም ,ሌላዉ ቀርቶ በዉጭ ያሉ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችን በየሃገሩ መመልከት ይቻላል በሚያሳፍር ሁኔታ ለትግራይ ልጆች ብቻ አገልግሎት እንዲሰጥ ሁኖ የተዋቀረ መሆኑን ላለፉት 21 ዓመታት ያየነዉ ይህ ደግሞ ለአንድነታችን አደጋኛ ሁኔታ መሆኑን አዉቀዉ እንዲህ ዐይነቱን ሥራ መቃወም የግድ ይላል , በየሀገሩ ኢትዮጵያዉን በኢትዮጵያ ኤምባሲ በር ላይ እንደ እባብ ራስ ራሳቸዉን ተቀጥቅጠዉ ሲሞቱ ማን ደረሰላቸዉ ማንም የደረሰላቸዉ የለም ምክንያቱም የሕወሃት አባል ወይም የትግራይ ተወላጅ እስካልሆኑ ድረስ ኤምባሲዉ እንደማይመለከተዉ ያየነዉ ጉዳይ ነዉ ,አንድ ጊዜ ሀገር ቤት የሆነዉን ማስታወስ የግድ ሆነብኝ በኦሮምያ ክልል ዉስጥ አንድ የትግራይ ተወላጅ በሆነ በተፈጠረ ግጭት ህይወቱ አለፈች , በዚህም ምክንያት አካባቢዉ ቀዉጢ ሆነ በሙሉ ትንሽ ትልቁ ተጋፎ ወደ እስር ቤት ገባ ከዚያ በኋላ በእስር ቤት ዉስጥ የሆነዉን እግዚአብሔር ይወቀዉ ,የሟቹ አስከሬንም በክብር ወደ ትግራይ ሄዶ መስሪያ ቤት ተዘግቶ የሀዘን ቀን ሆኖ ሥርዓተ ቀብሩ ተፈጽሟል,ታዲያ ለሌላዉ ኢትዮጵያዊ ማን ይድረስለት አሁን ያለዉ የወያኔ መንግስት ዘረኛ ስለሆነ ተፈጥሮዉ ኢትዮጵያዊ ስላልሆነ አሁንም ኢትዮጵያን ከማፍረስ ዉጭ ሌላ ነገር መጠበቅ ከዕባብ ዕንቁላል የርግብ ጫጩት እንደመጠበቅ ይቆጠራል,የአማራ፣የኦሮሞ

፣የጋምቤላ፣ የአፋር የጉራጌ ወዘተ ልጆች ግን በየቀኑ ወያኔ ባዘጋጀዉ ወጥመድ ዉስጥ ገብተዉ ምንም የማያዉቁ ሕጻናት በየቀኑ ሕይወታቸዉ በማለፍ ላይ ይገኛል,

በቤንሻጉል በጉራፈርዳ በጋምቤላ አሁንም ግፍ እየተፈጸመ ነዉ ያለዉ አማራዎቹ ወደ መጡበትይመለሱ እንጂ በዚያ ምን ዐይነት ወንጀል እየተፈጸመባቸዉ እንደሆነ የምናዉቀዉ ምንም ነገር የለም ,የምንሰማዉ ነገር ግን ከሚዲያ እንዲርቁ            አድርጎ የዘር ማጥፋቱ ወንጀል በከፋ ሁኔታ እየተፈጸመባቸዉ ነዉ ,አሁን የሞተዉን ህዝብ ታሪክ ማዉራቱ ምንም ፋይዳ የለም ወያኔ በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ ሞት፣ ስደት፣  ዉርደት በአማራ ህዝብ ላይ የማይቋረጥ ሂደት ነዉ ,

በአማራ ሰላማዉያን ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለዉን አደጋ ወያኔ እንዲያቆም ከተፈለገ ስራ መስራት ያስፈልጋል,አሁን ይህንን ወንጀል የፈጸመዉ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዉንን በማጥፋት ያለዉ ወያኔ ብቻ ሳይሆን ይህ ድርጊት ሲፈጸም ዝም ብለዉ

ያዩ የሃይማኖት መሪዎች፣ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ምሁራን ፣ታዋቂ ግለሰቦች ሁሉ በተባባሪነት ወንጀል ይጠየቃሉ,ሁላችንም ተጠያቂዎች ከመሆን ለመዳን ከጎሳ ፖለቲካ በመዉጣት እጅ ለእጅ ተያይዘን ወያኔን መታገል የግድ ነዉ ,ካሁን በኋላ ከወሬ ያለፈ ሥራ መስራት ካልቻልን የወያኔ የዘር ማጥፋት ወንጀል አያቆምም ምናልባት የሚሆነው ከአማራዉ ወደ ኦሮሞዉ ከኦሮሞዉ ወደ ወላይታዉ በፈረቃ እንደ አዲስአበባ መብራት እየተዘዋወረ ይቀጥላል እንጂ አይቆምም እየሞቱ ከመኖር እየኖሩ መሞት አማራጭ የሌለዉ መፍትሔ ይሆናል,ወያኔ በየጊዜዉ ወንጀል በፈጸመ ቁጥር ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንዲያዉቀዉ ከማድረጉ ባሻገር ለዘላቂ መፍትሔ የትግል መስመር መቀየስ ያስፈልጋል ,የሰላማዊ ትግል ሁኔታ ሃያ አንድ ዓመታት የታዬ ስለሆነ በሱ ላይ ጊዜ ማጥፋት አያስፈልግም ,የሰላማዊ ትግል ሂደትበሽብርተኛ ስም ጉዞዉ እስከቃሊቲ ድረስ ብቻ ይሆናል,ሁሉም ኢትዮጵያዊ ልዩነቱን አስወግዶ በኣንድነት በመታገል ነጻ ሊወጣ ወይም በጎሳ ተከፋፍሎ

በሀገሩ ላይ ስደተኛ ባሪያ ሁኖ በወያኔ የባርነት ወጥመድ ዉስጥ ለዘለዓም መኖር ይሆናል ,

ወያኔን በጸረ ኢትዮጵያዊነት የሚቀድመዉ እንጅ የሚበልጠዉ የለም እንደዚህ ዐይነት የዉርደት ፣የስቃይ፣ የጥፋት ዘመን በታሪክ ተፈጥሮ አያዉቅም ESAT TVን  በመደገፍ የምናሳየዉ ትብብር ከቀጠለና ለሌላዉም የትግል መስመር እንደዚህ ከተባበርን ወያኔን የማናጠፋበት ምንም ምክንያት አይኖርም

ወያኔን በቃ ብለን እንነሳ በየቀኑ እንደቅጠል ለሚረግፉ ወገኖቻችን እንድረስላቸዉ ወያኔን በሚገባው ቋንቋ እናነጋግረዉ

ሰላም ድል ለኢትዮጵያዉን

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/2524

የዘረፋ ውሎ

በእንዳማሪያም (ገብረመድህን አርዓያ)

ስብሃት ነጋ ባለፈው ሳምንት አዲስ አበባ በሚታተመው የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ የሰጠውን ቃለ መጠይቅ አነበብኩት:: ስብሃት ነጋ “ኢህዴግን የመሰለ ፓርቲ በአፍሪካ የለም” እና ሌላም ብዙ ፣ ብዙ ይላል:: ይዘብታል ፣ ይፎክራል፣ ይሸመጥጣል፣ ያቀረሻል፣ በህዝብ ሞራል ላይም ያላግጣል:: ብዙም አልደነቀኝም:: ስብሃትም ሆኑ የዚህ ፋሺስታዊ ስርዓት አንቀሳቃሾች በብዙሃን ደም ላለፉት አርባ አመታት ታጥበዋል ፣ ታሪክ አውድመዋል ፣ እጅግ ከፍተኛ ዘረፋ ፈጽመዋል ፣ አገር ቆርሰው ሸጠዋል:: በጣም ከፍተኛ ወንጀል የሰሩ ሰዎች እንደመሆናቸው በአገሪቷ የፖለቲካ ለውጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ መቀጣጠሉ እንቅልፍ እንደነሳቸው እያየን ነው:: አዎን ስብሃት ገና ፣ ገና ከዚህም በላይ ብዙ ይናገራል ፤ ቁጣው እያየለ በሄደ ቁጥር ብዙ ወንጀሎችም ይሰራል::

gem

ዛሬ ወያኔ ኢህአዴግ ከመቼውም ጊዜ በበዛ ፍጥነት እና ማን አለብኝነት ኢትዮጵያዊ የሆኑ መሰረቶችን የመናዱን ስራ አጠናክሮ እየሰራ ለመሆኑ በየእለቱ የምንሰማቸው ዜናዎች እና ዘገባዎች ያሳያሉ:: እንደ እኔ ፣ እንደ እኔ የወያኔ የጥፋት ስራ ሳይሆን የጨመረው ይልቁንስ ረጅም እድሜ ለኢሳት ይስጠውና የዜና ዘገባ ብዛት እና አይነቱ መጨመሩ ይመስለኛል:: ወያኔ ሲፈጠር ጀምሮ ኢትዮጵያዊ መሰረት ያላቸውን እሴቶችን የማጥቃት ስራን እንደ መጨረሻ ግብ(strategic goal) አስቀምጦ የሚንቀሳቀስ ድርጅት መሆኑን ቀድመን ላወቅን እና ለተረዳን ሰዎች ግን እምብዛም አዲስ ነገር አይደለም:: ዛሬ ላይ ከኢትዮጵያ ከሚወጡ ዜናዎች በብዛት የምንሰማው ብዙዎች ሲያለቅሱ እና ጥቂት ዘረኞች ደግሞ ያለ ይሉኝታ ሲዘርፉ ፣ ሰዎችን አስረው ሲያሰቃዩ፣ እና ኢትዮጵያውያንን ዘር ቆጥረው ከቀያቸው ሲያፈናቅሉ ሆኗል::

የኢትዮጵያውያን ገበሬዎች ዋይታ በቤኒሻንጉል እና ጉራፈርዳ፣ የባህታውያን ለቅሶ በዋልድባ ፣ የእስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን የፍትህ ጥያቄ በመላ ሃገሪቱ ፣ ሌላም ፣ ሌላም:: ወያኔ ኢህአዴግ በአገር እና በወገን ላይ የሚያደርሰው ጥቃት በግብ ደረጃ የተያዘ በመሆኑ ይብሱን ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚችል በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል:: ዛሬ ላይ ከዳር ቆመው የሚመለከቱ ሰዎችም ሆነ በስርዓቱ ውስጥ ያሉ ካድሬዎች እና አገልጋዮች ይህንን ሃቅ በደንብ ልብ ብለው ሊመለከቱት ይገባል:: የጥቃት ዱላው በአንድ ወይም በሌላ በኩል አይደርስ የሚመስልበት ቦታ ሁላ ይደርሳል::

ኢትዮጵያውያን ከምንም ነገር በላይ ለሃይማኖት እና የእምነት ተቋሟት ታላቅ ክብር ይሰጣሉ:: በዛሬ ጽሁፌ ለማንሳት የፈለግኩት ጉዳይ በአንድ ወቅት በወያኔ ኢህአዴግ ውስጥ ታጋይ በነበርኩበት ወቅት በዘመቻ ከስብሃት ነጋ እና ከሃለቃ ጸጋይ በርሄ ጋር ሌሎች ሁለት ታጋዮችም ተጨምረውበት አንድ ገዳም እንዴት እንደፈርን እና እንደዘረፍን በማሳየት ስብሃትም ሆነ ድርጅቱ እንዴት ለአገራዊ እና ሃይማኖታዊ ተቋማት ያላቸውን ንቀት ለማሳየት ነው:: ጊዜው ሕዳር ወር 1971ዓ.ም. እና የተ.ሓ.ህ.ት. 1ኛ ጉባኤ እየተቃረበ የመጣበት ወቅት ነበር። ድርጅቱ ለጉባኤው ማካሄጃ በሚል ሰበብ የትግራይ ደሃ ገበሬዎችን ንብረት እና ገንዘብ በስፋት መቀማቱን በዘመቻ ተያይዞታል:: ሃብትና ንብረታቸው የተዘረፈ ንጹሃን የትግራይ ገበሬዎችንም ሃለዋ ወያኔ በማስገባት መፍጀቱ ተጧጡፏል፤ በወቅቱ የተ.ሓ.ህ.ት. ቤዝ በለሳ፤ እገላ ወረዳ ውስጥ ይገኛል። ብዙ ክፍሎች፤ ማለትም 02 ወታደራዊ ማሰልጠኛ፤ 03 ህክምና፤ 04 ፖለቲካ ጽ/ቤት፤ 05 ክፍሊ ኢኮኖሚ፤ 09 መሳሪያ ግምጃ ቤትና 06 ሃለዋ ወያነ ተበለው ተከፋፍለው እዚሁ ቦታ ላይ በተለያየ አቀማመጥ ሆነው ይሰራሉ። አቦይ ስብሃት በ04 ፖለቲካ ጽ/ቤት በሚታዘዙ እና በአዲ ጨጓር እና በለሳ ምይ ሃማቶ ላይ በሚገኙ ሁለት ሃለዋ ወያኔዎች(እስር ቤቶች) ንጹሃንን አሳስሮ ያስገርፋል፣ ያስገድላል:: እኔ በወቅቱ የህክምናው ክፍል ሃላፊ ነበርኩኝ:: እና ታዲያ በዚሁ አንድ የህዳር ቀን በስብሃት የተጻፈ ቀጭን ደብዳቤ በምሰራበት የህክምና ክፍል ደረሰኝ:: ደብዳቤው እንዲህ ይላል : ነገ ጠዋት ልክ በ2 ሰዓት መሬቶ እንድትጠብቀኝ፤ ወደ ሽራሮ ለሥራ ጉዳይ አብረን እንሄዳለን:: ለምን ፣ እንዴት ፣ በምን ተብሎ አይጠየቅም፤

በነጋታው እንደታዘዝኩት በተባለው ሰዓት መሬቶ ቁሽት ቀድሜ ደረሼ ቆየሁት። እሱም በሰዓቱ መጣ። ተያይዘን ጉዞአችንን ወደ ጭላ ወረዳ ቀጠልን። ቀኑን ሙሉ ስንጓዝ ውለን በመሃልም ግርማይ ጀብር የሚመራት አንድ ሃይል ተቀብላን አንድ ቦታ አደርን። ከአስመራ ወደ አድዋ የሚወስደውን መንገድ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ አሻገሩን። ይህ መንገድ ሁልጊዜ የኢትዮጵያ ጦር አይለየውምና ለመሻገር ጥንቃቄ ይሻል::

ጭላ ከጥዋቱ 2 ሰዓት ገባን። እዛ የቆዩን ሃለቃ ፀጋይ በርሄ–የላይ አድያቦ ሕዝብ ግንኙነት፤ አጽብሃ ሀ/ማርያም–የአንከረ ሕዝብ ግንኙነት፤ ቀሺ ታደሰ–የክርቢት ነውጠኛ መሪ ነበሩ። እኔና ስብሃት ተደምረን አምስታችን ጭላ ውለን ስብሃት ቀድሞ ለወጠነውና አስቅድሞ መረጃው ለሌለኝ የዘረፋ ስራ ወደ እንዳማርያም ገዳም ጉዞ ጀመርን:: ሃለቃ ፀጋይ በርሄ በስብሃት በታዘዘው መሰረት አስቀድሞ ጥናቱን ጨርሶ ስለነበር፤ የቤት ክርስትያኑን አቃቤ ግምጃ ቤት ባህታዊ ማን መሆናቸውን እና የት አካባቢ እንደሚኖሩ አውቋል። ሌሎቻችን ታጣፊ ክላሽንኮቭ ስብሃት ነጋ ደፍሞ ሽጉጥ ታጥቋል። ለምን እና ወዴት እንደምንሄድ ቀሺ ታደሰ፤ አጽብሃ ሃይለማርያምም ሆነ እኔ አናውቅም። ኋላም ተጉዘን እንዳማርያም ቤተ ክርስቲያን ገባን። ቤተ ክርስቲያኑ በጥንት ዘመን በአብርሃ ወአፅብሃ ዘመነመንግሥት የተሰራ፤ በጣም ሰፊና ብዙ የአትክልት እና ፍራፍሬ እርሻ የሚለማበት ገዳም ነው:: በመነኮሳት ጉልበት በመስኖ የለማ ሎሚ፤ ሙዝ፤ ብርቱካን፤ ትርንጎ፤ መንደሪን ገዳሙን ከቦታል። መቼም አካባቢው ውብ እና ለመንፈሳዊ ህይወት የተመቸ ነው:: በእድሜ የበለጸጉ ባህታውያን፤ ቀሳውስት፤ መናንያን እና ዲያቆናት በገዳሙ ዙሪያ መንፈሳዊ ህይወታቸውን ይመራሉ። ውስጥ ለውስጥ ብዙ ከሄድን በኋላ ከፊታችን አንድ ዲያቆን አገኘን። ሃለቃ ፀጋይ ዲያቆኑን ለብቻ ነጥሎ አናገረው፤ ምን እንደተነጋገሩ እኔ ካለሁበት ብዙም አይሰማም ብቻ ሁለቱ ተያይዘው ከፊት እየመሩ ወደ አንድ ቤት ውስጥ አስገቡን። ቀጥሎም ስብሃት ነጋ እንዲህ አለ፤ ሌሎቻችሁ እዚሁ ቆዩ:: እኔ ፣ ገ/መድህን እና ሃለቃ ፀጋይ ብቻ የገዳሙን አስተዳዳሪ ለማናገር እንሄዳለን:: ከዚያም ሶስታችንም ተያይዘን ከነትጥቃችን ወደ ገዳሙ አስተዳዳሪ ቤት አቀናን:: የገዳሙንም አስተዳዳሪ ከቤታቸው አገኘናቸው:: ለአፍ ያህል ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ ስብሃት ጊዜ ሳያጠፋ “የመጣነው ገንዘብ እንዲሰጡን ስለሆነ ያለዎትን ሁሉ ይስጡን!” አላቸው። ለመነኩሴው ግር የሚል ትዕዛዝ ነበር:: ብዙም ሳያቅማሙ “እኔ አልሰጥም፤ የእመቤቴ ብርሃን ንብረትና ሃብት ላይ የማዘዝ መብት የለኝም:: አልሰጥም::” በማለት እቅጩን በግልጽ አማርኛ ተናገሩ:: ስብሃትም አይኑን እያጉረጠረጠ ድምጹን ከፍ አድርጎ አምጡ ማለቱን ቀጠለ:: ስብሃት በቀላሉ እንደማይመለስ በድምጽም ፊቱን በመቀያየርም እንዲረዱ አደረገ ፣ ምስኪኑ አባትም አማራጭ እንደሌላቸው ተረዱ::ትንሽ አስብ አደረጉና ወደውስጥ ገብተው የተቋጠረ ከረጢት ተሸክመው መጡ።

ባዘነ አንደበት እንዲህም ሲሉ ተናገሩ ፤ “የቤተ ክርስቲያን ሃብት ወድጄ ፈቅጄ ሳይሆን የሰጠኋችሁ አስገድዳችሁ እና አንቃችሁ እንደወሰዳችሁ እወቁት::” ከዚያም ከረጢቱን አልሰጥም በማለት ብር 50,000 የታሰረ ገንዘብ ከፊቱ ዘረገፉለት። ስብሃትም በፍጥነት ይዘነው በመጣነው ‘ሃቨር ሳክ’ በሚባል ወታደራዊ ሻንጣ ሞልተን ተሸክመን እንድንወጣ አዘዘ:: እኛም የተባልነውን አደረግን:: ባህታዊውም በመውጫችን ላይ እንዲህ አሉ፤ “ነገ ጠዋት ለሕዝበ ክርስቲያኑ የሆነውን ሁሉ እናገራለሁ::” የተዘረፈውን ገንዘብ እኔና ስብሃት ተሸክመን ተመልሰን በለሳ ማይሃምቶ ገባን።

የተፈጸመውን የዘረፋ እና የገዳም ደፈራ የአካባቢው ሕዝብ ሁሉ ሰማው፤ በተሰራው ስራም ክፉኛ አዘነ፤ አወገዘውም። ስብሃት ድርጊቱ የየግል ምስጢራችን ሆኖ መጠበቅ እንዳለበት አስጠነቀቀን። ለዘረፋው ስራም ባለን ድርጅታዊ ታማኝነት እንደተመረጥን ገለጸልን። እንግዲህ ይህ አንድ ገጠመኝ ብቻ ነው:: ዘረፋ፣ ማውደም ፣ ታሪክ እና ቅርስ ማጥፋት ፣ የእስላምም ይሁን የክርስቲያን ቤተ እምነቶችን መድፈር እና ማበላሸት ለህወሃት የሰርክ ስራዎች ናቸው::

በአለቃ ገበረ ሃና ስም የሚነገር አንድ ታሪክ አለ:: ልጅቷ አለቃ ጋር ሄዳ “ጎረምሶቹ ሁሉ ድንቼ ፣ ድንቼ እያሉ ይጠሩኛል:: ለምን ይመስልዎታል::” ብትላቸው አለቃም እንዲህ አሉ:: ” ሊልጡሽ ፈልገው ነዋ!”:: ትናንትና በዘር እና በሃይማኖት እየመረጠ የአንድን አገር ወንድማማቾችን አንዱን ለአንዱ ታሪካዊ ጠላትህ ነው ፤ ላንተ ህልውና ከኔ በላይ ላሳር እያለ ሲመጻድቅባቸው የነበሩ የሃይማኖትም ሆነ የብሄር ቡድኖችን ከነጠለ በኋላ ያለ ሃይ ባይ ሲያጠቃ እያየን ነው:: ዛሬ ላይ በኢትዮጵያ እስር ቤቶች አስር ሺህ በሚቆጠሩ ኦሮሞዎች ታጭቀዋል:: በቃሊቲ ፣ በጨለንቆ ፣ በዝዋይ ፣ በሸዋ ሮቢት ፣ እና በሌሎችም በይፋ ባልተመዘገቡ የወያኔ ማጎሪያዎች ውስጥ ዜጎች ያለሃጥያታቸው ታስረው ይሰቃያሉ::

ስርዓቱ ዛሬ ላይ በሰፊው በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ የመጨረሻውን ዱላ ከማንሳቱ በፊት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን የማጥቃቱን ስራ ሙሉ አቅሙን አሳርፎ ሰርቷል:: ከኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በቀር በጉዳዩ ብዙም ግድ ያለው አልነበረም:: ነገ ደግሞ ተረኛ የካቶሊካዊት ወይም የሌላ ወንጌላውያን ቤተክርስቲያናት ሊሆኑ እንደሚችሉ መገመት አይከብድም:: ይህን ዘረኛ እና ከፋፋይ ስርዓት በመታገስ እና በማስታመም የትኛውም የህብረተሰብ ክፍል ነገ ጥቃት ተቀባይ ሊሆን አይገባም::

ስለወያኔ ማንነት ይኸው ለአመታት የተናገርኩት አንድ በአንድ ጊዜውን እየጠበቀ ሲፈጸም አየን:: አሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ ኢትዮጵያውያን በአንድ ድምጽ በቃ የሚሉበት ጊዜ ላይ ደርሰናል:: የለውጥ ጊዜ እየቀረበ ነው:: ኢትዮጵያውያን አይን ለአይን ተያይተው ፤ ልብ ለልብ ተግባብተው ይህንን ዘረኛ እና ፋሺስታዊ ስርዓት ከዚያች ቅዱስ አገር የሚያጠፉበት ጊዜ በእውነትም እየቀረበ ነው:: ኢትዮጵያውያን በአንድነት ሲሰሩ ምን ማድረግ እንደሚችሉ እስከ አፍንጫው በታጠቀው የወራሪው የፋሺስት ኢጣልያ ጦር ላይ የተቀዳጁትን የአድዋውን ድል ማስታወሱ ብቻ በቂ ነው::በአዲስ ተስፋ ለህልውናቸው እና ለቀጣይ ትውልድም የምትበቃ አገር እና መንግስት ለማቆም ሊሰሩ የሚገባበት ወቅት እየመጣ ነው:: በመጨረሻም ከሰሜን እስከ ደቡብ ፤ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ:: እስላም እና ክርስቲያን ሳይሉ ፤ ኦሮሞ ፣ አማራ ፣ ትግሬ ፣ ጉራጌ ፣ ወላይታ ፣ አገው ፣ አፋር ፣ ቤኒሻንጉል ፣ ስልጤ ፣ አደሬ ነኝ ብለው ወያኔ በሰፋላቸው የዘረኝነት ወጥመድ ውስጥ ሳይወድቁ እጅ ለእጅ ተያይዘው ለወሳኝ የፖለቲካ ለውጥ እንዲሰሩ ጥሪዬን አስተላልፋለሁኝ::

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

ገብረመድህን አርዓያ

http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/7413

“የተዘነጉት እስረኞች” እና የተዘነጋው የቤተሰቦቻቸው ስቃይ (ልብ የሚነካ ታሪክ)

በፍቃዱ ዘ- ኃይሉ

konj

ላለፉት አራትዓመታት ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ቅዳሜ እና እሁድ የሄደ ሰው ወጣቷን ናርዶስን ሳያገኝ አይመለስም፡፡ ናርዶስ ገና የ20 ዓመት ወጣትእና በኪያሜድ የመጀመሪያ ዓመት የነርሲንግ ተማሪ ናት፡፡ ናርዶስ ዘሪሁን በየሳምንቱ  ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትመላለሰው በ‹‹አሸባሪነት›› ‹በእነብርጋዴር ጄኔራልተፈራ ማሞ መዝገብ› ከተከሰሱት 36 ሰዎች መካከል ዕድሜ ልክ የተፈረደባትን እናቷን ልትጎበኝ ነው፡፡ እነዚህ እስረኞች ሚያዝያ16/2001 አመሻሹ 12 ሰዓት አካባቢ ነበር ሁሉም በያሉበት በቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡ እኛም 4ኛ ዓመታቸውን ለማሰብ ተሰባስበንወደቃሊቲ ማረሚያ ቤት በተለይ እማዋይሽ ዓለሙን ለመጠየቅ ሄደን ነበር፡፡ እንደተለመደው ናርዶስንም አገኘናት እና ብዙ ነገሮችንአጫወተችን፡፡

ናርዶስ ትረካዋን  የጀመረችው እናቷን እና ሌሎችም በተመሳሳይ መዝገብ ተከሰው የተፈረደባቸውንሰዎች አያያዝ ነበር፡፡ ‹‹ሳስበው የተረሱ ያህል እየተሰማኝ ነው፤ ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ሚዲያዎች ስለነሱ አይደለም እያነሱ ያሉት፡፡በእናቴ ክስ የታሰሩት ከ30 ሰዎች በላይ ናቸው፡፡ አንድ ሰሞን ከይቅርታ ጋር በተያያዘ ስማቸው እየተነሳ ነበር አሁን ግን ሁሉነገር የተረሳ ይመስለኛል›› በማለት የእስሩ ሕመም ለታሳሪዎቹ እና ለቤተሰቦቻቸው ግን የሚረሳ ዓይነት አለመሆኑን ነገረችን፡፡

‹‹ሚያዝያ16፣ አርብ ቀን ነበር ሁሉም የተያዙት›› በማለት ሲታሰሩ የነበረውን ጠቅላላ ሁኔታ በማስታወስ ትጀምራለች፡፡ ‹‹ለአንድ ሰው የመጡየማይመስሉ ብዙ ሲቪል የለበሱ እና የፌዴራል ፖሊስ ልብስ የለበሱ ፖሊሶች መሳሪያቸውን አቀባብለው ነበር ወደቤት የገቡት፡፡ ስልካችሁንአጥፉ ወደማንም እንዳትደውሉ አሉን፡፡ የብርበራ ማዘዣ ይዘው ነበር፤ ‹ቤት ልንፈትሽ ነው የመጣነው እማዋይሽ ዓለሙ በቁጥጥር ስርውለሻል› አሏት ቤት ፍተሻው እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት ድረስ ቀጥሏል፡፡ ቀኑ አርብ ነበር፤ እናቴ ደግሞ እስከ 12 ሰዓት ትጾምስለነበር ከሥራ ወደቤት እንደገባች ‹ምግብ ስጡኝ› እያለች እያለ ነበር ፖሊሶች የገቡት ስለዚህ ምግብ ሳትበላ ውላ ነው ወደ እስርቤት የወሰዷት፡፡ ከዚያ በኋላ አራት ወራት ያክል ዓይኗን አላየነውም ነበር፤ ትሙት ትኑር የምናውቀው ነገር አልነበረም፡፡  ደግነቱ በሌላ ጉዳይ ታስራ በተፈታች ሴት አማካይነት መልዕክት ደረሰኝ፡፡ ‹አንቺደህና ከሆንሽ ሽሮ እና ጎመን ሰርተሸ አስገቢልኝ፤ እኔ ደግሞ ደኅንነቴነን የባናና ማስቲካ ወረቀት እልክልሻለሁ፡፡ ደኅና ካልሆንኩኝግን ያ ነገር ይቀራል› ብላ ላከችብኝ፡፡ ከዚያ እኔም ሽሮ እና ጎመን ሠርቼ በመላክ፣ እሷም የባናና ወረቀት በመላክ ደኅንነታችንንየሚገልፅ መልዕክት እንለዋወጥ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ እየሆነ ባለበት ሰዓት እኛ በሌለንበት ጉዳያቸው ፍርድቤት ይታይ ነበር፡፡›› በማለትጉዳያቸው በኢፍትሐዊ መንገድ በመንግሥት እንደተያዘ አጫውታናለች፡፡

‹‹እናቴ ስዕልመሳል ትወዳለች፡፡ እናም በየጊዜው የጀመረቻቸው ስዕሎች የተበላሹ ሲመስሏት ቅርጫት ውስጥ ትጥላቸዋለች፡፡ ይመስለኛል፤  የቤት ሠራተኛችን እጅ አለበት፡፡ ስትታሰር የቀረበባት መረጃ እነዚህ የተጣሉወረቀቶች ተሰብስበው ‹የድርጅቱን አርማ ስታዘጋጅ ነው› የሚል ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ፈቃድ የነበረው፣ ያውም የማይሠራ ሽጉጥም እንዲሁበማስረጃነት የቀረበባት መሆኑ ነው፡፡›› በማለት ለእርሷ ፍርዱ ፍትሐዊ አለመሆኑን እና እናቷም ነጻ መሆኗን እንደምታምን ነግራናለች፡፡

‹‹የሚያሳዝነውነገር ደግሞ ሲታሰሩ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተላለፈው ዜና ነው፤ እንኳን አገር ወዳዷ እናቴ ማንም ባገሩ ላይ የሚያደርገውን ነገርነው አደረጉ ያለው፤›› የዜናውን ፖለቲካዊ ወገንተኝነት ወቅሳለች፡፡ እናቷ ሕዝብና አገር የማሸበር ፍላጎት ሊኖራት ለአገር ፍቅርሕይወቷን የሰጠች መሆኗን ስታጫውተን ‹‹እናቴ ሁልጊዜ የምትነግረኝ ነገር አለ፤ ሕይወቴ ማለፍ ካለበት አገሬን በሚጠቅም ነገር መሆንአለበት ትለኝ ነበር፤›› ብላናለች፡፡ ነገር ግን መንግሥት በአንድ በኩል ‹‹ሕገ መንግሥቱን ለመናድ በመሞከር ነው ያሰርኳችሁ እያለበሌላ በኩል ደግሞ የፖለቲካ እስረኞች የሉኝም ይላል፤›› ካለች በኋላ ‹‹ተቃዋሚ መባላቸው ካልቀረ የኢሕአዴግ መንግሥት የፖለቲካእስረኞች እንደሆኑ ቢያምን  እንኳ ጥሩ ነው፤›› ብላናለች፡፡ ‹‹እናቴለአገሯ ከማንም  በላይ ሠርታለች ብዬ አምናለሁ፡፡ ነገር ግን አገራችንለእናቴ ውለታዋን እየከፈለቻት ነው ብዬ አላምንም፡፡ ያለሃጢያታቸው ሃጢያት ተሰጥቷቸው ነው ያሉት›› በማለት ፍርዱ አገር ወዳድእናቷን የሚያዋርድ እንደሆነ በሐዘን  ተርካልናለች፡፡

የእናቷ በአሸባሪነትመፈረጅ ለናርዶስ ማኅበራዊ እና ስነልቦናዊ ቀውስ እያደረሰባት መሆኑንም አጫውታናለች፡፡ ‹‹ለትምህርቴ መስጠት የሚገባኝ ጊዜ ያህልመስጠት አልቻልኩም፤ እናቴ የታሰረችው እኔ ስምንተኛ ክፍል እያለሁ ነበር፡፡ ዩንቨርስቲ መግባት ሲኖርብኝ አሁን ግን ‹ነርሲንግ›እየተማርኩ ያለሁት በዚሁ ተፅዕኖ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ የእነርሱን የእስር ዜና ኢቲቪ ከአቀረበበት መንገድ አኳያ ትምህርት ቤት ውስጥራሱ እኔን መቅረብ የሚፈሩ ሰዎች አሉ፤› በማለት የእናቷ እስር በእርሷ ማኅበራዊ ሕይወቷ ላይ ያጠላበትን ጥላ አጫውታናለች፡፡

‹‹እስጢፋኖስአካባቢ የሚገኘው እና በእናቴ ስም  ተይዞ የነበረው የቀበሌ ቤታችንበልማት ስም ሲፈርስ እንኳን ለጎረቤቶቻችን በምትኩ ሲሰጣቸው ለእኛ ግን አልተሰጠንም፡፡ ሌላው ቀርቶ መታወቂያ እንኳን ለኛ ለመስጠትፈቃደኞች አይደሉም›› ቤታቸውን ካፈረሱባቸው በኋላ አክስቷ ጋር እየኖረች እንደሆነ ስትነግረን በየመሐሉ እየገታችው ታወራልን የነበረውእምባዋ ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ሲወርድ ማድረግ የቻልነው ነገር ቢኖር በዝምታ ማጀብ ነበር፡፡

‹‹ያለአባትያሳደገችኝን የእናቴን ፍቅሯን አልጠገብኩትም›› የምትለን ናርዶስ ‹‹በዚህ ዕድሜዬ ለኔ የሚገባኝ ቦታ ቃሊቲ አልነበረም፡፡›› በማለትብዙ ነገር መሥራት በነበረባት ጊዜ ቃሊቲ በመመላለስ እንዲባክን መንግሥት እንደፈረደባት እንደሚሰማት ነግራናለች፡፡ ‹‹አራት ዓመቱን  በአሰቃቂ ሁኔታ ነው ያሳለፍኩት፤ ከ16 ዓመታት በኋላ ከእስር የተፈታው አባቴየራሱን ሁሉ ነገር ትቶ ሕይወቱን ለኔ መስዋዕት ባያደርግ ኖሮ አልወጣውም ነበር›› በማለት እንደዕድል እናቷ ከመታሰሯ ሁለት ወርያክል ቀድሞ በተፈታው አባቷ ድጋፍ ከብዙ ቀውስ እንደተረፈች እየነገረችን ከናቷ ጋር የነበራትን ፍቅር ‹‹እናቴ ሁለ ነገሬ ነች!››ብላለች፡፡

‹‹እናቴንሊጎዳ የሚያስብ ሰው እኔን  አንድ ነገር ሊያደርግ ይችላል በሚል ተሳቅቄነው የምኖረው›› በማለት በዙሪያዋ ያለውን ወዳጅ እና ጠላት እንኳን ማመን እየቸገራት እሷ ራሷም ቢሆን ከማኅበረሰብ የመነጠል እናየመስጋት ስነልቦናዊ ችግር ውስጥ እንደሆነች አስረድታናለች፡፡

‹‹የርዕዮትዓለሙእህት እስከዳር ዓለሙ ‹የቤታችን ሰላም እና ፍቅር ከርዕዮት ዓለሙ ጋር ታስሯል› ያለችው በጣም ትክክል  ነው›› በማለት በታሰሩት ሰዎች ቁጥር እኩል የሚሆኑ ቤተሰቦች በከፍተኛ ፈተናውስጥ እያለፉ መሆኑን አበክራ ነግራናለች፡፡

የናርዶስ  ታሪክ የብቻዋ ታሪክ አይደለም፡፡ የሌሎች የብዙ ቤተሰቦቻቸው የታሰሩባቸውቤተሰቦች ታሪክ ነው፡፡ ናርዶስም ‹‹እንደኔ ሁሉ ችግር ላይ ያሉ፣ አባቶቻቸው የታሰሩባቸው ብዙ ልጆች አሉ›› ብላናለች፡፡ በዚሁመዝገብ ተከሰው የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው አቶ መላኩ ተፈራ ቤተሰቦችም ከሰኞ እስከ እሁድ ቃሊቲ ደጃፍ ላይ ከማይጠፉት ሰዎች ውስጥይመደባሉ፡፡ በሥራ ጉዳይ ከአገር ውጪ ያለችው ልጃቸው ፅዮንም አባቷን ለመጎብኘት ሲባል ቶሎ፣ ቶሎ እንድትመላለስ ተገድዳለች፡፡እነጄኔራል ተፈራ ማሞ፣ እነአሳምነው  ፅጌ እና ሌሎችም ደግሞ በእስረኞችመሐል ‹‹ተነስቷል በሚል ፀብ›› ሰበብ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ወደዝዋይ እንዲዛወሩ ተደርገዋል፡፡ ይህ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዳይገናኙሌላ ተጨማሪ ጫና አሳድሮባቸዋል ብላናለች፡፡ እዚህ የቀሩት ታሳሪዎችም አጋሮቻቸውን በማጣት ለብቸኝነት ስሜት ተዳርገዋል፡፡

ከነርሱ መዝገብውጪ ያሉ ሌሎችም እስረኞች እና ቤተሰቦቻቸው በተመሳሳይ ፈተና ውስጥ መሆናቸውን እስረኞችን ለመጎብኘት በሄድንባቸው ጊዜያት ተረድተናል፡፡መንግሥት ለፖለቲካ ግብአቱ የይቅርታ ደብዳቤ ካስፈረማቸው በኋላ እንኳን ለመፍታት ፍላጎት አያሳይም፡፡ ይልቁንም፤ ከቦታ ቦታ እያዘዋወረስቃያቸውን ያበዛል፡፡ ለዚህ እንደምሳሌ ባለፈው አርብ (ሚያዝያ 11/2005) ወደዝዋይ እንዲዘዋወር የተደረገው ጋዜጠኛ ውብሸትታዬ ተጠቃሽ ነው፡፡ በእርሱ የጋዜጠኝነት ደሞዝ ላይ ጥገኛ የነበሩት ባለቤቱ እና ልጁ (ፍትሕ ውብሸት) በእናትዬው መፍጨርጨር ሕይወታቸውንእንዲመሩ ከመገደዳቸውም በላይ አሁን የቤቱን አባውራ ለመጠየቅ ዝዋይ ድረስ እንዲመላለሱ ተፈርዶባቸዋል፡፡ ለዚህም ነው መንግሥት የፖለቲካ አይደሉም የሚላቸውን የፖለቲካ እስረኞችን ከነቤተሰቦቻቸው ከሚቀጣበት መንገድ ይታረም ዘንድ ሊጠየቅ ይገባዋል በማለት የምንመክረው፡፡

http://www.zehabesha.com/amharic/archives/2511