Monthly Archives: December, 2013

በኩላሊት ህመም የሚሰቃየው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ በቂ ህክምና ሳያገኝ ወደ ዝዋይ እንዲመለስ ተወሰነ

ዘ-ህበሻ | December 21st, 2013

ዘጋቢ ጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞን ከአዲስ አበባ

webshet taye
በዝዋይ ወህኒ ቤት ቆይታው ለከፍተኛ የኩላሊት ህመም በመዳረጉ የተሻለ ህክምና ያገኝ ዘንድ በማረሚያ ቤቱ ክሊኒክ ሪፈር የተጻፈለት ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ወደ አዲስ አበባ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ቢዘዋወርም የናፈቀውን የተሻለ ህክምና ሳያገኝ ወደ ዝዋይ ማረሚያ

ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ ወይም ቪዲዮውን ለማየት እዚህ ላይ ይጫኑ።

የወያኔ ልዩ ፖሊስ በምስራቅ ሃረርጌ ዞን ንጹሃንን በጥይት ፈጀ •

(ከምኒልክ ሳልሳዊ) በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልላዊ መንግስት ሚሊሻዎች የሆኑ እና “ልዩ ፖሊስ” በመባል የሚታወቁት የወያኔ የጸጥታ ሃይሎች በምስራቅ ሃረርጌ ዞን አራት ንጹሃን ዜጎችን ገለው ሁለት ማቁሰላቸው ታውቋል::እንዲሁም እስካሁን ቁጥራቸው ያልታወቁ ነዋሪዎች ከአከባቢው መፈናቀላቸው ታውቋል::

ባለፉት ወራቶች ጀምሮ የልዩ ፖሊስ ሃይሎች አከባቢውን በመውረር በዚሁ ምስራቅ ሃረርጌ በማዩ ሙሉጋ አከባቢ የሚኖሩ ንጹሃንን በማንገላታት በማሰር በመግደል የአከባቢውን ነዋሪዎች ከአከባቢው በማፈናቀል ላይ ሲሆኑ ይኸው ወረራ እና ማፈናቀል መግደል ጡምቢጎሃ ; ሴላጃጆ እና አናሚኖ;በስፋት እየተካሄደ ሲሆን አብዛኛው የአከባቢው ነዋሪዎች ቦታቸውን በመልቀቅ ይህንን የወያኔ ወረራ በመሸሽ ከአከባብያቸው ተፈናቅለው ወደ ቡርቃ ቲልጢላ እና የአከባቢ ወረዳዎች በመሸሽ ቦታቸውን የአከባቢው የወያኔ ሚሊሻዎች ወይንም ልዩ ፖሊስ ተቆጣጥሮት ይገኛል::

http://www.zehabesha.com/

በህወሓት/ወያኔ መቃብር ላይ ብቻ ኢትዮጵያ በሰላምና በብልጽግና ትኖራለች!


 

የኢትዮጵያ ህዝብ ማናቸውም መብቶቹ ተነፍጎ የመኖርና ያለመኖር የህልውና ጥያቄ ላይ እንገኛለን:: የህዝቡ የሰብዓዊ መብቶችበየትኛውም ዓለም በማይገኝ መልኩ ይጨፈለቃል ለዚህ ያበቃን ደግሞ ትልቁ ምክንያት የህወሓት/ወያኔን የወንበዴነት ጭካኔ ለመጋፈጥ ያለመፈለጋችን ወይም የጭካኔያቸውን መጠን የሚቋቋም ትግል ባለመኖሩና መስዋዕትነትን ለመክፈል ባለመቁረጣችን የመጣብን መከራ እንጂ ህወሓት/ወያኔ ምንም ስለሆነ አይደለም::  የተቃራነውን ጎራ የልብ ትርታ የተረዳው ህወሓት/ወያኔ ሲፈልገው ይገድላል፣ያስራል፣ ያዋክባል፣መሬትንና ንብረትን በሠበብ አስባቡ ይነጥቃል፣ ከስራ ያባርራል፣ የትምህርትና ሌሎች መብቶችን ገፎ ለመከራ ይዳርጋል ካልሆነም ከአገር ማሳደድን እንደትልቅ አማራጭ ተያይዞታል::

በኢትዮጵያ የመኖር መብት እንዳለንና አገራችን መሆኑን እያወቀ መብቶቻችንን የነፈገን ህወሓት/ወያኔ በማን አለብኝነት መቀጠላቸውን ይሁን ብለን ተቀብለን እኛም መስማማታችን ለዛሬው የባሰበት ችግር አድርጎናል:: እነሱ አገራችን አይደለችም ብለው በሚበዘብዟት አገር ላይ ተንደላቀው እየኖሩ ኢትዮጵያ አገሬ የሚሏት እየተዋከቡ ለችግርና ለመከራ መዳረጋችን እጅግ ያሳዝናል:: አሁን ባለው ሁኔታ ኢትዮጵያ ለውጥ ልታመጣ የምትችለው ህወሓት/ወያኔ ይዞት ከተነሳው  አገርን የማጥፋት እኩይ ተግባሩና አስተሳሰቦቹ ጋር ወደመቃብር ሲወርድ ብቻ ነው :: ህዝቡም ጨክኖ ለዚህ እውነት ሲነሳ ብቻ ነው::

ከመቼውም ጊዜያት በላይ ህዝባችንና አገራችን ለከፍተኛ ውርደት የተጋለጥንበት ሁኔታ ላይ ደርሰናል:: በሃገራችን መኖር አልቻልንም፣ በሃገራችን ጉዳይ ላይ መወሰን አልቻልንም ፣በሃገራችን ላይ የበይ ተመልካች ሆነን እንገኛለን፣ በህወሓት/ወያኔ ቀኝ ገዥነት ህዝባችንና አገራችን ለከፍተኛ ብዝበዛ ተጋልጠናል፣ በከፍተኛ ሁኔታ በታጠቁ የህወሓት/ወያኔ በዝባዞች ቁጥጥር ውስጥ ወድቀናል፣ ከፍተኛ ህዝብ ከረሃብ አልፎ ለከፍተኛ ጠኔ ተጋልጦ ይገኛል፣ ይህ አልበቃ ብሎ የአገሪቷ ህዝብ ወደ ውጭ ወጥቶ እንኳን እንዳይሰራ ለከፍተኛ ውርደት ተዳርጎ ማንም እንደፈለገው የሚያደርገውና ተከላካይ የሌለው በዓለማችን ላይ የሚገኝ ህዝብ ለመሆን በቅተናል::

ህዝቡ በአገር ውስጥ ለከፍተኛ ችግር ተጋልጦ ማንም እንደፈለግ የሚጫወትበት ህዝብ ከመሆኑም በላይ በየትኛውም ነገሩ ላይ ሃይማኖታዊ ጉዳዮቹን ጨምሮ በፈለገው መልኩ እንዳያከናውን መደረጉ ይታወቃል:: ከዚህም አልፎ ደግሞ የአገሪቷ መሬት በተለያዩ ጊዜያት ለተለይዩ ጎረቤት አገራትና ሃይሎች በመስጠትና በማካለል ትልቅ የታሪክ ውርደት ገጥሞናል:: ኢትዮጵያ መቼም ባልታየ መልኩ ለትልቅ ችግር ተጋልጣለች:: ይህንን ሁኔታ ለመቀየር ትልቅ መስዋእትነትን የሚጠይቅ ትግል ከፊታችን ተጋርጦብናል ይኸውም በህወሓት መቃብር ላይ አገራችንን እንደገና ለማከም የሚያስገድድ ሁኔታ ገጥሞናል:: የህዝብ መብት ጉዳይ ሲነሳ ግድያ፣እስራትና ሞት ሆኗል እጣችን የአገሪቷን ወሰን ለማስጠበቅ የተወሰደው እርምጃም ምንም ባለመሆኑ ዛሬ ኢትዮጵያ መሬቷንና የግዛት ክልሎቿን እየተነተቀጭ ትገናለች::

በአባቶቻችን ተከብረው የነበሩ ድንበሮችን አሳልፎ ለመስጠት ዛሬ ለሱዳንና ለኤርትራም ጭምር እንደፈለገ የሚደራደረው ህወሓት/ወያኔ ገና ያልጨረሳቸው ኢትዮጵያን የማጥፋት አላማዎቹ አላለቁም እና እንዲሁም ቀደምት ወራሪዎቻችን  የፈለጉትን መሬት አባቶቻችን በትግላቸው ያቆዩትን አገር በባንዳዎች በእጅ አዙር ለማግኘት እየጣሩ መሆኑና ለዚህም ተፈጻሚነት ደግሞ የህወሓት/ወያኔ የባንዳ ቡድን ሃላፊነት ወስዶ እየሰራ መሆኑን ስንመለከት ያሳዝናል::

የእነዚህ ባንዳዎች አስተሳሰባቸው እና ድርጊታቸው በኢትዮጵያ ላይ መቀጠሉ እንዲያበቃ ዛሬ በህብረት ሆ ብለን መነሳት ካልቻልን ተግባራቸውም ከመፈጸም ሊያቆሙ የሚችሉ አይደሉም :: ህወሓት/ወያኔን ለማሸነፍ ሰዎች የተለያዩ የትግል አማራጮች አዋጭ ናቸው ብለው ባሰቡበት መንገድ ሊሄዱ ይችላሉ፣ ይሁንና አሁን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ግን ህወሓት/ወያኔን በሰላማዊ ትግል እናሸንፋለን ለሚሉ ትግሉ ተገቢ ውጤት እንዲያመጣ ከተፈለገ ትግሉን ማቀጣጠልና በአጭር ጊዜ ወደውጤት እንዲመጣ ማድረግ ወይም ትግሉን ትቶ መውጣት ሌላኛው አማራጭ ይሆናል :: ምክንያቱም ህወሓት/ወያኔ በናንተ ስም የኢትዮጵያን ህዝብ እያታለለና ብልጭ ድርግም በሚለው የሰላማዊ ትግል ውስጥ አማራጭ እየመሰላችሁ እየገባችሁ የህዝቡን ተስፋ ሟሟጠጥና ከትግል ማራቅ በፍጹም አዋጭ የትግል ሥልት እንዳልሆነ ሁላችንንም እንረዳለን ለዚህም ምክንያቱ ደግሞ ህወሓት/ወያኔ በአገሪቷ ታሪክ ውስጥ የፈጠራቸው ዘርን ከማጥፋት ጀምሮ እስከግለሰቦችና ቡድኖች ጭምር ለወሰዳቸው ግፎች  የሚፈለግ ቡድን ከመሆኑም በላይ በትግራይ ህዝብ ሳይቀር በተለያዩ ቡድኖችና ግለሰቦች የሚፈለጉ ሰዎች ስብስብ በመሆኑ ሰላማዊ ሽግግርን ይፈልጋሉ ብሎ ማሰብ በፍጹም የሚታሰብ አይደለምና ነው::

ለዚህም ምስክር ይሆን ዘንድ በቅርቡ በራያ በተደረገው ስብሰባ ለአቶ አብርሃ አንድ ተሰብሳቢ ያቀረቡላቸውን ጥያቄ መስማት ብቻ ይበቃል እሱም ህወሃት የሽፍታ ቡድን መሆኑን እና ከእነሱ የሚያላቅቋቸው መሆኑን በጥያቄ መልክ ማቅረባቸውን “ሽፍታ” ማለት ደግሞ ምን ማለት እንደሆነ ለኢትዮጵያውያን በሙሉ የሚታወቅ በመሆኑ ነው::

ይህ ብቻ አይደለም በተለያዩ ጊዜያት አገርን በመክዳትና የአገሪቷንና የህዝቦቿን ጥቅሞች አሳልፎ በመስጠትም የሚፈለጉ ከመሆናቸውም በላይ በሠብዓዊ መብት ረገጣ በኩል አሁን ህወሓት/ወያኔን የሚመሩ ሃይሎች በአገራችን ውስጥ የተፈጸሙ የጅምላ ጭፍጨፋዎችን በማቀድ፣ በመተግበርና በማስተግበር በከፍተኛ ሁኔታ በአገር ውስጥና በውጭ ሃገራት የህግ አካላት እንደሚፈለጉ ጠንቅቀው የሚያውቁ መሆናቸውም ጭምር ነው::

ስለሆነም ይህ ችግራቸው ሊያመጣባቸው የሚችለውን አደጋ በማየት አገሪቷን ለመከላከል ሳይሆን ይህንን የራሳቸውን ችግር ለመቅረፍ የሚያስችላቸውን ሁሉ ለማድረግ እንደቆረጡና ይህንን ችግራቸውን ሊያቃልልላቸው የሚችልን ካልሆነም ጊዜ ሊያራዝምላቸው የሚችልን ሁኔታን ለመፍጠር ሲባል ማናቸውንም የአገሪቷን ጥቅሞች አሳልፈው ለመስጠት መቁረጣቸውን በቀላሉ መረዳት እንችላለን፣ በምንም መለኪያ ኢትዮጵያዊ እንዳልሆኑ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ላይ ከሚወስዱት አረመኔያዊ እርምጃ ልንመለከታቸው እንችላለን::

ከሁሉም በላይ ህወሓት/ወያኔ በተለያዩ ሰዓት የሚቀብራቸው በአንድ ወቅትና ወይም በተለያዩ ጊዜያት ሊፈነዱ የሚችሉ እምቅ ችግሮች በአገራችን ህዝቦች መካከል የፈጠራቸው እንዳሉ ሆነው አሁን ደግሞ ከጎረቤት አገራት በተለይም ከሱዳን ጋር ድንበር ለማካለል በሚል በሟቹ ጠቅላይ ሚኒስቴር ተጠንሥሶ የነበረውና አብሮት ያልተቀበረው አስተሳሰቡ ዛሬ በቀሪዎቹ የኢትዮጵያ ጠላቶች ሊተገበር ከፍ ዝቅ እያሉ ያሉበት ጊዜ በመሆኑና በሌላ በኩል ከህወሓት/ወያኔ ማንነትና ይዞት ከተነሳው ዓላማው አንጻር ህወሓት/ወያኔ ሲፈልግ ኢትዮጵያዊ ይሆናል ሳይፈልግ ደግሞ ታላቋ ትግራይ ይሆናል  ስለሆነም ለመሆኑ የማንን መሬት ነው ህወሓት/ወያኔ የሚደራደርበት ? ህዝቦች ለተወሰነ ጊዜ ሊጨቆኑ ይችሉ ይሆናል ሁል ግዜ ግን እየተጨቆኑ ይኖራሉ ማለት ግን እንዳልሆነ አውቆ መረዳት ያልፈለገው ህወሓት/ወያኔ እራሱ ላይ ትልቅ ችግርን ሊያመጣ መቃረቡን በትክክል መገመት ይቻላል::

ህወሓት/ወያኔ በምንም መለኪያ ኢትዮጵያዊ እንዳልሆነና ኢትዮጵያዊነት ምኑም እንዳልሆነ የራሱ ታሪክ ያሳየናል:: ለዚህም ማስረጃ ለታላቋ ትግራይ ሲሆን አሰብ ይካለላል ለኢትዮጵያ ሲሆን አሰብ የኤርትራ ይሆናል ፣ ለህወሓት/ወያኔ ሲሆን ህገመንግስት ይጣሳል ለህዝብ ጥቅም ሲሆን ይኸው ህገመንግስት እንደፈለገ ይተረጎማል፣ የኢትዮጵያውያን ደም በሳውዲ ሲፈስ ህገወጥ ያሰኛል ለዚሁ ሰብዓዊ ግፍ ካሳን ከሳውዲ መጥየቅ ሲግባ 360 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት እቅዶች ለሳውዲዎች ያሸልማል፣ በኢትዮጵያ ላይ የመበታተን አደጋ ስትፈጥር የነበረችው ሱዳን በአምላክ እጅ መልሷን አግኝታ ስትበታተንና ደረቅ መሬቷን ስትታቀፍ ለህወሓት በታታኝ ቡድን ላደረገችው አስተዋጾ ከ1200 ኪ. ሜ በላይ በሚሸፍን መሬት ላይ እስከ 50 ኪ.ሜ ወደ ውስጥ የሚገባን መሬት ለመስጠት ሲሆን ሽንጡን ገትሮ ህወሓት/ወያኔ ሲንቀሳቀስ ምን ይባላል ? ህዝብን የሚያሸብርና ሽብርተኛ እራሱ ህወሓት/ወያኔ ሆኖ ሳለ የህዝብ ወገኖች የሆኑ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ታጋዮች ምንም ትጥቅ ሳይኖራቸው በሽብርተኝነት እየተፈረጁ በየዕስር ቤቶች የሚንገላቱ ለመሆን በቅተዋል::

በአጠቃላይ ህወሓት/ወያኔ የኢትዮጵያዊነት መለኪያም ሆነ ተግባር የሌላቸው ህይሎች ስብስብ የሆነና በኢትዮጵያውያን ደምና ላብ የራሳቸውን የኢኮኖሚና የፖለቲካ የበላይነት ጥማት ለማርካት በቋመጡ  ሃይሎች የተዋቀረ ቡድን በመሆኑና ይህንን የማፍያ ቡድንን እኩይ ተግባርን ለማገዝ በነዚሁ ዘረኞች በተዋቀረ ሠራዊት እየታገዙ አገራችንን ይዘው ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠናልና አገራችንን ለማዳን መቁረጥ ይኖርብናል:: ማንም ሊረዳን አይችልም ትግላችን ወደፊት ሲገፋ ግን ብዙዎች አቋማቸውን አስተካከለው ከኢትዮጵያውያን ጋር ይወግናሉ:: ምክንያቱም አገራችን በህወሓት/ወያኔዎች የባንዳ ሃይሎች ብቻ ሳይሆን በታሪካዊ ጠላቶችችንም እጅ ስር በመውደቃችንም ጭምር ነውና ::

ህወሓት/ወያኔ በወልቃይት ጥገዴ ህዝብ ላይ የፈጸመው የዘር ማጥፋት ዘመቻ በሰላም የተጠናቀቀ መስሎት ከሆነ ተሳስቷል:: የወልቃይት ጠግዴ ህዝብ፣ የሲዳሞ ህዝብ፣ የጋምቤላ ህዝብም ሆነ ሌሎች የህወሓት/ወያኔ የጅምላ ጭፍጨፋ ተጠቂዎች ሁሉ እንዳልተሸነፉ መታወቅ ይኖርበታል በእርግጥ መከራቸው ሁሌም የሚያደማ ቢሆንም :: ይልቁንም ህወሓት/ወያኔ አሁንም ሆነ ለወደፊትም ቢሆን በህዝብና በታሪክ ፊት በፍርድ ፊት ሊሆን የቀረበበት ጊዜ ነው:: ህወሓት/ወያኔ የሚቀብራቸው ፈንጂዎች ምን አልባትም በመጀመሪያ የሚያጠፉት እራሱን ህወሓትን/ወያኔን እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ:: ምክንያቱም ለህዝቦች መከፋፈልና እልቂት የቀበራቸው ፈንጂዎች አቅጣጫቸውን ወደ እራሱ  ወደ ህወሓት/ወያኔ እያደረጉ በመሆኑም ጭምር ነው:: ህወሓት/ወያኔና ባለሟሎቹ የኢህአዴግን ስም ተከናንበውና ተሸፋፍነው በህዝብ ላይ የሚፈጽሙትን ደባ ለማስቆም በሚደረገው ትግል ውስጥ ተሳትፎአችንን እናጠናክር በህወሓት/ወያኔ መቃብርም ላይ አዲሲቷን ኢትዮጵያ በጋራ እንመስርት:: ካልሆነ ህወሓት/ወያኔ አገሪቷን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሊበታትናት መቁረጡን ከድርጊቱ መመልከት እንችላለን:: ቸር ይግጠመን::

http://www.zehabesha.com/

አቶ ሙሐመድ ኢብራሒም ማእከላዊ እስር ቤት ዉስጥ በደረሰባቸው ድብደባ ህይወታቸዉ ማለፉ፤ ሆድ-እቃቸዉ ተከፍቶ ኩላሊታቸዉ መሰረቁ ታወቀ

አስክሬን ምንሊክ ሆስፒታል ሄደን እንድንወስድ ስልክ ተደወለልን ለሞቱከደነገጥነዉ በላይ አስክሬኑን ስንመለከት ፍጹም ተረብሸናል ከአዉሬ አፍ የተረፈአስክሬን ነበር ሚመስለዉሰዉነቱ ተቦጫጭቋል!”  ጓደኞች

አቶ ሙሐመድ ኢብራሒም ማ

አቶ ሙሐመድ ኢብራሒም ማ

ዋሽንግተን ዲሲ፤ ህዳር 30/2006 (ቢቢኤን) ፦

ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ ወይም ቪዲዮውን ለማየት እዚህ ላይ ይጫኑ።

ሚሚ ስብሃቱ ጠረጴዛ ምን ያደርግላታል?

ከዳዊት ሰለሞን

mimi sibehatuጠረጴዛ ከመመገቢያነት፣ለመጻፊያ ማስደገፊያነትና ከቁሳቁስ ማስቀመጫነት በተጨማሪ በዙሪያው በሚኮለኮሉት ወንበሮች የተነሳ ሰዎችን በአንድነት መሰብሰብ በመቻሉ የሐሳብ መንሸራሸሪያ መድረክ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡በጠረጴዛ ዙሪያ የሚቀመጡ ግለሰቦችና ቡድኖች በፊት ለፊታቸው በተዘረጋው ጠረጴዛ ላይ ሐሳባቸውን፣አመለካከታቸውንና አይዶሎጂያቸውን ያቀርባሉ፡፡የተጣሉ፣ልዩነት ያለባቸው ወገኖችም በጠረጴዛ ዙሪያ ቅራኔያቸውን ለማጥበብ ይደራደራሉ፡፡

ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ ወይም ቪዲዮውን ለማየት እዚህ ላይ ይጫኑ።

http://www.ethiopianreview.info

የወያኔ መንግስት በኦሮሞ ወጣቶች ላይ በተደጋጋሚ እየፈፀመ ያለው የግፍ ግድያ, በኦሮሞ ህዝብ ላይ የከፈተው የዘር ማጥፋት ዘመቻ አካል ነው!

A statement from the Qeerroo Oromo Youth Movement.

———————–

Gadaa.com

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ገበታው ላይ እያለ በወያኔ ታጣቂዎች በግፍ የተገደለው ወንድማችን ግድያ አጥብቀን እናወግዛለን!

የወያኔ መንግስት በኦሮሞ ወጣቶች ላይ በተደጋጋሚ እየፈፀመ ያለው የግፍ ግድያ, በኦሮሞ ህዝብ ላይ የከፈተው የዘር ማጥፋት ዘመቻ አካል ነው!

ወጣት አንተነህ አስፋው ለገሰ በ1983 ዓ.ም በዲላ ዞን፣ ፍሰሀ ገነት ወረዳ፣ ቀበሌ 02 ተወለደ፡፡ ይህ ወጣት ተማሪ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የ3ኛ ዓመት የማርኬቲንግ ክፍል /department/ ተማሪ ሲሆን ወደ ዩኒቨርሲቲ በ2004 ዓ.ም የገባና በ2006 ዓ.ም ይመረቅ የነበረ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ህዳረ 24/2006 ዓ.ም ቁጥራቸው ከ60 በላይ ከሚሆኑ ከክፍሉ ተማሪዎች ጋር በመሆን ዳሽን ቢራ በተባለ ቦታ የግብዣ ፕሮግራም አድርገው ነበር፡፡ ከግብዣው ፕሮግራም በኋላ ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ወደ ዩንቨርሲቲው ቅጥር ግቢ እየተመለሰ ሳለ የኦሮሞ ተማሪዎች ለብቻቸው ተነጥለው የትግል ዘፈኖችን እየዘፈኑ ይሄዱ ነበር፡፡ የሀበሻ ልጆችም አካባቢውን በጩኸት በመበጥበጥ በመንገድ ላይ ሲንቀሳቀስ የነበረውን ሰው ሁሉ ሲደበድቡ ነበር፡፡ የኦሮ ልጆች በወቅቱ የትግል ዘፈኖችን ከመዝፈን ውጪ ያነሱት ሁከት አልነበረም፡፡ ሆኖም ግን ከዳሽን አለፍ ብለው “ቀሀ” የተባለውን ወንዝ ተሻግረው 18 ቀበሌ ሲደርሱ የሀበሻ ልጆች መንገዱ ላይ ተሰማርተው የነበሩ የወያኔ ታጣቂዎች ላይ ድንጋይ መወርወር ጀመሩ፡፡ የወያኔ ታጣቂዎችም እየረበሹ ያሉትን የሀበሻ ልጆች ትተው ትኩረታቸውን የኦሮሞ ልጆች ላይ በማድረግ እናንተ ኦነግን ታወድሳላችሁ በማለት ተኩስ ከፈቱባቸው፡፡ በወቅቱ በግንባር ቀደምትነት የትግል ዘፈኖች እየዘፈነ የነበረው አንተነህ አስፋው ሲሆን እሱን ጀርባው ላይ በመምታት ሌሎቹን በተኗቸው፡፡ ይህ ልጅ የተመታው ከምሽቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ሲሆን ወዲያውኑ ወደ ዩኒቨርስቲው ሆስፒታል የተወሰደ ቢሆንም የደረሰበት ጉዳት ከባድ በመሆኑ ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል እንደተወሰደ እያለ ሂወቱ ሊያልፍ ችሏል፡፡ ከልጁ ሞት ጋር በማያያዘ ህዳር 25/2013 ከ3,000 – 4,000 የሚሆኑ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በተለይ የኦሮሞ ልጆች ወደ ሆስፒታሉ በሚወስደው መንገድ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣት “we need freedom””ነፃነት እንፈልጋለን” በማለት ድምፃቸውን አሰምተዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲውን ንብረት ያወደሙ ሲሆን እስካሁን ድረስ በዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ የሚገኘው የኦሮሞ ተማሪ፣ አስተማሪና ሌሎች ሰራተኞች ትምህርትና ስራቸውን አቋርጠዋል፡፡ የሀበሻ ልጆች ግን ወደ ትምህርታቸው ተመልሰው እየተማሩ ናቸው፡፡ ወያኔ ይህን ስልት የተጠቀመው የኦሮሞ ልጆችን ለመጨረስ ነው ሲል የሪፖርቱ ምንጭ ይገልፃል፡፡ “በጥይት ተመትቶ ህይወቱ ያለፈውን ወገናችንን ደም ሳንበቀል አንቀመጥም ትምርቱም ይቅርብን” ብለው በርካታ ቁጥር ያላቸው የኦሮሞ ልጆች ትምህርታቸውን አቋርጠው እንደሚገኙ ሪፖርቱ ይገልፃል፡፡

ድል ለኦሮሞ ህዝብ!

ገዳው የነፃነት ነው!

http://gadaa.com

መንግስት ነን ብላችሁ፤ አገር እያስተዳደራችሁ እንደሆነ ለምትቆጥሩ ግን ሞራል ለሌላችሁና ሀላፊነት ለማይሰማችሁ የሀገራችን ገዥዎች

ከመልካም ብሥራት

ማርም ሲበዛ ይመራል ይላሉ አበው፡፡ ውሸታችሁ፤አስመሳይነታችሁ፤ ወሰን ያጣው በቀለኝነታችሁ፤ አቅመቢስነታችሁ፤ ዘረኝነታችሁ፤ ሙሰኝነታችሁ….ኧረ ስንቱ የናንተ ነገር ተዘርዝሮ ያልቃል? በዛ፤ መረረንም፡፡ መንግስት ህዝብን ወክሎ የአንድን ሀገር ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ የሚመራ ተቋም ሆኖ በእንቅስቃሴዎቹ ሁሉ ታሳቢና ተቀዳሚ የሚያደርገው የህዝብን ተጠቃሚነትና የሀገርን ልማት፤

ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ ወይም ቪዲዮውን ለማየት እዚህ ላይ ይጫኑ።

http://www.ethiopianreview.info

ሃገሪቷን የስደት ሃገር ያደረገው ራሱ መንግስት ነው

  • “ዜጐች የተሰደዱት መንግስት የሥራ ዕድል ባለመፍጠሩ ነው”

መንግስት ከሣውዲ የሚመለሱ ዜጐች ቁጥር አስቀድሞ ከተገመተው በላይ መሆኑን ገልጿል። ቀድሞ የተመላሾቹ ቁጥር  “ዜጐች የተሰደዱት መንግስት የሥራ ዕድል ባለመፍጠሩ ነው”

28 ሺህ እንደሚሆን ቢገመትም አሁን ወደ 80ሺህ እንደሚደርስ ተነግሯል፡፡ በስደተኞቹ ላይ እየደረሰ ያለውን እንግልት

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም፤ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ከማውገዝ አልተቆጠቡም፡፡ ጉዳዩ በሰከነና

የዲፕሎማሲ መርሁ በሚፈቅደው መንገድ መያዙንም ገልፀዋል፡፡ መንግስት ከዚህ በላይ በዲፕሎማሲው ርቆ ሊሄድባቸው

የሚችልበት አማራጮች  እንደሌሉ የሠሞኑ መግለጫዎቹ ያመለክታሉ፡፡ ይሁን እንጂ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ

ሣይንስ ምሁሩ ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ መንግስት የዜጐቹን መብት በማስከበርም ሆነ የሃገርን ክብር በማስጠበቅ ረገድ ምንም

አልተራመደም ይላሉ – ተመላሾቹን ከመቀበል የዘለለ ዲፕሎማሲያዊ እርምጃዎች መውሰድ አለመቻሉን በመግለፅ፡፡ ዶ/ር

መረራ ጉዲና በጉዳዩ ዙሪያ የሰጡንን አጭር ማብራሪያ እነሆ:-

በሣውዲ አረቢያ በዜጐቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ተከትሎ መንግስት ጉዳዩን የያዘበትን መንገድ እንዴት

ገመገሙት?
ሁለት ሶስት ነገሮች አሉ፡፡ አንደኛው አሜሪካ፣ ጀርመን፣ ስዊድን በመሳሰሉት ሃገሮች ያሉ ኢትዮጵያውያን በሣውዲ

አረቢያ ላይ ተቃውሞ ሲያሰሙ እየፈቀዱላቸው፣ እዚህ መከልከሉ በዜጐች ላይ ተጨማሪ ወንጀል መስራት ነው፡፡

ሁለተኛው በተለያየ መንገድ እየሰማን እንዳለው አሁንም ቢሆን በ40ሺህ የሚቆጠሩ ዜጐች እየተንገላቱ ነው፡፡ እሪታና

የይድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ደግሞ የሚያወራው ሌላ ነው፡፡ መደብኩ እንኳን ያለው 50

ሚሊየን ብር አንድ እነሱ “የመንግስት ሌባ” የሚሉት የሚሠርቀው እኮ ነው። 50 ሚሊየን ብር ለ70ሺህ ሰው ነው

የመደቡት። ነገር ግን በሙስና የተከሰሱት ሰዎቻቸው እኮ የዚያን ሶስት እጥፍ ሰርቀዋል ተብሏል፡፡ በእውነቱ የተመደበው

ገንዘብ በጣም ትንሽ ነው፡፡ ሌላው ደጋግመው የሚያሰሙት፤ የሣውዲ አረቢያ መንግስትን ድርጊት የሚኮንን ሳይሆን

ወዳጅነት እንዳይበላሽ ትልቅ ስጋት ያላቸው የሚያስመስላቸው ነው፡፡ ከዜጐች ድብደባ፣ ግድያና እንግልት ይልቅ

የሣውዲ መንግስት ፍቅር የያዛቸው ነው የሚመስለው፡፡ ስለዚህ በሚፈለገው መንገድ ለጉዳዩ ምላሽ እየሰጡ አይደለም

የሚል መደምደሚያ ላይ መድረስ ይቻላል፡፡ ድሮውንም ቢሆን እነዚህ ዜጐች የተሰደዱት የኢትዮጵያ መንግስት የስራ

እድል መፍጠር ባለመቻሉ ነው፡፡ ሃገሪቷን የስደት ሃገር ያደረገው ራሱ መንግስት ነው፡፡
በሃላፊነትም ያስጠይቀዋል፡፡ ስለዚህ መንግስት በቀን ይሄን ያህል ሰው መለስኩ ከሚል፣ በመሠረታዊነት ዜጐች

የማይሰደዱባት ሃገር መፍጠር አለበት፡፡ የስራ እድል ሊኖርና የሰብአዊ መብት ሊከበር ይገባል፡፡
መንግስት በዜጐቹ ላይ ለተፈፀመው ግፍ፣ በአለማቀፍ ፖለቲካዊ ዲፕሎማሲው ምን ድረስ ነው ሊሟገት የሚችለው?
መንግስት እኮ ደጋግሞ የሚነግረን በህገወጥ መንገድ ከሃገር የወጡ ናቸው እያለ ነው፡፡ እንኳን በዚህ ዘመን ቀርቶ በጥንት

ዘመንም ስደተኞች ክብር አላቸው፡፡ ዝም ብሎ ይገደሉ፣ ይፈለጡ፣ ይቆረጡ አይባልም፡፡ ስለዚህ ሣውዲ አረቢያ ኋላቀር

በሆነ መንገድ ዜጐቻችንን ስታንገላታ በህግ መክሰስም ይቻላል፡፡ ሌላ አማራጭ ከተፈለገም እንደወዳጅ መንግስትና

የንግድ ሸሪክ ብዙ ተጽእኖ ማድረግ ይቻላል፡፡ ይልቁንስ የኢትዮጵያ መንግስት እያየ ያለው፣ እዚህ ያሉ ተቃዋሚዎች ምን

አሉ የሚለውን ብቻ ነው፡፡ ተቃዋሚዎች ከሰሱን፣ አጣጣሉን የሚለው ላይ ነው ያተኮረው፡፡
ከዚያም ሲያልፍ ሌት ተቀን እንደ መጽሐፍ ቅዱስ የሚነግረን ዜጐቹ በህገወጥ መንገድ መሄዳቸውን ነው፡፡ ዋናው ጉዳይ

መጀመሪያ የዜጐችን ነፍስ ማዳን ነው፤ ሌላው ደግሞ ለስደት የዳረገንን የኢኮኖሚ ችግር በመፍታት፣ ኢትዮጵያን ከስደት

ሀገርነት ዝርዝር ለማውጣት መንቀሳቀስ አለበት፡፡ ግን አሁን ባለው ሁኔታ የዚህ አዝማሚያ እምብዛም እየታየ አይደለም፡፡
መንግስት በሣውዲ አረቢያ ላይ ይከተል የነበረውን የዲፕሎማሲ አቅጣጫ ለመፈተሽና ለመቀየር የእነዚህ ዜጐች እንግልት

ምክንያት ሊሆን ይችላል ብለው ያስባሉ?
አሁን እኮ መንግስት ጠንከር ያለ መግለጫ እንኳ አላወጣም፡፡ በመኮነን ደረጃ እንኳ ደፍሮ መግለጫ ማውጣት

አልቻለም፡፡ ሌሎች ሀገሮች እኮ ቢያንስ በዜጐቻቸው ላይ በደል ሲፈፀም በመንግስት ደረጃ የመረረ ጩኸት ያሰማሉ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ግን ከህዝቡ ጋር አብሮ ሊጮህ ቀርቶ፣ የህዝቡንም ድምጽ እያፈነ ነው፡፡ ለዚህ ነው በተለይ

በፖለቲካ ዲፕሎማሲው በኩል እየተወሰደ ያለው እርምጃ በቂ አይደለም የምለው፡፡
መንግስት ዜጐቹን ከሃገሪቱ ከማስወጣት ባለፈ እርምጃ ያልወሰደው የኢኮኖሚ ጥገኝነት ጉዳይ ስላለ ነው፤ የኢትዮጵያ

ዋነኛዋ የውጪ ንግድ ሸሪክ ሣውዲ በመሆኗ ነው የሚሉ አስተያየቶችንስ እንዴት ያዩዋቸዋል?
በእርግጥ የኢኮኖሚ ጥገኝነቱ አለ፡፡ እናውቃለን። ታላላቅ የሣውዲ አረቢያ ከበርቴዎች በዚህች አገር ኢንቨስት ያደርጋሉ፡፡

ነገር ግን ለኢኮኖሚ ሲባል የዜጐችን መብትና ብሔራዊ ጥቅምን አሣልፎ መስጠት በየትኛውም የፖለቲካ አማራጭ ፈጽሞ

አይመከርም፡፡ ከምንም በላይ የዜጐች መብትና የሃገር ክብር ይቀድማል፡፡ በመቶ ሺህ የሚቆጠር ሰው እየተንገላታ

ለኢኮኖሚ ጥገኝነቱ ሲባል ዝምታን መምረጥ እንዲሁም የዜጐችን ጩኸት ወደማፈኑ መሄድ ተገቢ አይደለም፡፡
አንድ መንግስት በሌላ ሀገር የሚኖሩ ዜጐቹን መብት ለማስከበር ከአለማቀፍ ህግና ፖለቲካ ተመክሮ አንፃር ምን ያህል

ርቀት ነው ሊጓዝ የሚችለው?
ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ጨርሶ እስከማቋረጥ ይደርሳል፡፡ ከዲፕሎማሲ ግንኙነት ማቋረጥ ባለፈም ችግሩን ለአለማቀፉ

ህብረተሰብ በጩኸት ማሰማትም ይገባል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ግን አፉን ሞልቶ ‘በዜጐቻችን ላይ እየተሰራ ያለውን

ግፍ እንኮንናለን’ ለማለት እንኳ እየጨነቀው ነው፡፡ እዚህ ያለውን ኤምባሲ እንኳ ሲያነጋግሩ፣ ዋናውን አምባሳደር

አይደለም፡፡ በሰለጠኑትን ሃገሮች ደረጃ ቢሆን በ30ሺህ፣ 60ሺህ የሚቆጠሩ ዜጐች እንዲህ ያለ እንግልት ሲደርስባቸው

ቀላል ጉዳይ አድርገው አይመለከቱትም፡፡ የህንድ፣ የፊሊፒንስ እና የሌሎች ሃገሮች ዜጐች ከኢትዮጵያውያኑ በተለየ

ክብራቸው ተጠብቆ ነው ከሃገር የወጡት፡፡ ይሄ ለምን ሆነ ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡
የስደተኞቹ ስቃይ ለፖለቲካ መጠቀሚያነት እንዳይውል መንግስት ጠይቋል፡፡ በእርግጥ ለፖለቲካ መጠቀሚያነት ውሏል?
የኢትዮጵያ ዜጐች በያሉበት ብሶት እያሰሙ ነው። በተለያዩ መንገዶች በየሃገራቱ በኢትዮጵያውያኑ ላይ የሚፈፀሙት

በደሎች ሲሰሙ ይዘገንናሉ፡፡ እኛ እኮ እየጠየቅን ያለነው የእነዚህ ኢትዮጵያውያንን መብት ነው፡፡ ነገር ግን መንግስት

ጉዳዩን በሌላ እየተረጐመው እኮ ነው የተቸገረው፡፡

http://www.ethiosun.com